Popular Posts

Friday, November 1, 2019

አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው?



አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው። መዝሙረ ዳዊት 39፡7
ሰው ከአልጋው የሚነሳው በተስፋ ነው፡፡ ሰው ለመኖር ለመውጣት ለመግባት የሚወስነው በተስፋ ነው፡፡ ሰው እንደገና ለመኖር የማይፈራው በተስፋ ነው፡፡
ሰው በእግዚአብሄር ለልዩ አላማ ተፈጥሮአል፡፡ ሰው ለዚያ ለተፈጠረለት አላማ ለመኖር ተስፋ ያደርጋል፡፡ ሰው በውስጡ ያለውን አላማ ለማሳካት ተስፋ ያደርጋል፡፡ ሰው መድረስ የሚፈልግበት ለመድረስ ተስፋ ያደርጋል፡፡
መኖር የተስፋ ማስፈፀሚያ መንገድ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም፡፡ ሰው ተስፋ ከሌለው ለመኖር ምንም ምክኒያት አይኖረውም፡፡ ሰው ተስፋ ካላደረገ የመኖር ምክኒያትን ያጣዋል፡፡
ሰው በሚያልፍበት መንገድ ሁሉ እርምጃን እንዳያቆም የሚጠብቀው እግዚአብሄርን ተስፋ ማድረጉ ነው፡፡ ሰው በከፍታና በዝቅታ እጁን እንዳይሰጥ የሚጠብቀው እግዚአብሄርን ተስፋ ማድረጉ ነው፡፡ ሰው መከራን የሚታገሰው በተስፋ ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡3-4
በምድር ላይ ሰዎች ተስፋ የሚያደርጉዋቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እንደ እግዚአብሄር አስተማማኝ ተስፋ የለም፡፡ ሰዎች ውስን ስለሆኑ ብዙ የማያውቁትና ብዙ ማድረግ የማይችሉት ነገር ስላለን ለሌላው ሰው የሚሰጡት ተስፋ አስተማማኝ ተስፋ አይደለም፡፡
እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ ስለሆነ የሚሰጠው ተስፋ አስተማማኝ ተስፋ ነው፡፡  
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11
እግዚአብሄር በእርሱ ላይ ብቻ እንጂ በሰዎች ላይ ተስፋ እንድናደርግ አይፈልግም፡፡
እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል? ትንቢተ ኢሳይያስ 2፡22
እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው! ትንቢተ ኢሳይያስ 2፡22 /አዲሱ መደበኛው ትርጉም/
ይልቁንስ ልአያንዳንዱ ጥያቄ መልስ ያለው ለእያንዳንዱ ችግር መውጫ መንገድ ያለው እግዚአብሄር እርሱን ብቻ ተስፋ በሚያደርጉት ይደሰታል፡፡
እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል። መዝሙረ ዳዊት 147፡11
ከእግዚአብሄር ውጭ ተስፋ ያደረግናቸው ነገሮች ይዘግይም ይፍጠንም ያሳፍሩናል፡፡
ዘመን ሲያልፍ ዘመን ሲተካ ተስፋችን በእኛ ላይ አላማው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2፡4
ነገሮች ሲለዋወጡ የማይለወጥ እግዚአብሄን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም። ትንቢተ ሚልክያስ 3፡6
ነገሮች ሲከፉ በየትኛወም አቅጣጫ ብታዩት ብታገላብጡት መልካም እንጂ ሌላ ሊሆን በማይችለው መልካምነቱ በማይለወጥው በእግዚአብሄር ላይ ብቻ ተስፋ እናርጋለን፡፡
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። የያዕቆብ መልእክት 1፡17
እግዚአብሄርን ብቻ ተስፋ እናደርጋለን እግዚአብሄርን ብቻ እንጠብቃለን፡፡ ከእግዚአብሄር ውጭ በምንም ነገር ላይ ተስፋ ባለማድረግ እግዚአብሄርን ብቻ በትግስት እንጠብቃለን፡፡  
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው። መዝሙረ ዳዊት 39፡7
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ  Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #መከራ #ፈተና #ሞት #በሁሉ #እንገፋለን #አንጨነቅም #እናመነታለን #ተስፋአንቆርጥም #እንሰደዳለን #አንጣልም #እንወድቃለን #አንጠፋም #ህይወት #ስጋ #መፅናት #መታገስ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment