Popular Posts

Sunday, December 8, 2019

እንደገና መኖር ቢፈቀድልኝ



እንደገና መኖር ቢፈቀድልኝ ደግሜ እና አብዝቼ የምኖረው የፍቅርን ህይወት ነው፡፡ የክርስትና ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ህይወት ምንም እንከን የማይወጣለት ህይወት ነው፡፡  
ሰዎች ይህንን የፍቅርን ህይወት ላለመኖር የሚያቀርቡት አንዱ ምክኒያት ስለማልችል ነው አቅቶኝ ነው ከባድ ነው የሚል ብቻ ነው፡፡ ይህንን የፍቅርን ህይወት ላለመኖር የፍቅር ህይወት ችግሩ ይህ ነው የሚል ሰው የለም፡፡ በህይወቴ ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ጥሩ አይደለም የሚል ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡
እውነተኛው ፍቅር በኢየሱስ አዳኝነት ከእግዚአብሄር ጋር በመታረቃችን በልባችን የሚፈስ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው እንጂ እውነተኛው ፍቅር በተፈጥሮ አይገኝም፡፡ ሰው ኢየሱስ በውስጡ ካልኖረ በስተቀር የፍቅርንብ ህይወት ለመኖር አቅም የለውም፡፡
በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 5፡5
ነገር ግን የሰው ግብ መሆን ያለበት በፍቅር መኖር ነው፡፡
ፍቅር የሚወጣለት ነገር የለም፡፡ በፍቅር ላይ የሚሰራ ህግ የለም፡፡ ፍቅር ከህጎች ሁሉ የበላይ ነው፡፡ ፍቅርን ደርሶበት የሚከሰውና የሚያስቀጣው ምንም ህግ የለም፡፡ ከፍቅር በላይ የሚጠበብ ጠቢብ የለም፡፡ ከፍቅር በላይ ሃያል የለም፡፡ ከፍቅር በላይ ባለጠጋ የለም፡፡ ህጎች ሁሉ ለፍቅር ህግ ይገዛሉ፡፡
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22-23
ፍቅር ንፁህ ነው፡፡ ፍቅርን በንፅህና ጉድለት የሚያማው ማንም የለም፡፡ ፍቅርን ይህ ይህ ችግር አለበት የሚል ሰው የለም፡፡
ለሰው መልካም አሰብክ ፣ ለሰው መልካም ተናገርክ ለሰው መልካም አደረክ ብሎ የሚከስ እና የሚያስፈርድ ሰው የለም፡፡
እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡13
ጌታ ኢየሱስን በመከተል የሚገኘውን የዘላለምን ህይወት የእግዚአብሄር አብሮነትና ከሃጢያት አርነት መውጣት ትተን በምድር ላይ በፍቅር መኖር ጤናን ይሰጣል፡፡ ሰው ለፍቅር በፍቅር ስለተፈጠረ ከፍቅር ውጭ ጤናማ አይሆንም፡፡
ማንም ሰው በንፅህናው ምንም እንከን በማይወጣለት በፍቅር ቢኖር ያተርፋል እንጂ አይከስርም፡፡
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡22-23
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #መውደድ #መስጠት #መባረክ #ማንሳት #ድፍረት #መልካም #ማካፈል #ሙላት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #መታበይ #ራስወዳድነት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment