ዘርህ
እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡18
እግዚአብሄር
ለአብርሃም ልጅ እሰጥሃለሁ ሲለው እስከ 100 ዓመቱ ድረስ ልጅህ አልነበረውም፡፡ ሚስቱም ሳራ አርጅታ ነበር 90 ዓመት ሆኗት ነበር፡፡
በምድራዊ
አስተያየት አብርሃም ልጅ የመውለድ ምንም ተስፋ አልበነረውም፡፡
አብርሃም
የቀረው አንድ ተስፋ የእግዚአብሄር የተስፋ ቃል ብቻ ነበር፡፡
እምነት
የሚያስፈልገው በምድር ተስፋ ስለሌለው ነገር ነው፡፡ በምድር ተስፋ ላለው ነገር ግን ምን እምነት ያስፈልገዋል?
እምነት
ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው እንደሚል አብርሃም የእግዚአብሄርን ቃል ተስፋ አደረገ፡፡ የምድር አሰራር ልጅ ለመውለድ
ተስፋ ቢያስቆርጠውም አብርሃም የእግዚአብሄርን አሰራር ተስፋ አደረገ፡፡ አብርሃም የመውለድ ሃይሉ ተስፋ ቢያስቆርጠውም በእግዚአብሄር
ሃይል ተስፋ አደረገ፡፡ አብርሃም ሰውነቱ ተስፋ ቢያስቆርጠውም እግዚአብሄርን ተስፋ አደረገ፡፡
የመቶ
ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ወደ ሮሜ ሰዎች 4፡19
አብርሃም በስጋ ሲደክም በእምነት በረታ፡፡ የምድራዊ
ልጅ የመውለድ ተስፋው ቢያደክመውም አብርሃም በእምነቱ አልደከመም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ተስፋ #እምነት #ቃል
#ከመስማት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment