Popular Posts

Monday, December 16, 2019

ይህ እንዴት ይሆናል?



ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው። መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። የሉቃስ ወንጌል 1፡34-35
ማሪያም በድንግልናዋ ልጅ ትወልጃለሽ ስትባል ይህ እንዴት ይሆናል ብላ በመጠየቅዋ እግዚአብሄር አልተቆጣም፡፡
ከእግዚአብሄ ጋር ባለሽ የህይወት እርምጃ ይህ እንዴት ይሆናል ካላልሽ በእምነት መኖር አልጀመርሽም ማለት ነው፡፡ ሁሉንም ነገር አውቀሽ ከጨረሽ የምትኖሪው በስሌት እንጂ በእምነት አይደለም፡፡ ህይወትሽን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው የምታውቂ ከሆንሽ የምትመላለሽው በእምነት ሳይሆን በማየት ነው፡፡
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡6-7
እምነት ያስፈለገው በተፈጥሮአዊ አይናችን የማናየውን ነገር ለማየት ነው፡፡ እምነት የሚያስፈልገው እውቀት ስለሌለን ነገር እውቀት ባለው በእግዚአብሄር ላይ ለመደገፈ ነው፡፡
ስለዚህ በህይወት ጉዞሽ ይህ እንዴት ይሆናል ካላልሽ እምነትን የምታውቂው በዝና እንጂ በተግባር አይደለም፡፡  
ሁላችንም ይህ እንዴት ይሆናል የምንልበት አጋጣሚ አለ፡፡ እግዚአብሄር የሚናገረንና እኛ ያለንበትን ስናስተያየው ይህ እንደት ይሆናል ብሎ መጠየቅ ያለ ነው፡፡ በእጃችን ያለው ሃይልና እግዚአብሄር እንድንፈፅጽመው የሰጠን ስራ ሲስተያይ ይህ እንደት ይሆናል ማለት የተለመደ ነው፡፡ የህይወት መንገዳችንን አስልተን አስልተን እንቆቅልሹ አልፈታም ሲለን ይህ እንዴት ይሆናለ ማለት ግዴታ ነው፡፡
አምኛለሁ መንገዱን ግን አላውቀውም ማለት ያለ ነው፡፡ አንተ ትክክል ነህ አንተ ፃድቅ ነህ አንተ አትሳትም ግን ይህ እንዴት ይሆናል ማለት ትህትና ነው፡፡ እንዴት እንደሚሆን ባይገባቸውም እንኳን እግዚአዚአብሄር የሚናገራችውን ነገር አምነው የሚቀበሉት እግዚአብሄር ደስ ይሰኛሉ፡፡
የእግዚአብሄርንም አደራረግ ሙሉ ለሙሉ ባይረዱትም በትህትና ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ በሚሉት እግዚአብሄር ይደሰታል፡፡
ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። መጽሐፈ ኢዮብ 42፡2
እግዚአብሄር እንድናምን እንጂ ሁሉንም እንድንረዳ አይጠብቅብንም፡፡ እግዚአብሄር በእምነት እርምጃ እንድንወስድ እና ከእግዚአብሄር ጋር እንድንተባበር እንጂ እንድንፈፅጽመው አይጠብቅብንም፡፡ የስራው ባለቤት እግዚአብሄር ነው፡፡ የስራው ዋና ሰራተኛ እግዚአብሄር ነው፡፡ እኛ አብረን ሰራተኞች ነን፡፡
እሺ ጌታ ሆይ የሚሉትን ሰዎች እጃቸውን ይዞ ወደ እቅዱ ወስጥ ያስገባቸዋል፡፡  
በትህትና ሳይሆን ይህ አይሆንም ከሚል ድምዳሜ ተነስቶ እንዴት ይሆናል ማለት ግን ትእቢት ነው፡፡
ዘካርያስም መልአኩን፦ እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው። እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው። የሉቃስ ወንጌል 1፡18፣20
ሰው የእግዚአብሄር ፈቃድ ሲሰማ በጣም የሚረበሸው እግዚአብሄር በራሱ እንዲፈፅመው የፈለገበት ስለሚመስለው ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ማንንም ተማምኖ አይናገረም፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን ለራሱ ሊያስገዛ የሚችልበት አሰራር አለው፡፡ እግዚአብሄር ሊሆን ያለውን ሲናገር ሁሉንም አዘጋጅቶ ነው፡፡ የእግዚአብሄር አምላዊ መልስ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው፡፡  
ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው። መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። የሉቃስ ወንጌል 134-35
ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በመንፈሴ እንጂ በሃይልና በብርታተ አይደለም የሚለው፡፡
ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውም መልአክ መልሶ፦ እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን? አለኝ። እኔም፦ ጌታዬ ሆይ፥ አላውቅም አልሁ። መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ዘካርያስ 4፡5-6
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ክርስቶስ #ጌታ #እረፍት #ቅድሚያ #መደገፍ #መታመን #እንዴት #እምነት #እውቀት #መደገፍ #ሰንበት #በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment