አንተ
ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡6
ከሚያስፈነቅዱኝ
የእግዚአብሄር የተስፋ ቃሎእች አንዱ ይህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል የሚለው ቃል
ነው፡፡
ወደ እግዚአብሄር መፀለይ እግዚአብሄር ትልቅ ስራን
እንደሰራንለት ያህል ዋጋን እንዲከፍለን ያደርገዋል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር
የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6
በሁኔታዎች
ውስጥ መፅናት ትልቅ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄርን ስንፈልግ እግዚአብሄር በፅናት ዋጋን ይከፍለናል፡፡
እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። መዝሙረ ዳዊት 105፡3-4
እግዚአብሄርን መፈለግ ብቻ እግዚአብሄር ዋጋ እንዲከፈለን
ያስደርጋል፡፡
እግዚአብሄር መጠየቅ መለመንን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር
ለሚጠይቁት ለሚለምኑት መስጠት ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር የሚጠይቁትን የሚለምኑትን መልስ በመስጠት ደስ ይለዋል፡፡
እግዚአብሄር የሚለምኑትንና የሚጠይቁትን ከባለጠግነቱ
በማካፈል ይደሰታል፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡12
እግዚአብሄርን ያየው ማንም የለም በእቅፉ ያለው
አንድ ልጁ ተረከው እንደሚል እግዚአብሄርን በትክክል ልቡን የሚተርክልን ኢየሱስ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ልብ የምናየው በኢየሱስ ትምህርት
ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለልጆቹ ያለውን ልብ የምንረዳው በኢየሱስ እካሄድና ትምህርት ነው፡፡
ኢየሱስ ከተራራው ስብከት ጀምሮ እስከ መጨረሻው
ሰአት ድረስ ደቀመዛሙርቱ ወደደእርሱ ለሚፀልዩት ሰዎች ሁሉ ወደሚከፍለው እንዲፀልዩ በትጋት ያስተምር ነው፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥
የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-8
ሰው
የሚፀልየው ፀሎት ይታያል፡፡ ሰው በእልፍኙ የሚተጋው ትጋት ይታያል፡፡
ፀሎት
አይደበቅም አይሰወርም፡፡ ፀሎት በክፍያ ይታያል ይገለጣል፡፡
የማይገለጥ
የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። የሉቃስ ወንጌል 8፡17
በእልፍኙ
እግዚአብሄርን የሚፈልግና ወደ እግዚአብሄር የሚፀልይን ሰው እግዚአብሄር በግልፅ ይከፍለዋል፡፡
ነገር
ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም
ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። የሉቃስ ወንጌል 12፡2-3
እግዚአብሄር
ፀሎትን የሚከፍለው እንዳይሰወር በወዳጅም በጠላትም ፊት ለፊት በግልፅ ነው፡፡
በፊቴ
ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። መዝሙረ ዳዊት 23፡5
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም
ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡6
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር
#ለምኑ #ፈልጉ
#አንኳኩ #ይቀበላል
#ያገኛል #ይከፈትለታል
#በግልፅ #ይከፍልሃል #ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#የእግዚአብሄርቃል #የእግዚአብሔርፈቃድ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment