Popular Posts

Thursday, November 7, 2019

የጥበብ የወርቅ አንኳር



በህይወት ያለን ጉልበት ለመከናወን በቂ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የሃይል ጉድለት የለብንም፡፡ ብዙ ጊዜ ያለብን ጉድለት ሃይላችንን በምን ላይ እናውለው የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ ምንም ሃያል ብንሆን ያለንን ሃይል በተሳሳተ ቦታ ላይ ካዋልነው ውጤት አናገኝም፡፡
ለመኖር ብዙ ነገር አያስፈልግም፡፡ ለመኖር የሚያስፈልገው ጥቂትና አንድ ነገር ነው፡፡ በብዙ ነገሮች መካከል ጥቂቱንና አንዱን ነገር ለመለየት ጥበብ ይጠይቃል፡፡
የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት። የሉቃስ ወንጌል 10፡42
ቅድሚያ የሚሰጠውንና የማይሰጠውን ነገር መለየት ጥበብ ነው
በህይወታችን ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ሰው ለጁሉም ነገር ቅድሚያ መስጠት አይችልም፡፡ ሰው በህይወት ዘመኑ ቅድሚያ በሚሰጣቸውና ቅድሚያ በማይሰጣቸው ነገሮች መለየት ካልቻለ ስኬታማ አይሆንም፡፡
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡33
ጥበብ የሚተኮርበት ላይ ማተኮር የማይተኮርበትን ማለፍ ነው
ሰው ውስን ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለሁሉም ነገር አይደለም፡፡ ሰው የተፈጠረው ለተለየ አላማ ብቻ ነው፡፡ ሰው ያለው ስጦታ ለህይወት አላማው ብቻ የሚበቃ ነው፡፡ ሰው በአንድ ጎዜ ብዙ ነገር ላይ ማተኮር አይችልም፡፡ ውጤት የሚመጣው በትኩረት ስራ ነው፡፡ ውጤት የሚመጣው በአንድ ነገር ላይ ብቻ በማተኮርና በትጋት በመስራት ነው፡፡ ሰው በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ላይ ሊያተኩር ከሞከረ ምንም ነገር ላይ ማተኮር አይችልም፡፡
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።ወደ ዕብራውያን 12፡1-2
ጥበብ በሚፈልገውና በሚያስፈልገው መካከል መለየት ጥበብ ነው
የሰው ፍላጎት አያልቅም፡፡ ሰው ፍላጎቱን ሁሉ ከተከተለ በህይወቱ ተቅበዝባዥ ይሆናል፡፡ ሰው ፍላጎቱን ሁሉ ከተከተለ ህይወቱን በከንቱ ያባክናል፡፡ ሰው በህይወት ዘመኑ በሚያስፈልገውና እንዲሁ በሚፈልገው ነገር መካከል መለየት ካልቻለ ውጤታማ አይሆንም፡፡
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6፡6-8
ጥበብ ዛሬ ብቻ እንዳለን መረዳት ነው
ጥበብ ያለፈውን ለመለወጥ ያለመሞከር ብልሃት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘመንንን ከፋፍሎ የሰራው ስራችን በዘመን መካከል እንዲከፋፈልና እንዲቀል አስቦ ነው፡፡ ሰው የነገውን ዛሬ አምጥቶ ለመስራት መሞከሩ የጥበበ ጉድለት ነው፡፡  ጥበብ የዛሬውን ሰርቶ ለነገ አለመጨነቅና የነገን ለነገ የመተው ብልጠት ነው፡፡
ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡34
ጥበብ የማይታየውን ማየት የሚየታየውን አለማየት ነው
ጥበብ የማይታየውን የእግዚአብሔን ፈቃድ ማየትና በዚያ ያል ማተኮር በአንይን የሚያታየውን ነገር ላየ አለማተኮት ነው፡ሸ ጥበ በአይን በማይታየው የእግዚአብሔ መንግስት ፈቃድ ላይ ማተኮር በአይን በሚታየው በሁኔታ ላይ አለማተኮት ነው፡፡ ጥበብ በእግዚአብሔር ቃል በተገለጠው በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ ማተኮር ከእግዚአብሔር ቃል በተቃራኒር በሚናገረው በሁኔታዎች ላይ አለማተኮት ነው፡፡ 
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
ጥበብ ጉልበትን በምን ላይ ማፍሰስ እንዳለብን መረዳት ነው
ጥበብ በጭንቀት ላይ የሚፈሰውን ጉልበት መልሶ በፀሎት ላይ ማፈስስ ነው፡፡ ጭንቀት እንድንጨነቅ ስንፈተን ያንን ለጭንቀት የምናውለውን ጉልበት በፀሎት ላይ ማዋል ውጤትን እንድናገኝ ያደርጋል፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6
ጥበብ ክፉ ነገርን በማሰቢያ ጉልበት ፋንታ የእግዚአብሔርሔርን ቃል የማስላሰል ብልሃት ነው
ጥበብ በእግዚአብሔር ቃል አእምሮን መሙላት ነው፡፡ ጥበብ አእምሮን በእግዚአብሔር ቃል ሳይሞሉ ክፉ ነገርን ላለማሰብ መታገል ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል በማሰላለስ ክፉ ሃሳብ ቦታን ማሳጣት ነው፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡5-7
ጥበብ የዘመናችን ቁጥር ጥቂት መሆኑን መረዳት ነው
ጥበብ ያለንን ጊዜ ባወቅና በጊዜያችን መጠቀምን ያስችላል፡፡ ሰው ለዘላለም በምድር ላይ ለዘላለም እንደሚኖር እያሰበ ከኖረ ይሳሳታል፡፡ በምድር ላይ የምንኖረው ኑሮ አጭር መሆኑንና ይህ አጭር የምድር ቆይታን እንዴት እንዳሳለፍነው እንደምንጠየቅ ማወቅ ጥበብ ነው፡፡
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ። መዝሙረ ዳዊት 39፡4
ጥበብ ማድረግ የምንችለውንና ማድረግ የማንችለውን መለየት ነው፡፡
ሰው ማድረግ የሚችለው ነገር አለ፡፡ ሰው ማድረግ የማይችለው ነገር አለ፡፡ ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰራው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሔር ለሰው የሚሰራው ነገር አለ፡፡ ማድረግ የምንችለውንና ማድረግ የማንችለውን መለየት ጥበብ ነው፡፡ ሰው ማድረግ የሚችለውን ነገር አድርጎ ማድረግ የማይችለውን ነገር ለማድረግ አለመሞከር ጥበብ ነው፡፡ ሰው ማድረግ ያለበትን ነገር አድርጎ ማድረግ ስለማይችለው ነገር በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ እነ ራሰን መስጠት ጥበብ ነው፡፡
ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22፡42
ጥበብ የሆነውንና ያልሆነውን ማወቅ ነው
የተፈጠርንበትን አላማ የተጠራንበትን ጥሪና የተሰጠንን ስጦታ ማወቅ ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን እንዲሁ ያልተፈጠርንበትን አላማ ያልተጠራንበትን ነገር ያለተሰጠንን ስጦታ ማወቅ ያሳርፋል፡፡ የሆነውን ነገር መረዳት ያልሆነውን ነገር እንድንረዳ እና የሆነውን ነገር እንድናደርገው ባለሆነው ነገር ውስጥ ባለመግባት ለሆኑት ሰዎች ስጦታው ላላቸው ሰዎች ስፍራን መልቀቅን ያስተምረናል፡፡  
ከሕዝቡም አንድ ሰው፦ መምህር ሆይ፥ ርስቱን ከእኔ ጋር እንዲካፈል ለወንድሜ ንገረው አለው። እርሱም፦ አንተ ሰው፥ ፈራጅና አካፋይ በላያችሁ አንድሆን ማን ሾመኝ? አለው። የሉቃስ ወንጌል 12፡13-14
ጥበብ መቼ እሺ እንደምንልና መቼ እንቢ እንደምንል ማወቅ ነው
ጥበብ እሺ ማለትን ብቻ ሳይሆን እንቢ ማለትን ይጠይቃል፡፡ ለሁሉም ነገር እሺ የምንልን ከሆንን ልካችንን አናውቅም ማለት ነው፡፡  
ጥበብ ሃጢያትን ላለማድረግ መታገል ሳይሆን ፅድቅን በማድረግ ጉልበትን ማፍሰስ ነው
ሰው ያለውን ጉልበት ሃጢያትን ለማድረግ በመታገል ላይ ቢያውለው ምንም አይጠቅመውም፡፡ ሰው ያለውን ጉልበት ፅድቅ በማድረግ ላይ ቢያፈሰው ሃጢያትን አለማድረግ ይችላል፡፡ ሰው ያለውን ጉልበት ሃጢያትን ላለማድረግ በመታገል ላይ ከማዋል ይልቅ ፅድቅ በማድረግ ላይ ቢያውለው ሃጢያትም አያደርግም ፅድቅንም ያደርጋል፡፡
ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 6፡13
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #ተግሳፅ #ዘለፋ #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment