Popular Posts

Thursday, November 21, 2019

ተምሬአለሁ



የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13
በክርስትና ህይወት በምናልፍበት የህይወት ዝቅታና ከፍታ የምንማረው እጅግ ውድ የሆነ ትምህርት ይበቃኛል ማለትን ነው፡፡
ሰው ይበቃኛል የሚለውን ከተማረ በእውነት እጅግ ውድ የሆነ ትምህርት ቀስሟል ማለት ነው፡፡ ሰው በሚያልፍፈበት ነገር ውስጥ ሁሉ ይበቃኛል የሚለውን ካልተማረ ገና አልተማረም ማለት ነው፡፡
ሰው ሌላውን ለማገልገል ዝግጁ የሚሆነው ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡ ሰው ለሌላው የሚተርፈው ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡ ሰው ሌላውን የሚያገለግልበት ነገር የሚኖረው ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡  
ሰው ራሱ ካላቆመው የሰው ልጅ ፍላጎት የማያልቅ እንደሆነ የሚረዳው ለመኖር ብዙ እንደማያስፈልገው ሲረዳ ብቻ ነው ፡፡ ሰው ከማያልቅ የሰው ልጅ የሩጫ ውድድር ራሱን የሚያገለው ለመኖር ብዙ እንደማያስፈልገው ሲረዳ ብቻ ነው፡፡ ሰው የዚህን አለም ፉክክር ከንቱነት የሚረዳውና ጌታን ለማገልገል ራሱን የሚሰጠው ያለኝ ይበቃኛል የሚለውን ሲማር ብቻ ነው፡፡
በእግዚአብሄር ዘንድ የተማረ የሚባለው ሰው ማግኘትም ማጣትም ምንም እንዳይደሉ የሚረዳ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሄር አይን የተማረ የሚባለው ማግኘትም ማጣትም ምንም ነገር እንደማያስችሉ የተረዳ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ የተማረ የሚያስብለው ማጣት ሁሉን ማድረግን እንደማይከለክል ማግኘት ሁሉን ማድረግን እንደማያስችል መረዳት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ የተማረ የሚያስብለው ያጣንም ሆነ ያገኘንም ሰው የሚያስችለው ማግኘታቸው ወይም ማጣታቸው ሳይሆን ክርስቶስ እንደሆነ መረዳት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የተማረ የሚባለው ክርስቶስ ሁሉን እንደሚያስችል የተረዳ ሰው ነው፡፡
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
ሰው የተማረ የሚያሰኘው ማግኘትንም ማጣትንም ትክክለኛ አቅማቸውን ማወቁ ነው፡፡ ሰው የተማረ የሚያሰኘው ለማግኘት ከሚገባው በላይ ትኩረት አለመሰጠቱ ነው፡፡ ሰው የተማረ የሚያሰኘው ማግኘትን ከአቅሙ በላይ ዋጋ አለመስጠቱ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማግኘት ሊያደርግ የሚችለውንና ሊያደርግ የማይችለውን ነገር ለይቶ መረዳት ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው የክርስቶስ ሃይል እንጂ ማግኘትም ሆነ ማጣት በህይወት ላይ ምንም እንደማይጨምሩ ማወቁ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማጣት በህይወት ላይ ምንም እንደማያጎድል መረዳቱ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማጣት ህይወታችንን ሊያበላሽ እቅም እንደሌለው መረዳቱ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው በህይወት ማጣት ከህይወት አላችን እንደማያግደንንና አቅምን እንደማያሳጣን ልኩን ማወቁ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማጣትን ልኩን ማወቁና አለመፍራቱ ነው፡፡
የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መጥገብ #መራብ #መብዛት #መጉደል #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment