እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ምልክና አምሳል
ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር
ክብር ነው፡፡
እንስሳት በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ስላልተፈጠሩ
በምግብ ብቻ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እንስሳት በእግዚአብሄር እንስሳት ሰው እንደ እንስሳት በምግብ ብቻ መኖር አይችልም፡፡ ሰው ለመኖር
ከምግብ ያለፈ ነገር ያስፈልገዋል፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ ግቡን እንዲመታ ከምግብ ከፍ ያለ ነገር ይጠይቃል፡፡
የእግዚአብሄርን ቃል መቀበል ያቆመውን አዳምን
እግዚአብሄር ያለው ሞትን ትሞታለህ ነው፡፡ በእግዚአብሄር እይታ የእግዚአብሄርን ቃል በታዘዘ ቀን አዳም ህይወትን መኖር አቁሟል፡፡
የእግዚአብሄርን ቃል በጣለ ቀን አዳም በስጋ ይኑር እንጂ በመንፈስ ከህይወት ምንጭ ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይቷል፡፡
ሰው የእግዚአብሄር ቃል ከማግኘቱ በፊት የሚኖረውን
ኑሮ እግዚአብሄር ኑሮ አይለውም፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ከመታዘዙ በፊት የሚኖረው ኑሮ የት ኑሮ እንጂ ህይወት አይደለም፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡1-3
ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ከመቀበሉ በፊት የሚኖረው
ኑሮ የቁጣ የመርገም ህይወት ነው፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር
ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። የዮሐንስ ወንጌል 3፡36
ኢየሱስ
ወደ ምድር የመጣው እግዚአብሄር ቃል በኩል ህይወት እንዲሆነን እንዲበዛልን ነው፡፡
እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። የዮሐንስ ወንጌል 10፡10
ሰው ህይወትን የሚጀምረው የእግዚአብሄን ቃል መቀበል
ሲጀምር በነው፡፡ ሰው ህይወቱ የሚበዛው የእግዚአብሄር ቃል በህይወቱ ሲበዛ ነው፡፡ ሰው ህይወትን በሙላት የሚኖረው የእግዚአብሄር
ቃል በሙላት ሲኖርበት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡16
ሰው
እግዚአብሄር ወዳየለት የህይወት የክብር ደረጃ ሙሉ ለሙሉ የሚገባው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣው በእያንዳንዱ ቃል ነው፡፡
እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ
ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። የማቴዎስ ወንጌል 4፡4
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ፍሬያማነት
#ፍሬ #ማፍራት
#ስኬት #በእኔኑሩ
#ቃል #ህይወት
#ሙላት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ሰላም #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#መመዘኛ #መስፈርት
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment