Popular Posts

Tuesday, September 10, 2019

ባሪያህ ይሰማልና ተናገር የማለት 10 ምክኒያቶች



እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 310
1)     እግዚአብሄርን ካልሰማን እግዚአብሄር በህይወታችን እየሰራ ያለውን ነገር አናውቅም ልንተባበረውም አብረነው ልንሰራም ልናገለግለውም አንችልም፡፡
ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። የዮሐንስ ወንጌል 5፡17
2)      እግዚአብሄርን ካልሰማን እንስታለን
እግዚአብሄር ምሪት ካልሆነ የእግዚአብሄርን ሃሳብ የምናውቅበት ሌላ ምንም መንገድ የለም፡፡ ክፉና ደጉን ለመለየት በራሳችን ማስተዋል ለመደገፍ ብቁ አይደለንም፡፡ መንገዳችን የሚቀናው ለእርሱ ምሪት እውቅና ሰጥተን ድምፁን ስንሰማ ብቻ ነው፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5-7
3)      እግዚአብሄርን መስማት ከምንም ድንቅ መስዋእት ይበልጣል፡፡
ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።
4)      እግዚአብሄርን ካልሰማን ውጤታማ አንሆንም፡፡ የተፈጠርነው እግዚአብሄርን በመስማት እና በመታዘዝ ውጤታማ እንድንሆን ዲዛይን ተደርገን ነው፡፡ እግዚአብሄርን አለመስማት ከተፈጠርንበት ዲዛይን ውጭ በመኖር ፍሬ የማፍራት ከንቱ ሙከራ ነው፡፡  
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7-8
5)      እግዚአብሄርን ካልሰማን የእስራኤል ህዝብ የሴይርን ተራራ 40 አመት እንደዞረ እንዞራለን እንጂ ህይወታችን አይለወጥም፡፡
ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። ወደ ዕብራውያን 3፡8-9
6)      እግዚአብሄርን ካልሰማን ልናስደስተው አንችልም፡፡  

እግዚአብሄርን የምናስደስተው በራሳችን መንገድ አይደለም በእርሱ በራሱ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናስደስተው ራሳችን የምንፈልገውን በማድር አይደለም እርሱ የሚፈልገውን በማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የምናስደስተው በራሳችን ህግ አይደለም በእርሱ ህግ ነው፡፡ እርሱ ንጉስ ነው፡፡ እርሱ ህግ አውጪ ነው፡፡ እርሱ እውነተኛ ነው፡፡ እርሱ ትክክል ነው፡፡ እርሱን መስማት እንድናስደስተው ያስችለናል፡፡ እርሱን አለመስማት ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነታችንን ያበላሻል፡፡

ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 116

7)      እግዚአብሄርን አለመስማትና በእግዚአብሄር ላይ ማመፅ ጣኦትን እንደማምለክ ነው
ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15:23
8)      እግዚአብሄርን ካልሰማን አናርፍም
የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። መጽሐፈ ምሳሌ 1፡33
9)      እግዚአብሄርን ካልሰማን የህይወት አላማችንን እንስታለን፡፡

በምድር ላይ ያለነው ለልዩ አላማ ነው፡፡ ያንን አላማ በህይወታችን የሚሰራውን እግዚአብሄርን ለመስማት ጊዜ ካልሰጠንና ካልታዘዝነው አላማ ቢስ ሆንን ህይወታችንን እናባክናለን፡፡

10)   ጠላት ዲያቢሎስ እያለ የበላይ ሆነን በድል የምናሸንፈው እግዚአብሄርን ለመስማት እና ለመታዘዝ ስንቀርብ ብቻ ነው፡፡

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡16-17
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ምሪት #ጆሮ #ትህትና #ቃል #ድምፅ #አእምሮ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #መታዝዝ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment