በእኔ
ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16:33
የመጀመሪያው የሰላም ምንጭ መከራ እንደለ መረዳት
ነው፡፡ መጀመሪያ ሰላሙን የሚያጣው መከራ እንዳለ የማይረዳ ሰው ነው፡፡ መጀመሪያ ሰላሙን የሚያጣው የተሳሳተ ከመከራ የፀዳ የአለም
ምስል በአእምሮው ያለው ሰው ነው፡፡ መጀመሪያ ሰላሙን የሚያጣው መከራን የማይጠብቅ ሰው ነው፡፡
በአለም መከራ መጀመሪያ የሚሰናከለው በአለም ሳለን
ከመከራ ነፃ እንደምንሆን የሚያስብ ሰው ነው፡፡ በአለም ሳለን መከራ እንዳለብን የሚረዳ ሰው አሸናፊ ነው፡፡
የአለምን መከራ ለማሸነፍ የመጀመሪያው ደረጃ መከራ
የአለም ኑሮ አንዱ ክፍል እንደሆነ መረዳት ነው፡፡ የአለምን መከራ የማሸነፍ ቅድም ሁኔታው በአለም ሳለን መከራ እንደሚገጥመን መጠበቅ
ነው፡፡
መከራ ሊገጥመኝ አይችልም ብሎ የሚያስብ ሰው ሞኝ
ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ሳደርግ ተግዳሮት አይገጥመኝም የሚል ሰው ስለህይወት ያለተረዳ ሰው ነው፡፡
በሳል ሰው በሁኔታዎች ውስጥ የእግዚአብሄርን አሰራር
የሚረዳ ሰው ነው፡፡ በሳል ሰው የእግዚአብሄርን አላማ ስናስፈፅም በመንገዳችን የሚቆመውን የሰይጣንን አካሄድ የሚረዳ ሰው ነው፡፡
በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡11
ጥያቄው
እንዴት መከራን እንለፈው እንጂ መከራ አለ የለም አይደለም፡፡ ወደ ፈተና ላለመግባት ለመከራ የምንዘጋጀው በሰላሙ ቀን በፀሎት ነው፡፡
ወደ
ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው። የሉቃስ ወንጌል 22፡46
ጥያቄው
መከራን ለማለፍ ህይወታችን የእግዚአብሄርን ቃል በመታዘዝ መሰረት ላይ እንገንባ እንጂ መከራ አለ የለም አይደለም፡፡
ስለዚህ
ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ
ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። የማቴዎስ ወንጌል 7፡24-25
ጥያቄው
መከራን የምናልፈው የእግዚአብሄርን ጥበብ በመቀበል ነው የሚል እንጂ መከራ አለ የለም አልነበረውም፡፡
ወንድሞቼ
ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት . .
. ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። የያዕቆብ
መልእክት 1፡2-5
ጥያቄው
መከራ አለ የለም ሳይሆን መከራ በህይወታችን የሚሰራውን የፍፁምነት ድንቅ ስራ ነው፡፡
ወንድሞቼ
ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም
ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። የያዕቆብ መልእክት 1፡2-4
የሰላም
ምንጭ በአለም ሳለን መከራ እንዳለብን መረዳትና መከራን እንዴት ማስተናገድ እንደለብን እንደምናሸንፈው ከእግዚአብሄር ቃል መማር
ነው፡፡
በእኔ
ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።
የዮሐንስ ወንጌል 16:33
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ክብር #መዋረድ #መከራ #ፈተና #መፅናት #መታገስ #ሰላም #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment