Popular Posts

Tuesday, December 17, 2019

በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ



ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ። ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡12-14
በክርስቶስ መከራ በምንካፈልበት ልክ ወደእኛ የሚመጡ ብዙ በረከቶች አሉ፡፡
በክርስቶስ መከራ መካፈል ክብር ነው፡፡ በክርስቶስ መከራ የመካፈልን ክብር ከመፅሃፍ ቅዱስ እንመልከት
1.      በክርስቶስ መከራ መካፈል የመዳናችን ምልክት ነው
ኢየሱስ ጌታ ነው ብንለን ከመሰከርብ ጊዜ አንስቶ ከጠላት ግዛት ወጥተን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ገብተናል፡፡ ለኢየሱስ እሺ ማለት ለሰይጣን እንቢ ማለት ነው፡፡ ሰይጣን እንደፈለገ ሲገዛቸውና ሲጠቀምባቸው የነበሩት ሰዎች ሲያምፁበት ደስ አይለውም፡፡ ከቻለ ከክርስቶስ መንገድ ሊያሰናክለን ካልቻለ ደግሞ ደስተኛ ሆንን እንዳንከተለው ይጥራል፡፡
ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። የዮሐንስ ራእይ 210
2.     በክርስቶስ መከራ መካፈል የጥሪያችን አንዱ ክፍል ነው
መከራ ሲገጥመን እንግዳ ነገር እንደመጣብን ከእግዚአብሄር መንገድ እንደሳትን መቁጠር የለብንም፡፡
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት የያዕቆብ መልእክት 1፡2-3
ከክርስቶስ ጋር አብረን ለመውረስ አብረን መከራን መቀበል አለብን፡፡
ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡17
3.     በክርስቶስ መከራ መካፈል የመዳን ምልክት ነው
በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡28-29
ክርስቶስን እየተከተለ መከራ የማይቀበል ሰው እንጂ መከራን የሚቀበለ ሰው አያስደንቅም፡፡
በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ። በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡11-12
4.     በክርስቶስ መከራ መካፈል ሙሉ ሰዎች ያደርገናል
ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም። የያዕቆብ መልእክት 12-4
በሌላ መንገድ የማይሰራውን ባህሪያችንን ስለሚሰራ በክርስቶስ መከራ በመፅናት እንመካለን
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 53-4
5.     በክርስቶስ መከራ መካፈል ከክብሩ አንፃር ምንም አይደለም
ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን። ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡17-18
6.     በክርስቶስ መከራ መካፈል የእግዚአብሄርን መንፈስ ሃይል ያበዛልናል
ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡14
7.     በክርስቶስ መከራ መፅናት የአክሊላችን ምክኒያት ነው
ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ። የዮሐንስ ራእይ 2፡10
8.     በክርስቶስ መከራ መካፈል ክብራችን ነው
ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው። እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤ የሐዋርያት ሥራ 5፡40-41
9.     በክርስቶስ መከራ መካፈል የሚያስደስት እንጂ የሚያሳፍር አይደለም
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር። 1 የጴጥሮስ መልእክት 416
10.    በክርስቶስ መከራ መካፈል በሰማይ ታላቅ ዋጋ አለው
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። የሉቃስ ወንጌል 6፡22-23
11.     የእምነት አባቶች እንድንመስላቸው ያዘዙን በክርስቶስ መከራ በመካፈል ጭምር ነው
እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤ 2 ጢሞቴዎስ 18
12.    በክርስቶስ መከራ መካፈል የተሻለ ነገር እንዳለን የእምነት ምልክት ነው
ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ። የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ወደ ዕብራውያን 10፡32-34
13.    በክርስቶስ መከራ መካፈል አውቀን ወስነን የምንገባበት ክብር ነው
ህይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ በክርስቶስ መከራ መካፈል ዋጋችንን ተምነን በእውቀት የምንወስነው ውሳኔ ነው፡፡
ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። ወደ ዕብራውያን 11፡25-26
14.    መከራ የእግዚአብሄርን ብቸኛ አዳኝነት እና የሚያስችል ሃይል የምናይበት ወርቃማ እድል ነው
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡9-10
15.    በክርስቶስ መከራ መካፈል እግዚአብሄርን የሚያስደስተውን እውነተኛ መታዘዝን ያስተምረናል
ልጅነታችን ከመከራ አያድነንም፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ መታዝዝን የተማረው ከተቀበለው መከራ ነው፡፡ 
ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ወደ ዕብራውያን 5፡8

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #መዋረድ #መከራ #ፈተና #መፅናት #መታገስ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #አንድነት #ፀጋ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment