ህይወትህ ብትንትን ያለና ምንም ቅርፅ የሌለው
መስሎሃል?
የምትፈልግው ተስፋ ርቆ እንደተሰቀለ ያህል ተሰምቶሃል?
አለኝ ብለህ የተማመንከብተ ነገር እየፈረሰ እንዳለ
ተሰምቶሃል?
ያለፈው ህይወትህ መላው ህይወትህን ሁሉ እንዳበላሸው
እና ሊስተካከል እንደማይችል ተሰምቶሃል?
በህይወት ያለህ ጊዜ እና ማድርግ የምትፈልገው
ነገር እንዳልተመጣነ ተሰምቶሃል?
የህይወት መንገድህ ተግዳሮት እንደተራራ ገዝፎብሃል?
ሰው ሊታመን እና ለጨበጥ እንደማይችል ተሰምቶሃል?
ጊዜ እያለፈብህ እንደሆነ ከህይወት ወደኋላ እንደቀረህ
ተሰምቶሃል?
ካለህበት አስቸጋሪ ነገር ውስጥ የመውጫው መንገድ
እንደሌለው ተሰምቶሃል?
በልብህ ወደምታየው ደረጃ እየሄድክ እንዳለሆንክ
ተሰምቶሃል?
እዛው አንድ ቦታ እየረገጥክ እንደሆነና ህይወትህ
ለውጥ የሌለው ድግግሞሽ እንደሆነ ተሰምቶህ ይሆን?
እንግዲያውስ በእግዚአብሄር ለመደገፍ ትክክለኛው
ቦታ ላይ ነህ፡፡
እንግዲያውስ በእግዚአብሄር መደገፍ ብቻ የሚጠቅምበት
ትክክለኛ ቦታ ላይ ነህ፡፡
እንግዲያውስ ሲጀመር በእግዚአብሄር መደገፍ ያስፈለገበት
ትክክለኛ ቦታ ላይ መጥተሃል፡፡
እንግዲያውስ በእግዚአብሄር መደገፈ የሚባለው ነገር
የተሰራበት እና የታለመበት ትክክለኛው ቦታ ላይ ደርሰሃል፡፡
እውቀታችን ሙሉ አይደለም፡፡ ሁሉንም ከመጀመሪያው
እስከመጨረሻው እንደ ነጭና ጥቁር በፍፁም የምንረዳና እውቀታችን ሙሉ ቢሆን ኖሮ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ አይጠበቀብንም ነበር፡፡
ሁሉን በሚያውቀውና እኛን ከምናስበው በላይ በሚወደን በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ያስፈለገው እውቀታችን ውስን ስለሆነ ነው፡፡
በራሳችን ሁሉንም ነገር ማድረግ የምንችል ብንሆን
በእግዚአብሄር ላይ መደገፍን አያስፈልግም ነበር፡፡ በሃይልም በችሎታም ከእኛ እጅግ ከፍ ባለው በእግዚአብሄር ላይ የምንደገፈው ጉልበታችን
ውስን ስለሆነና በራሳችን ማድረግ የማንችለው ነገር ስላለ ነው ፡፡
ደግሞም በእግዚአብሄር ላይ ያለን መደገፍ ለዚህ
ወሳኝ ጊዜ ካልጠቀመን መቼ ሊጠቅመን ነው?
እምነት የሚጠቅመው ሁሉ ነገር ቦታ ቦታውን ሲይዝ
እና ሲሰምር አይደለም፡፡ እምነት የሚጠቅመው የምንፈልገውን ነገር ሁሉ በእጃችን ስናስገባ አይደለም፡፡ እምነት የሚጠቅውመው ሁሉም
ነገር በታሰበው ጊዜና ሁኔ ሲሄድ አይደከለም፡፡ እምነት የሚያስፈልገው በስኬት ተራራ ላይ የወጣን ሲመስለን አይደለም፡፡ እምነት
የሚያስፈልገው ሁሉንም የህይወትህ አቅጣጫ ቅርፅ ሲይዝ አይደለም፡፡ እምነት እና በእግዚአብሄር ላይ ተስፋ ማድረግ የሚያስፈልገው
የምትፈልገው ነገር በእጅህ ለመግባት ሲፈጥን አይደለም፡፡
ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡24
እምነትና በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ የሚጠቅመው
ማድረግ የሚገባህን ነገር ለማድርግ አቅም ሲያንስህ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ የሚጠይቀው እንዴት ሊሆን እንደሚችል መውጫና
መግቢያው ሲጠፋህ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ የሚጠይቀው የህይወት ክር ውስብስብ ብሎ ውሉ ሲጠፋብህ ነው፡፡ በእግዚአብሄር
ላይ መደገፍ የሚጠይቀው ህይወት እንደቆመ ሲመስልህ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ
የሚጠይቀው በህይወት ማድረግ የምትፈልጋቸው ነገሮችና ያለህ ጊዜ ሳይመጣጠን ሲቀር ነው፡፡ በእግዚአብሀር ላይ መደገፍ የሚጠይቀው
ማድርግ አለብኝ ብለህ የምታስበውና ማድርግ የምትችልበት አቅምህ ልዩነት ሲያመጣ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መታመን የሚጠይቀው ጊዜ
እያለፈብህ እንደሆነ እና ወደኋላ እንደቀረህ ሲሰማህ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መታመን የሚያስፈልገው በህይወትህ የሚሆኑት ነገሮች
ለምን እንደሆኑ ምክኒያትን ስታጣላቸው ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መታመን የሚጠይቀው ለዚህ አልፌ አልሰጠም ላልከው ነገር አልፈህ
ስትሰጥ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ መታመን የሚጠይቀው በህይወትህ የሆነው ነገር ምክኒያቱ ነገር ሁሉ ለበጎ ስለሚደረግ ብቻ እንደሆነ ከማመን በቀር ሌላ ምክኒያትን ስታጣ ነው፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡28፣31
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ ምሳሌ 3፡5
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር
share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ማየት #አለማየት #ቃል #መታመን #መገደፍ #መተማመን
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መደገፍ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment