ስለዚህ ማንም በክርስቶስ
ቢሆን አዲስ
ፍጥረት ነው፤
አሮጌው ነገር
አልፎአል፤ እነሆ፥
ሁሉም አዲስ
ሆኖአል። 2ኛ
ወደ ቆሮንቶስ
ሰዎች 5፡17
የሰውን ማንነቱን ፣ ተፈጥሮውን ፣ ባህሪውን
፣ ተስፋውን ፣ ግቡን የሚለውጠው እና የሚያድሰው አዲስ ፍጥረት መሆኑ ነው፡፡ ሰው አዲስ ፍጥረት ካልሆነ አዲስ ወር አዲስ አመት
በመጣ ቁጥር አዲስ ነገር መጠበቅ ተመሳይ ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት እንደመጠበቅ ከንቱ ነው፡፡
አዲስ ዘመን እንዲሆን አዲስ ሰው ይጠይቃል፡፡
አዲስ ዘመን ቢመጣም ሰውየው አዲስ ካልሆነ ዋጋ የለውም፡፡
ኢየሱስ አዲስ ነገር በአዲስ መያዣ ውስጥ መቀመጥ
እንዳለበት ከዚህ በታች ባሉት ጥቅሶች በማብራሪያ ያስተምራል፡፡ አዲስ አመት አዲስን ሰው ይጠይቃል፡፡ አዲስነት እንዲሰምር ሁለቱም
አዲስ መሆን አለባቸው፡፡ አንዱ ብቻ አዲስ ሆኖ ሌላው አሮጌ ከሆነ አይሰራም፡፡
በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። የማርቆስ ወንጌል 2፡21-22
መልካም አዲስ አመት
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ቀን
#አመት #ወንጌል
#አዲስአመት #ለውጥ
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
#እንቁጣጣሽ #ዘመንመለወጫ
No comments:
Post a Comment