Popular Posts

Monday, November 4, 2019

የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አስረዝሚ



ብዙ ጊዜ በህይወታችን ከደረሰብን ውጣ ውረድ አንፃር ራሳችንን መወሰን ይቀለናል፡፡ ፍፁም ባይሆንም ባለንበት የምቾት ቀጠና መኖርና መሞት እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሄር የተሻለ ነገር እንዳለው ልባችን እያወቀው ነገር ግን ጥሩ ላለመዘርጋትና ላለመውረስ ምክኒያት ያገኘን መስሎን እንታለላለን፡፡
እግዚአብሄር ግን ራሳችንን የወሰንነበትን ውስንነት በየጊዜው እንድንጥስ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ራሳችንን ከመጠንንበት መጠን አልፈን እግዚአብሄር ወደአየልን እንድንሻገር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች ከወሰኑልን ገደብ ጥሰን እንድንወጣ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ግን ሁኔታው ከወሰነን ወሰን አልፈን እንድሄድ ይፈልጋል፡፡ ከእርሱ ቃል ውጭ ምንም አይነት ገደብ በህይወታችን እንዲኖር እግዚአብሄር አይፈልግልም፡፡ የእኛ ገደብ እግዚአብሄር የተናገረው ቃል ብቻ እንዲሆን እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና። ትንቢተ ኢሳይያስ 54፡2-3
በመጀመሪያ ደረጃ ለእግዚአብሄር ሁሉ ቻይነት እውቅና እንድንሰጥ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር እንድናመሰግነው  ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ ደስ እንድንሰኝ ይፈልጋል፡፡  
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስ 54፡1
ውስንነት የሚመጣው እምነት እስኪመጣ ድረስ ብቻ ነው፡፡ እምነት ከመጣ ውስንነት ቦታውን ይለቃል፡፡ እግዚአብሄር የማይቻለውን እንደሚያደርግ ልናምን ይገባል፡፡ የሚያምንመ በምንም አይወሰንም፡፡ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል፡፡
የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡4-5
ለእግዚአብሄር ሁሉ ይቻለዋል፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ሊሰራ ሲፈልግ እግዚአብሄርን አንወስነው፡፡
እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2፡7-8
ከቃሉ እግዚአብሄር እንደሚያይ እያየን ውስንነታችንን አስወግደን ከእግዚአብሄር ጋር ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት እንነሳ፡፡
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና። ትንቢተ ኢሳይያስ 542-3
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #አስፊ #ይዘርጉ #አትቆጥቢ #አስረዝሚ #አፅኚ #ትሰፋፊያለሽ #ይወርሳል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ማየት #መርገጥ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መቃተት #መንበርከክ #መጠበቅ #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment