Popular Posts

Sunday, November 17, 2019

የማንጠቅም ባሪያዎች

እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። የሉቃስ ወንጌል 17፥10
አንዳንድ ጊዜ አገልግለን ሰጥተን ጠቅመን ነገር ግን መጨረሻ ላይ የምናፈርሰው በአመለካከታችን አለመስተከካል ምክንያት ነው፡፡
ሲጀመር አገልግሎት መስጠት መጥቀም የሚጀመረው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ አገልግሎት መጥቀም መስጠት የሚጀመረው እግዚአብሄርን ከማመስገን ከምስጋና ልብ ነው፡፡
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡15
ለሌላው አገልግሎት መጥቀም መባረከ ለእኛ ለመገልገል ለመጠቀም ለመባረክ መሆን የለበትም፡፡ አገልግሎት መጥቀም መባረክ እኛ አስቀድመን በእግዚአብሄር ስለተገለገልን በእግዚአብሄር ስለተባረክንና በእግዚአብሄር ስለተጠቀምን ነው፡፡
አገልግሎት መጥቀም መባረክ ተደርጎልኛል ተቀብያለሁ ተሞልቻለሁ ከሚል ከምስጋና ልብ ካልመጣ ሙሉ ፍሬ አያፈራም፡፡
ሌላውን መጥቀም መባረከ እና ማገልገል ተደርጎልኛል ተባርኬያለሁ ተጠቅሜያለሁ ከሚል የምስጋና ልብ ከመጣ ውለታን ለመክፈል ይተጋል እንጂ ውለታ እንዲዋልለት አይጠብቅም፡፡
ተጠቅሜያለሁ ተባርኬያለሁ ተቀብያለሁ የሚል ሰው የሚያደርገውን ሁሉ በምስጋና ልብ ያደርገዋል እንጂ ስለሚያደርገው ማንኛውም ነገር ምስጋናን አይጠብቅም፡፡
እግዚአብሄር ለህይወቱ ሙሉን ዋጋ ከፍሎለት በከበረው በክርስቶስ ደም የገዛው ሰው ራሱን ሊሰጥ ሊያገለግል ጌታውን ሊያስደስት እንጂ ጎሽ እንዲባል እንዲጨበጨብለት አይጠብቅም፡፡
በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡12
ልጁን ኢየሱስን ከፍሎለት ከጥፋት ከሞት ከመቅበዝበዝና ከከንቱነት ያደነው ሰው ለጌታው የሚጠቅም እቃ በመሆኑ ብቻ ይደሰታል እንጂ ጌታው ስለተጠቀመበት ከጌታው ክፍያ እና ከሚያገለግለው ምስጋናን አይጠብቅም፡፡
ልጁን ኢየሱስን ከፍሎለት ለዘላለም ከእግዚአብሄር ከመለየት የዘላለም ሞት ያዳነው ሰው እግዚአብሄር ስለተጠቀመበት ብቻ ራሱን እንደ እድለኛ ያደርጋል እንጂ ስለተጠቀመበት ዋጋን አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ታዘዘኝ አገልግለኝ የሚለው ሰው በፊት ከሰይጣን ስልጣን በፊት የወደቀ ሰው ነበር፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡1-2
ልጁን ከፍሎ ከጠላት መንግስት ያዳነው ሰው ወደ እግዚአብሄር አላማ በመመለሱ እና ጌታ ለአለማው ስለተጠቀመበት ብቻ ደስ ይለዋል አገልግሎቱንም በነፃ ይሰጣል እንጂ ስለመታዘዙ ክፍያን አይጠይቅም፡፡
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡13-14
ልጁን ኢየሱስን በመስቀል ላይ ሰውቶ ያዳነው ሰው እግዚአብሄር ካልተጠቀመብኝ ለምንም የማልጠቅም ሰው ነበርኩ ብሎ ራሱን ያዋርዳል እግዚአብሄርም ስለተጠቀመበት ብቻ ደስ ይለዋል እንጂ እንደ እኩያ ስለደሞዝ ስለምስጋና ስለክብር አይደራደርምን፡፡
ከእግዚአብሄር በቀር በጎነት የለንም፡፡ የምንጠቅም ካደረገን እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙረ ዳዊት 16፡2
እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። የሉቃስ ወንጌል 17፥10
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ#ዝቅታ ትህትና#ኢየሱስ #ጌታ#መሪነት #ቤተክርስትያን#አማርኛ #ስብከት#መዳን #መፅሃፍቅዱስ#መጋቢ #እምነት#ተስፋ #ፍቅር#ጌታ #ሰላም#ደስታ #አቢይ#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ#እወጃ #መናገር#ፅናት #ትግስት#መሪ

No comments:

Post a Comment