አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚታየውን ነገር ሁሉ ከማይታይ አለም የፈጠረ ታላቅ አምላክ
ነው፡፡
እግዚአብሔር ለታላቅነቱ ፍፃሜ የለውም፡፡
እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም። መዝሙረ ዳዊት 145፡3
እግዚአብሔር የፈጠረን በግኡዙ አለም ስለሆነ እኛ
የእግዚአብሔርን ነገር የምንረዳው በእምነት ብቻ ነው፡፡ እኛ የእግዚአብሔርን ስራ የምናውቀው በእምነት ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ይችላል ያደርጋል ብለን በቃሉ ካመንነው
እግዚአብሔር ማድረግ የማይችለው ነገር የለም፡፡
እርሱ ግን፦ በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል አለ። የሉቃስ ወንጌል
18፡27
እግዚአብሔር ሁሉንም ማድረግ ይችላል፡፡ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ሊከለክል የሚችል
ማንም የለም፡፡
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል
አወቅሁ። መጽሐፈ ኢዮብ 42፡1
ለሰው የማይቻለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቻላል፡፡ ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር
ይቻላል፡፡
እግዚአብሔር በምንም አይወሰንም፡፡
ለሰው የሚከብደው ለእግዚአብሔር አይከብደውም፡፡
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን
ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ። ይህም በእግዚአብሔር ዓይን ቀላል ነገር ነው፤ መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
3:17-18
እግዚአብሔር የማይቻልን ነገር በማድረግ የታወቀ ነው፡፡ እግዚአብሔ የማይቻልን ነግር
በማድረግ የተፈራ ነው፡፡ በምስጋና የተፈራ
አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም
የምታደርግ፥ በቅድስና የከበረ እንዳንተ ያለ ማን ነው? ኦሪት ዘጸአት 15፡11
እግዚአብሔር ለሰው የማይቻል ነገር በማድረግ ክብሩን መውሰድ ይፈልጋል፡፡
ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ
መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። የዮሐንስ ወንጌል 2፡11
እግዚአብሔርን በሚወስት ሰዎች አይደሰትም፡፡ የእስራኤል ህዝብእግዚአብሔር ብዙ ነገር
አድርጎላቸው ከግብፅ ከባርነት ነፃ አውጥቶዋቸው እሺ ይሁን አሁን ግን በምድረበዳ ስጋን ሊሰጠን ይችላል? ብለው እግዚአብሔርን አሙት
እግዚአብሔርን ወሰኑት፡፡
ተመለሱ፥ እግዚአብሔርንም ፈተኑት፥ የእስራኤልንም ቅዱስ አሳዘኑት። እነርሱም እጁን
አላሰቡም፥ ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን ቀን፥ በግብጽ ያደረገውን ተኣምራቱን፥ በጣኔዎስም በረሃ ያደረገውን ድንቁን። መዝሙረ ዳዊት
78፡41-43
የእግዚአብሔር አሰራር ሙሉ በሙሉ ባይገባንም እንኳን
እግዚአብሔር አይችልም ማለት የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ይችላል፡፡
የማይቻለውን እንዴት እንደሚችል ስለ እግዚአብሔር
ችሎታ እርግጠኛ ላልሆኑ ሰዎች የእግዚአብሔር አምላካዊ መልስ ይህ ነው፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ትንቢተ ኢሳይያስ 40፡28
እግዚአብሔር
ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን በእምነት እንጠብቀው፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #የማይቻል #ይቻላል #ለእግዚአብሔርቀላልነው ##መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment