በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡22
አካባቢያችንን
ስናይና የክፋትን መብዛት ስንመለከት ተስፋ ለመቁረጥ እንፈተናለን፡፡
ነገር
ግን ትክክለኛው ነገር እንዳለ ሁሉ ማስመሰያው ነገር እንዳለ መዘንጋት የለብንም፡፡ ማስመሰያው የመኖሩ ምልክቱ ትክክለኛው ነገር
እንዳለ ነው፡፡ ንፁህ ባልሆነ ልብ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠሩ እንዳሉ ሁሉ በንፁህ ልብ የእግዚአብሄር ስም የሚጠሩ ሰዎች ደግሞ
አሉ፡፡
ሰይጣን
ሊያሳምነን የሚፈልገው በንጹህ ልብ የእግዚአብሄርን ስም የሚጠሩ ሰዎች እንደሌሉና ሁሉም ስው እንደተባለሸ ንፁህ እንዳልሆነ ነው፡፡
ይህ ግን የሰይጣን ማታለል ነው፡፡ በዚህ ዘመን በንፁህ ልብ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሰው የለም የሚለው አባባል እኛን ከንፁህ
ልብ ሊያወጣን የሚመጣ የሰይጣን ውሸት ነው፡፡
እኛ
ብቻ ብቻችንን እንደቀረን የሚሰማን ስሜት በሁሉም እግዚአብሔርን በንፁህ ልብ በሚከተል ላይ የሚመጣ ፈተና ነው፡፡
እርሱም፦
ለሠራዊት አምላክ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም
በሰይፍ ገድለዋልና እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ አለ። መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 19፡10
እኔ
ብቻ ቀረሁ ላለው ለኤልያስ የእግዚአብሄር አምላካዊ መልስ አንተ ብቻ አይደለህም ለጣኦት ያልሰገዱ ብዙዎች አሉኝ የሚል ነው፡፡ እግዚአብሄር
በየዘመናቱ ቅሬታ አሉት፡፡
እኔም
ከእስራኤል ጕልበታቸውን ለበኣል ያላንበረከኩትን ሁሉ፥ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ። መጽሐፈ
ነገሥት ቀዳማዊ 19፡18
የክርስቶስን
ሳይሆን የራሳቸውን የሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በቅንነት ስለ እግዚአብሄር መንግስት ስለቤተክርስትያን ስለእግዚአብሄር ህዝብ የሚጨነቁ ሰዎች አሉ፡፡
እንደ
እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤ ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም። ወደ
ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡20-21
በንጹሕም
ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡22
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት
#የማይቻል #ይቻላል
#ለእግዚአብሔርቀላልነው #ቅንነት #ንፁህልብ #ጽድቅን #ፍቅርን #እምነትን #ንጹህ #አማርኛ #ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ቃል
#ማሰላሰል #ማድረግ
#ሁሉይቻላል #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment