Popular Posts

Saturday, November 23, 2019

ሞትም ጥቅም ነውና



ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡21-24
በምድር ያለንው ተልከን ነው፡፡ በምድር ያለንው እግዚአብሄር በምድር ላይ የሰጠንን ወንጌልን የመስበክ ስራን ለመፈፀም ብቻ ነው፡፡ በምድር ያለነው ስራችንን እስክንጨርስ ብቻ ነው፡፡  
እግዚአብሄር እኛን በምድር ላይ ያስቀመጠበት አላማ ሲያልቅ በምድር ላይ አንድ ሰከንድ መቆየት አንፈልግም፡፡
በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡6-7
በምድር ያለነው ከዚህ የተሻለ ቦታ ስለሌለ አይደለም፡፡ ክርስቶስን የምንከተል ሁላችን የምድርን ውጣ ውረድ ስናስብ መሄድን ከክርስቶስ ጋር መሆንን እንመርጣለን ለእኛ እጅግ የሚሻል ነውና፡፡ ከርስቶስን ስንቀበል በትንሳኤ ከሞት ስለተነሳን እና ለዘላለም ከእግዚአብሄ ጋር ስለምንኖር ሞት ለእኛ ወደጌታ መሄጃ በር ነው፡፡  
ለእኛ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ወደፊት ለራሳችን ስለማንኖር ለእኛ የሚሻል ስለሆነ ብቻ አንፈልገውም፡፡ የምንፈልገው የእግዚአብሄርን አላማ ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ስላለበት ከምቾት ይልቅ የምንፈልገው ተግዳሮቱን ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ስላለበት ከእረፍቱ ይልቅ የምንፈልገው ተጋድሎውን ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ስላበት የምንፈለግው ቶሎ መሄዱን ሳይሆን ጠብቀን ሃላፊነታችንን ተወጥተን በመጨረሻ አክሊላችንን መቀበል ነው፡፡
 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡21-24
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

No comments:

Post a Comment