Popular Posts

Wednesday, December 18, 2019

ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ



እግዚአብሔርም እንዳለኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን። እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ። ኦሪት ዘዳግም 21-3
እግዚአብሄር የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ያወጣቸው ወደከንአን ሊስገባቸው ነው፡፡ እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ ከግብፅ ያወጣቸው አንድን ተራራ እየዞሩ እንዲቀሩ አይደለም፡፡
ነገር ገን የእስራኤል ህዝብ ተራራውን ወደውታል፡፡ ተራራውን ያውቁታል፡፡ ተራራው አስተማማኝ ነው፡፡ ተራራውን መዞር ምንም አደጋ የለውም፡፡ ተራራውን መዞር ተመችቷቸዋል፡፡
የእግዚአብሄር ፈቃድ ግን ተራራውን እንዲዞሩ ሳይሆን ወደ ተስፋይቱ ምደር እንዲገቡ ነው፡፡
ወደተስፋይቱ ምድር ለመግባት ተራራውን እንደ መዞር ከአደጋ ነፃ አይደለም፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር መሄድ የሚያውቁትን አካባቢ መተው ይጠይቃል፡፡ ወደተስፋይቱ መደር መጓዝ ለአመታት የለመዱትን መተው ይጠይቃል፡፡ ወደተስፋይቱ ምድር ለመግባት ወደማያውቁት ምድር መሄድ ይጠይቃል፡፡ ወደተስፋይቱ ምድር ለመግባት መዋጋት ይጠይቃል፡፡
ወደተስፋይቱ ምድር መሄድ ወደማያውቁት ምድር መሄድን ይጠይቃል፡፡ ወደተስፋይቱ መደር መጓዝ የማይታየውን ማየት ይጠይቃል፡፡ ወደተስፋይቱ መደር መጓዝ በእምነት መራመድ ይጠይቃል፡፡
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡6-7
ወደተስፋይቱ መደር መጓዝ ሽልማቱን አስተያይቶ የጊዜውን መከራ መናቅን ይጠይቃል፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡17-18
ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ ነፍስን በእግዚአብሄር እጅ ላይ መተው ይጠይቃል፡፡
ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። የማቴዎስ ወንጌል 16፡25
ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ የፍርሃት ስሜቱ እያለ በፍርሃት ስሜት አለመቆምን ይጠይቃል፡፡
ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ ለአመታት በነፃ የምንበላውን መና ትተን ማረስ መስራት መድከም መጀመርን ይጠይቃል፡፡
ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ ከነፍሳችን ምቾት በላይ የእግዚአብሄርን አላማ ማስቀደምን ይጠይቃል፡፡
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። የሐዋርያት ሥራ 20፡20
ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ ባለፈው ከግብፅ በመውጣታችን ብቻ ደስ በመሰኘት የለመድነውን ተራራ እየዞርን በምድረ በዳ አለመቅረትን ይጠይቃል፡፡ ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ ወደከንአን የመግባት ህልማችንን ብቻ እያሰብን በምኞት ከመኖር ይጠብቀናል፡፡ እግዚአብሄር ህልምን የሚሰጠን ስለ ህልምነቱ ሳይሆን በህይወታችን እንዲፈፀም ነው፡፡ ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ በግብፅ ባለመጥፋታችንና በመጠበቃችን ብቻ አለመርካትን ይጠይቃል፡፡
ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ በመጠበቃችን ብቻ አለመርካትን ይጠይቃል፡፡ በምድር ላይ ያለነው ራሳችንን ጠብቀን ልንኖር ብቻ ሳይሆን ፍሬ እንድናፈራ ነው፡፡ በምድር ላይ ያለነው የእግዚአብሄርን አላማ ልንፈፅም ነው፡፡ ወደተስፋይቱ ምድር መጓዝ ከመጠበቃችን አልፎ ለፍሬያማነት መዘርጋትን ይጠይቃል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ክርስቶስ #ጌታ #እረፍት #ቅድሚያ #መደገፍ #መታመን #እንዴት #እምነት #እውቀት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment