Popular Posts

Tuesday, November 5, 2019

ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል



ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ሐጌ 2፡9
በህይወታችን ፈልገን ያጣናቸውን ነገሮች ስናይ እናዝናለን፡፡ በህይወታችን ጠብቀን ያላገኘነውን ነገር ስናስብ ልባችን ይወድቃል፡፡ በህይወታችን ይዘን ያጣነውንም ነገር ስናስብ እንደገና ደስታን አገኝ ይሆን ብለን እናስባለን፡፡
ምክንተያቱን ሲናገር ብሩ የእኔ ው ወርቁ የእኔ ነው፡፡ የመጀመሪያውን ክብር የሰጠሁት እኔ ነኝ የሁለተኛውን ክብር የምሰጠው እኔ ነኝ፡፡
 ብሩ የእኔ ነው፥ ወርቁም የእኔ ነው፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ትንቢተ ሐጌ 2፡8
ነገሮች ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ ነገሮች ይለወጣሉ የመልካምነት ምንጭ እግዚአብሄር ግን አይለወጥም፡፡
እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም። ትንቢተ ሚልክያስ 3፡6
እግዚአብሄር በራሱ በእግዚአብሄር በሰጭው ላይ እንጂ በስጦታው ላይ እንድንደገፍ አይደፈልግም፡፡
ሲጀመር እግዚአብሄር ለከፍታ እንጂ ለውድቀት አልጠራንም፡፡ የእኛ ከፍታ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡
የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡18
እግዚአብሄር ለተሻለ እንጂ ላነሰ ነገር አልጠራንም፡፡
ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም። ኦሪት ዘዳግም 28፡13-14
ነገር ግን ካነሰው ተራራ ላይ ካልወረድክ ታላቁ ተራራ ላይ መውጣት አትችልም፡፡ ከታናሹ ተራራ ወደ ታላቁ ተራራ ለመዝለል መሞከር የእግዚአብሄርን አሰራር አለመረዳት ነው፡፡
ያጣነው ነገር ካለ ለተሻለው ቦታ ሊለቅ እንጂ ልንከስር አይደለም፡፡ የለቀቅነው የተሻለ ነገር ልንይዝ እየተዘጋጀን እንጂ ባዶ እጃችንን ልንቀር አይደለም፡፡ የኋላችንን የምንረሳው ለሚመጣው ለወደፊቱ ከፍ ላለው ስፍራ እንዲለቅ እንጂ ልናንስ አይደለም፡፡ የተውነው ይበልጥ ልንበለፅግ እንጂ ልናነሰ አይደለም፡፡  
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡13
እግዚአብሄር የተሻለውን እንደሚከፍት ሁሉ ያነሰውን እንደሚዘጋ መረዳት አለብን፡፡  
በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል። የዮሐንስ ራእይ 3፡7
የተዘጋ በር ካለ የተሻለው ሊከፈት እንጂ ተዘግቶ ሊቀር አይደለም፡፡
ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ የዮሐንስ ራእይ 3፡8
እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡18
ባጣው ነገር የሚያዝንና የሚፀጸፀት ሰው የኋለኛውን ክብር ያልተረዳ ሰው ነው፡፡
ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ሐጌ 2፡9
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ጻድቃን #የታመነ #ፊተኛ #ሁለተኛ #ኋለኛ #ክብር #ይበልጣል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ጥቂትበጥቂት #ሙሉቀን #እየተጨመረ #በረከት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment