ፆም በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ስፍራ
አለው፡፡ ፆም ለህይወታችን የሚጠቅመውን ነገሮች ከእግዚአብሄ ቃል እንመልከት
1.
ስጋ ያለልክ እንዳይጠግብ ይጠቅማል
ፆም እግዚአብሄርን
የማይፈልገው የወደቀው የሃጢያት ማንነት እንዳያይል ስጋን ለመጎሸም እና ለእግዚአብሄር ፈቃድ ብቻ ለማሰገዛት ይጠቅማል፡፡
ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡27
2.
ፆም ስጋችን እንዳይከብደው
ያደርጋል
ምግብን የማድቀቅ ስርአት
በጣም ጉልበትን የሚጠይቅ ስርአት ነው፡፡ ሰውነታችን የምግብን ውህደት ሂደት የሚያካሂደው እንደትልቅ ፋብሪካ ነው፡፡ ከባድ ምግብ
ልክ እንደበላን ድካም ድካም የሚለን ስለዚህ ነው፡፡
ፆም የሰውነታችንን
ትልቅ የምግብ ማድቀቅ ስርአት ነፃ በመሆን ሰውነታችን ቀለል እንዲለውና እንድንነቃ በመንፈሳዊ ሁኔታ ላይ እንድናተኩር ይረዳናል፡፡
3.
ፆም በመንፈሳዊ ነገር ላይ
እንድናተኩር ይረዳል
ፆም በማይታየው በእግዚአብሄር በአምልኮ ላይ እንድናተኩር ያደርገናል፡፡ ፆም ስጋችነነ
ስለሚያደክመው የምድሩን ሳይሆን ቅድሚያ መስጠት ያለብንን ሰማያዊውን እንዳናስብ ይረዳናል፡፡
በአንጾኪያም
ባለችው ቤተ
ክርስቲያን ነቢያትና
መምህራን ነበሩ፤
እነርሱም በርናባስ፥
ኔጌር የተባለው
ስምዖንም፥ የቀሬናው
ሉክዮስም፥ የአራተኛው
ክፍል ገዥ
የሄሮድስም ባለምዋል
ምናሔ፥ ሳውልም
ነበሩ። የሐዋርያት ሥራ 13፡1
4.
ፆም መንፈስ እንዲያሸንፍ ይረዳል
ፆም መንፈስን እንዲያሸንፍ
መንፈስን ለመደገፍ ይጠቅማል፡፡ ፆም ስጋ እንዳያሸንፍ ለመጫን ይጠቅማል፡፡
ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥
እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡17
የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡24
5.
ፆም ለመንቃት ይጠቅማል
ብዙ ስንበላ እንቅልፍ
እንቅልፍ ይለናል መንቃትም ይከብደናል፡፡ ብዙ ካልባለን ግን ነቅተን ስራችንን ማቀላጠፍ እንችላን፡፡
በጣም ብዙ በልቶ ከተኛ
ሰው እና ጥቂት በልቶ ከተኛ ሰው መካከል ማነትው ንቁ እና ቶሎ የሚነቃው ብንል ትንሽ በልቶ የተኛው ሰው ነው፡፡ ብዙ ከጠጣውና
ጥቂት ከጠጣው ሰው መካከል ማነው በቶሎ ሊነቃ የሚችለው ብለን ብንመለከት ጥቂት የጠጣው በቶሎ ነገሮችን ማስተዋል ወደ አእምሮው
መመለስ እንደሚችል እናስተውላለን፡፡
በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡8
6.
ስጋ ፍላጎቱ እንዲገደብ ያደርጋል
ስጋ በሰጠነው መጠን ሌላ ይጠይቃል፡፡ ስጋ ባሟላልነት መጠን የሚቀጥለውን ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ፆም ስንይዝ ስጋ በምግብ
ጥያቄ ብቻ ላይ እንዲቆም እንገድበዋለን፡፡
ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ
ለመከልከል ምንም አይጠቅምም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡23
7.
ፆም የስጋችንን ድምፅ በመቀነስ የመንፈስን ድምፅ እንድንሰማ ይረዳናል
ፆም የስጋን ድምፅ በመቀነስ የመንፈስ ድምፅ እንዲያይል ለማድረግ ይጠቅማል፡፡
እግዚአብሄር በመንፈሳችን አማካኝነት ሁልጊዜ ፈቃዱን ይናገራል፡፡ የመንፈስን ድምፅ ለመስማይት የሚያስፈልገውን ነገር
ማድረግ ያለብን እኛ ነን፡፡ ስጋውን እንደፈለገ የሚመግበው ሰው የመንፈስን ድምፅ ለመስማት ይቸግረዋል፡፡ በፆም የስጋውን ድምፅ
የሚያዳክም ሰው ግን የመንፈስን ድምፅ በጥራት መስማት ይችላል፡፡
እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡6
በፀሎት እግዚአብሄርን ይበልጥ መስማት የምንችለው ስንፆም ነው፡፡
ትጸልዩም ዘንድ በመጠን
ኑሩ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ፆም
#ፀሎት #ስጋ #መንፈስ #ነፍስ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #አምልኮ #መስማት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እምነት #ቃል
#ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment