Popular Posts

Wednesday, September 11, 2019

የስኬት ጣሪያ መለኪያ



እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡10-11
እግዚአብሄር የፈጠረን በመልኩ እና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር እርሱን እንድንመስል ሳይሰስት ፈጥሮናል፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26-27
የእግዚአብሄር አላማ ራሱን በሰው ልጆች ውስጥ ማብዛት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ባህሪውን በሰው ልጆች ውስጥ ማየት ነው፡፡ የሰው ልጅ የህይወት አላማ እርሱን መምሰል ስለሆነ እግዚአብሄር እርሱን እንድንመስል የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ሳይሰስት ሰጥቶናል፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2 የጴጥሮስ መልእክት 1፡2-3
የእግዚአብሄር አላማ መልኩን በእኛ ውስጥ ራሱን ማየት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አለካማ ባህሪው በእኛ ውስጥ ሲበዛ ማየት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ የመልካምነቱ ሁሉ ባህሪ በእኛ ውስጥ ሲበዛና ሲሰፋ ማየት ነው፡፡
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡1
ሃዋሪያው ጳውሎስ በሞቱ እንኳንም እርሱን መምሰል ይመኝ ነበር፡፡
የክርስትና ስኬት የሚለካው ምን ያህል ክርስቶስን መስለሃል መልክህ ወደ ክርስቶስ ተጠግቷል በሚል ነው፡፡
ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡15
በክርስትናቸው ስላለተሳካላቸው ሰዎች መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር እንዳላደጉና ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ እንዳልተጠጉ ይናገራል፡፡
እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 219
የአለምና የእግዚአብሄር የስኬት መልኪያ ይለያያል፡፡ በህይወታችን በኑሮዋችን በአነጋገራችን በአካሄዳችን በአስተሳሰባችን ክርስቶስን መምሰል የስኬታችን መለኪያ ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuam Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ስኬት #ወንጌል #ፍቅር #በክርስቶስ #የጌታፈቃድ #የጌታአላማ #ባለጠጋ #ጠቢባን #ሃያላን #ሞገስ #ክንውን #በረከት #ቃል #ፀሎት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment