ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ
በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡25፣31-33
አገልግሎት
ከስጦታ አይጀምርም፡፡ ምንም ያህል መንፈሳዊ ስጦታ ቢኖርህ ስለመሰረታዊ ፍላጎትህ እግዚአብሄርን እስካላመንከው ድረስ አገልግሎት
አልጀመርክም፡፡ እግዚአብሄርን ስለምግብህ ስለልብስህ ስለቤት ኪራይህ ስለልጆችህ ትምህርት ቤት ክፍያ ስለመሳሰሉት እግዚአብሄርን
ሌሎች ብዙ ነገሮችን ማድረግ ትችላለህ ነገር ግን እግዚአብሄርን ማገልግል አትችልም፡፡
ሌላውን
የምታገለግለው የእግዚአብሄር ቃል በህይወትህ ፍሬ ባፈራ መጠን ብቻ ነው፡፡ ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ካላመንከው በስተቀር
የእግዚአብሄር ቃል እንደሚገባው በህይወትህ ፍሬ አያፈራም፡፡ ስለኑሮ
የምትጨነቅ ከሆንክ የእግዚአብሄር ቃል በህይወትህ ሙሉ ፍሬ አያፈራም፡፡ አገልግሎት ከህይወት ይመነጫል፡፡ ፍሬ ባላፈራህበት የህይወትህ
ዘርፍ ማገልገል አትችልም፡፡
በእሾህ
መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም
አያፈሩም። የሉቃስ ወንጌል 8፡14
አገልግሎት
የሚመነጨው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ አገልግሎት የሚመነጨው በእግዚአብሄር ከመገልገል ነው፡፡ አገልግሎት የሚመነጨው በእግዚአብሄር በመሰረታዊ
ፍላጎት ከመገልገል ነው፡፡ እግዚአብሄር አንተን እንደሚያገለግልህ ሳታምንና እርግጠኛ ሳትሆን አገልግሎት አትጀምር፡፡ በእግዚአብሄር
ሳይገለገሉ ማገልገል ውሸት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ሳያምኑ ማገልገል የሃይማኖት መልክ እንጂ እውነተኛ አገልግሎት አይደለም፡፡
አገልግሎት
ከመጀመርህ በፊት ወደ እግዚአብሄር ቅረብ፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ከእግዚአብሄር ጋር ያለህን ግንኙነት ፈትሽ፡፡ አገልግሎት
ከመጀመርህ በፊት እግዚአብሄርን ስለመሰረታዊ ፍላጎትህ ማመንህን እርግጠኛ ሁን፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ስለመሰረታዊ ፍላጎት
እግዚአብሄርን ማመን ተማር፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ በፊት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ማመን ተለማመድ፡፡ አገልግሎት ከመጀመርህ
በፊት ስለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን እንደ አባት ፣ እንደ አቅራቢና እንደ ምንጭ እወቀው፡፡
አባታችሁ
አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ
አትጠሩ። የማቴዎስ ወንጌል 23፡9-10
እግዚአብሄርን
እንደ አባት ካላወቅከው በስተቀር ሌላውን ሰው አባት ታደርግና ከማገልገል ይልቅ በእግዚአብሄር ሳይሆን በሌላው ሰው በመገልገል ህይወትህን ታባክናለህ፡፡ እግዚአብሄርን እንደ መሰረታዊ ፍላጎትህ
ምንጭ ካላወቅከው ሌሎችን የምታገለግላቸውን ሰዎች እንደ ምንጭ ትይዝና ህይወትህ በእረፍት ሳይሆን በረብሻ ይሞላል፡፡ እግዚአብሄርን
እንደ አቅራቢ ካላወቅከው ሌላውን አቅራቢ ታደርግና ከማገልገል ይልቅ በምስኪንነት አስተሳሰብ ከሌላው ሰው ጠባቂ ሆነህ ሳታገለግል
ህይወትህን ትፈጃለህ፡፡
ስለመሰረታዊ
ፍላጎትህ እግዚአብሄርን ማመን ከአገልግሎት ይቀድማል፡፡ እግዚአብሄር እንደሚንከባከብህ ሳትረዳ ከአንተ አልፈህ ሰውን በእውነት መንከባከብ
አትችልም፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
ለተጨማሪ
ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #መሰረታዊፍላጎት #ጭንቀት #አገልጋይ #እረፍት #ድካም #ጥረት #ባለጠግነት #በረከት #አላማ #ልፋት #ትህትና #መልካምነት #መከባበር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #አገልግሎት #ፉክክር #ዋጋ
No comments:
Post a Comment