Popular Posts

Follow by Email

Friday, November 16, 2018

የኢዮብ የታላቅነት ሚስጥር


መፅሃፍ ቅዱስ ስለ ኢዮብ ሲናገር ፍፁም ቅን እግዚአብሄርን የሚፈራ ከክፋትም የራቀ ሰው ነበር በማለት ስለኢዮብ ይመሰክራል፡፡ ኢዮብ በምስራቅ ካሉ ሰዎች ይልቅ ታላቅ የነበረበትን ምክኒያት በእግዚአብሄር ፊት የኖረውን ኑሮ በጥቂቱ እንመለክት፡፡  
ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ። መጽሐፈ ኢዮብ 1፡1፣3
መጽሐፈ ኢዮብ 29፡11-17
·         ኢዮብን ያወቁ ሰዎች ሁሉ ስለደግነቱ ይመሰክሩ ነበር፡፡
ቁጥር 11 የሰማችኝ ጆሮ አሞገሰችኝ፥ ያየችኝም ዓይን መሰከረችልኝ፤
·         ችግረኛንና ደሃ አደጉን ይረዳ ነበር፡፡
·         ቁጥር 12 የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረጂ የሌለውን አድኜ ነበርሁና።
·         የሰዎችን ችግር በመፍታት ደስ የሚያሰኛቸው ሰው ነበር፡፡
ቁጥር 13 ለጥፋት የቀረበው በረከት በላዬ መጣ፤ የባልቴቲቱንም ልብ እልል አሰኘሁ።
·         ትክክለኛን ፍርድ በመፍረድ እለት በእለት ለእውነት የሚቆም በእውነተኝነቱ የሚታወቅ ሰው ነበር
ቁጥር 14 ጽድቅን ለበስሁ እርስዋም ለበሰችኝ፤ ፍርዴም እንደ መጐናጸፊያና እንደ ኵፋር ነበረ።
ቁጥር 15 ለዕውር ዓይን፥ ለአንካሳ እግር ነበርሁ።
·         በእውቅና በአድልዎ ሳይሆን በእውነት የሚፈርድ ሰው ነበር
ቁጥር 16 ለድሀው አባት ነበርሁ፤ የማላውቀውንም ሰው ሙግት መረመርሁ።
·         በፍርሃት የማያመቻምች ክፉን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ ሰው ነበር፡፡
ቁጥር 17 የኃጢአተኛውን መንጋጋ ሰበርሁ፥ የነጠቀውንም ከጥርሱ ውስጥ አስጣልሁ።

መጽሐፈ ኢዮብ 29፡5-34

·         ህይወቱን ከሃሰት ይጠብቅ ነበር
ቁጥር 5-6 በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ይወቅ። በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኵላ እንደ ሆነ፥
·         ነውርን ይንቅ ነበር
ቁጥር 7 እርምጃዬ ከመንገድ ፈቀቅ ብሎ፥ ልቤም ዓይኔን ተከትሎ፥ ነውርም ከእጄ ጋር ተጣብቆ እንደ ሆነ፥
·         ህይወቱን ከመጆምጀት በትጋት ይጠብቅ ነበር
ቁጥር 9 ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደ ሆነ፥ በባልንጀራዬም ደጅ አድብቼ እንደ ሆነ፥
·         ለሰዎች ሁሉ ታላቅ አክብሮት ነበረው
ቁጥር 13 ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን ንቄ እንደ ሆነ፥
·         ድሃን መርዳት ሃላፊነት እንደራሱ ሃላፊነት ይወስድ ነበር
ቁጥር 16 ድሀውን ከልመናው ከልክዬ፥ የመበለቲቱን ዓይን አጨልሜ እንደ ሆነ፥
·         ስለደሃ አለመብላት ሃላፊነት ይወሰድ ነበር
ቁጥር 17 እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥ ድሀ አደጉም ደግሞ ከእርሱ ሳይበላ ቀርቶ እንደ ሆነ፤
·         ለብዙዎች ላልወለዳቸው ልጆች አባት ነበር
ቁጥር 18 እርሱን ግን ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥
·         እርስዋንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፤
·         በታላቅ የህይወት ደረጃ ይመላለስ ነበር
ቁጥር 19 ራቁቱን የሆነው ሰው ሲጠፋ፥ ወይም ድሀ ያለ ልብስ ሲሆን አይቼ እንደ ሆነ፥
ቁጥር 20 ጐንና ጐኑ ያልባረከችኝ፥ በበጎቼም ጠጕር ያልሞቀ እንደ ሆነ፤
·         ያለውን ተሰሚነት ተጠቅሞ የሚረዳው የሌለውን ሰው አይጨቁንም
ቁጥር 21 በበሩ ረዳት ስላየሁ፥ በድሀ አደጉ ላይ እጄን አንሥቼ እንደ ሆነ፥
·         በእግዚአብሄር እንጂ በወርቅና በር ተስፋ አያደርግም አይመካም ነበር  
ቁጥር 24 ወርቅን ተስፋ አድርጌ፥ ጥሩውንም ወርቅ፦ በአንተ እታመናለሁ ብዬ እንደ ሆነ፤
·         በእግዚአብሄር እንጂ ሃብቱ ደስ ላለመሰኘት ይጠነቀቅ ነበር
ቁጥር 25 ሀብቴ ስለ በዛ፥ እጄም ብዙ ስላገኘች ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፤
·         ከእግዚአብሄር ውጭ ምንም ነገርን ላለማድነቅና ላለማምለክ ይጠነቀቅ እንደክህደት የቆጥረው ነበር  
ቁጥር 26 ፀሐይ ሲበራ ጨረቃ በክብር ስትሄድ አይቼ፥
ቁጥር 27 ልቤ በስውር ተታልሎ፥ አፌም እጄን ስሞ እንደ ሆነ፤
·         በሚጠላው ሰው ውድቀት ላለመደሰት ራሰነ ይገዛ ነበር
ቁጥር 29 በሚጠላኝ መጥፋት ደስ ብሎኝ ክፉ ነገርም ባገኘው ጊዜ ሐሤት አድርጌ እንደ ሆነ፤
·         ጠላቱን ላለመርገም ይጠነቀቅ ነበር
ቁጥር 30 ነገር ግን በመርገም ነፍሱን በመሻት አንደበቴን ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አልሰጠሁም፤
·         ያለው ነገር ለሌሎች እንደተሰጠው ያምን ነበር
ቁጥር 32 መጻተኛው ግን በሜዳ አያድርም ነበር፥ ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፤
·         ሃጢያቱን ከመሸሸግ ይልቅ ለመናዘዝና ለመተው ፈጣን ነበር
ቁጥር 33 በደሌንም በብብቴ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰው ሰውሬ እንደ ሆነ፤
·         እውነትን ከመናገር የሰው ብዛት እንዳያስፈራው እና ከፍርድ እንዳያስተው ይጠነቀቅ ነበር
ቁጥር 34 ከሕዝብ ብዛት ፈርቼ፥ የዘመዶቼም ንቀት አስደንግጦኝ፥ ዝም ብዬ ከደጅ ያልወጣሁ እንደ ሆነ፤

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ደስታ #ኢዮብ #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment