Popular Posts

Monday, November 25, 2019

ሥራ ፈቶች



እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡8-10
ስንፈጠር ለስራ ለትጋት ለመከናወን ተፈጥረናል፡፡
በህይወት ደግሞ ገለልተኛ የሚባል ነገር የለም፡፡ ወይ አንዱን ይወዳል ሌላውን ይጠላል ወይ አንዱን ይንቃል ሌላውን ያከብራል፡፡
ለገንዘብ ያለመገዛት ፍቱን መድሃኒት ለእግዚአብሄር መገዛት ነው፡፡ ለእግዚአብሄር የሚገዛ ሰው ለገንዘብ መገዛት በህይወቱ ይሞታል፡፡ 
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። የማቴዎስ ወንጌል 6፡24
ሰው ካልተጋ ስራ ፈት እና ፍሬ ቢስ ይሆናል፡፡ ሰው ከተጋ ፍሬያማ ደግሞ ይሆናል፡፡ በትጋትና በስራ ፈትነት መካከል ከሁለቱም ያለሆነ ምንም ገለልተኛ ስፍራ የለም፡፡
በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር ማድረግ እንችልም፡፡ ራሳችንን ለአንድ ነገር ከሰጠን ለሌላው ተቃራኒ ነገር እንከለክላለን፡፡
የስጋን ነገር ካሰብን የመንፈስን ነገር ማሰብ አንችልም፡፡ የመንፈስን ነገር ካሰብን በቅፅበት የስጋን ነገር ከማሰብ ነጻ እንወጣለን፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡5-6
ብልቶቻችንን የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርገን ካቀረብን የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርገን ለእግዚአብሔር ማቅረብ አንችልም፡፡
ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ወደ ሮሜ ሰዎች 6፡13
ራሳችንን ለጭንቀት ከሰጠን መፀለይና ጭንቀታችንን በጌታ ላይ መጣል አንችልም፡፡ ከፀለይን አቅማችንንና ጉልበታችንን ከጭንቀት መልሰን ወደ ፀሎት አናፈሰዋለን፡፡ ከፀለይን ጊዜያችንን ጉልበታችንን አቅማችንን በጭንቀት ላይ ከማዋል እንድናለን፡፡
የእግዚአብሄርን ቃል ለማመን ጊዜን ከሰጠን የእግዚአብሄርን ቃል ከሰማን እና ካሰላሰልን ቃሉን ማመን እንጂ መጠራጠር አንችልም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ የማቴዎስ ወንጌል 21፡21
ፍቅርን የምትከታተሉ ከሆነ ለጥላቻ ጊዜ ጉልበት አቅም አይተርፋችሁም፡፡
ፍቅርን ተከታተሉ፥ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡1
ሰይጣንን የመቃወሚያ ተዘዋዋሪ መንገድ ለእግዚአብሄር መገዛት ነው፡፡ ለእግዚአብሄር መገዛታችሁ በራሱ ዲያቢሎስን በህይወታችሁ እንድትቃወሙ ያደርጋችኋል፡፡ ለእግዚአብሄር መገዛታችሁ ዲያቢሎስ በህይወታችሁ ስፍራ እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡
እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ የያዕቆብ መልእክት 4፡7
በመንፈስ መመላለሳችሁ ከስጋ ስራ ጋር እንድትለያዩና የስጋን ስራ እንዳትፈፅሙ ያደርጋችኋል፡፡ ሰው የስጋን ምኞት ላለመፈፀም ከመንቀጥቀጥና ከመፍራት ይልቅ በመንፈስ ቢመላለስ ሳያውቀው የስጋን ስራ አይፈፅምም፡፡
ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡16
ሰው ማሰብ የሚችለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የሚያስብ ሰው ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ ማሰብ ዜና ቦታ አይኖረውም፡፡
በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡8
ሰው የአለምን ነገር ላለማሰብ እና ላለማድረግ ከመፍጨርጨር ይልቅ የእግዚአብሄርን ነገር ለማሰብ ራሱን ቢሰጥ ከአለማዊነት ይድናል፡፡ 
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡2
ሰው በተጠራበት ነገር ላይ ሲያተኩርና ሲተጋ ህይወቱ ከስራ ፈትነትና ከፍሬ ቢስነት ይድናል፡፡ ሰው የራሱ ስራ ከሌለው በሰው ስራ ውስጥ ራሱን ማግኘቱ እና ህይወቱን ማባከኑ አይቀሬ ነው፡፡ ሰው ስለተጠራበት ነገር ግልፅ ራእይ ከሌለው ጊዜውን እና ህይወቱን በሌላው ራእይ ላይ ያባክናል፡፡
ሥራ ከቶ ሳይሠሩ፥ በሰው ነገር እየገቡ፥ ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና። 2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 3፡11
እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡8-10
ሰው የህይወት መንፈስ ህግን ከተከተለ ከሃጢያትና ከሞት ህግ ነፃ ይወጣል፡፡ ሰው ሃጢያትን ላለመስራት ከመፍጨርጨር ይልቅ የህይወት መንፈስን ህግ መከተሉ በራሱ ከሃጢያት ያድነዋል፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡2
ሰው ሌላውን ሰው ከባረከና ከፀለየለት እርሱን የሚጠላበት እና የሚረግምበት አቅም አይተርፈውም፡፡
ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡9
ሰው ትኩረቱን የሰማያዊው ነገር ላይ ካደረገ በሚጠፋው የምድራዊ ነገር ላይ ማተኮር አይችልም፡፡
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡1-2
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ንስሃ #መመለስ #ሃጢያት #ይቅርታ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #መናዘዝ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

የሚበልጥ አላማ


ከእኛ መካከል ራሱን የፈጠረ ማንም የለም፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሄር ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ የተፈጠረንበት አለማ ከመፈጠራችን በፊት ነበር፡፡ የተፈጠረነው የተፈጠርንበትን አላማ ለማሳካት ነው፡፡ ወደምድር የመጣነው የተፈጠርንበትን አላማ ለማስፈፀም ነው፡፡
ከእግዚአብሄር አላማ የሚበልጥ ምንም ነገር በምድር ላይ የለም፡፡
በምድር ላይ ያለው ነገር ሁሉ የእግዚአብሄርን አላማ ለማስፈፀም የተሰራ ነገር ነው፡፡ በምድር ላይ ያለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሄር አላማ ተስርቷል እንጂ የእግዚአብሄር አላማ በምድር ላይ ላለው ነገር አልረተሰራም፡፡
የእግዚአብሔር አላማ ከደስታችን ይበልጣል
ደስ ሊለን የሚገባው በህይወታችን የእግዚአብሄርን አላማ ስናደርግ ብቻ ነው፡፡ ደስ ሊለን የሚገባው ከእግዚአብሄር አላማ በተቃራኒ ባለመሄዳችን ነው፡፡ ደስ ሊለን የሚገባው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወታችን በመፈፀም እግዚአብሄርን ስናስደስተው ነው፡፡ ከእግዚአብሄር አላማ በተቃራኒው በመሄድ የሚገኝን ጊዜያዊ ደስታ መናቅ አለብን፡፡
ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። ወደ ዕብራውያን 11፡25-26
የእግዚአብሔር አላማ ከክብራችን ይበልጣል
በእግዚአብሀረ መልክና አምሳል በእግዚአብሀረ ክብር ተፈጥረን ነበር፡፡ በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄ ክብር ወድቀን ለዘላለም ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይተን ነበር፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ በሰራው የደህንነት ስራ ምክኒያት የእግዚአብሄር  ልጆች ሆነናል፡፡ አሁን ክብራችን እግዚአብሄር ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ቤተሰብ ውጭ ክብር የለንም፡፡ ከእግዚአብሄር አላማ ውጭ ክብር የለንም፡፡   
ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። የሐዋርያት ሥራ 20፡24
የእግዚአብሔር አላማ ከፈቃዳችን ይበልጣል
በህይወት የምንወደው እና የምንፈልገው ነገር አለ፡፡ የምንወድውንና የምንፈልገውን ነገር የምንፈልገው ከእግዚአብሄር አላማ ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር አላማ ጋር የተጋጨ እለት የምንፈልገውን ነገር አንፈልገውም የምንወደውን ነገር አንወደውም፡፡
ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22፡42
የእግዚአብሔር አላማ ከምቾታችን ይበልጣል
አንድን ነገር የምናደርገው ስለሚመቸን ወይም ስከለማይመቸን አይደለም፡፡ አንድን ነገር የምናደርገው የእግዚአብሄር አላማ ስላበት ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ከሌለበት ምንም ምቹ ነገርን ምቹ ስለሆነ ብቻ አናደርገውም፡፡ ለእኛ የመጨረሻው የምቾት ቦታ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ቦታ ነው፡፡  
እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው። ኦሪት ዘጸአት 3315-16
የእግዚአብሔር አላማ ከእኔነታችን ክብር ይበልጣል
የእኛ ኑሮ ለሞተልን ለእርሱ ነው፡፡ የሞተልንም ለሞተልን እንጂ ወደፊት ለራሳችን እንዳንኖር ነው፡፡ ከእርሱ ክብር የተለየ ክብር የለንም፡፡ ከእርሱ አላማ የሚበልጥ አላማ የለንም፡፡
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡15
እርስ በእርስ ከምንቀባበለው ክብር ይበልጥ የምንፈልገው ከአንዱ ከእግዚአብሄር የሚገኘውን ክብር ነው፡፡
እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? የዮሐንስ ወንጌል 5፡44
የእግዚአብሄር አላማ ከተቀባይነት ይበልጣል
የእግዚአብሄር አላማ ከሰው ከምናገኘው እሺታ እና ተቀባይነት ይበልጣል፡፡ ሰው ቢቀበለን ባይቀበለምን እግዚአብሄር ከተቀበለን ይበቃናል፡፡  
ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም። ወደ ገላትያ ሰዎች 1፡10
የእግዚአብሔር አላማ ከዝናችን ይበልጣል
አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፡8-9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #ወንጌል #አላማ #እቅድ #ግብ  #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

Saturday, November 23, 2019

በእኛ እንደሚማልድ



ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡18-20
በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ አምነትን የዳንን ሁላችን የክህንነት አገልግሎታችን ሁለት ነው፡፡ አንደኛው ስለሰው ለእግዚአብሄር መናገር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለእግዚአብሄር ለሰው መናገር ነው፡፡
ስለሰው ለእግዚአብሄር የመናገር የክህንንት አገልግሎታችን የምልጃ አገልግሎታችን ነው፡፡ በጠላት ስለተያዙ ራሳቸውን ማዳን ስለማይችሉ ሰዎች ካሉበት እስራት ውስጥ ይወጡ ዘንድ ስለሰው በእግዚአብሄር ፊት እንቆማለን፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ የታረቅን ሁላችን እግዚአብሄር የሰውን ክፋት እና አመፅ አይቶ እንዳይቀጣ እንዲራራ ይቅር እንዲል በእግዚአብሄርን በሰው መካከል እንቆማለን ስለሰዎች እንማልዳለን፡፡ ለራሳቸው መፀለይ ለማይችሉ ሰዎች በእነርሱ ቦታ ሆነን ህመማቸው ስቃያቸው እይተሰማን በእግዚአብሄር ፊት እንቆማለን እንለምናለን እንማልዳለን፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡1-2
ሁለተኛው የክህንነት አገልግሎታችን ስለእግዚአብሄር ለሰው መናገር ነው፡፡ ለእግዚአብሄር መንግስት አምባሳደሮች መልክተኞች ነን፡፡ እንደ ካህናት የእግዚአብሄርን ፍላጎትና ፈቃድ እናስፈፅማለን፡፡ እንደካህናት በህይወታችን የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቅ ፍላጎት እናስቀድማለን፡፡ እንደ ካህናት ስለእግዚአብሄር መንግስት መስፋት አንሰራለን፡፡ እንደካህናት በህይወታችንም በንግግራችንም ስለእግዚአብሄር መንግስት በጎነት እንመሰክራለን፡፡
እንደካህናት ሰዎች የእግዚአብሄርን መልካምነት በህይወታችው አይተው እንዲማረኩ የእግዚአብሄርን በጎነት በህይወታችን በማንፀባረቅ በጎን በማድረግ እንተጋለን፡፡
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡16
እንደካህናት ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር እንዲታረቁ እንለምናለን፡፡ እንደካህናት የእግዚአብሄርን የፍቅር ልብ ለሰዎች እናሳያለን፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ልመናና #ጸሎት #ምልጃ #ህይወት #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

ሞትም ጥቅም ነውና



ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡21-24
በምድር ያለንው ተልከን ነው፡፡ በምድር ያለንው እግዚአብሄር በምድር ላይ የሰጠንን ወንጌልን የመስበክ ስራን ለመፈፀም ብቻ ነው፡፡ በምድር ያለነው ስራችንን እስክንጨርስ ብቻ ነው፡፡  
እግዚአብሄር እኛን በምድር ላይ ያስቀመጠበት አላማ ሲያልቅ በምድር ላይ አንድ ሰከንድ መቆየት አንፈልግም፡፡
በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡6-7
በምድር ያለነው ከዚህ የተሻለ ቦታ ስለሌለ አይደለም፡፡ ክርስቶስን የምንከተል ሁላችን የምድርን ውጣ ውረድ ስናስብ መሄድን ከክርስቶስ ጋር መሆንን እንመርጣለን ለእኛ እጅግ የሚሻል ነውና፡፡ ከርስቶስን ስንቀበል በትንሳኤ ከሞት ስለተነሳን እና ለዘላለም ከእግዚአብሄ ጋር ስለምንኖር ሞት ለእኛ ወደጌታ መሄጃ በር ነው፡፡  
ለእኛ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ወደፊት ለራሳችን ስለማንኖር ለእኛ የሚሻል ስለሆነ ብቻ አንፈልገውም፡፡ የምንፈልገው የእግዚአብሄርን አላማ ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ስላለበት ከምቾት ይልቅ የምንፈልገው ተግዳሮቱን ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ስላለበት ከእረፍቱ ይልቅ የምንፈልገው ተጋድሎውን ነው፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ስላበት የምንፈለግው ቶሎ መሄዱን ሳይሆን ጠብቀን ሃላፊነታችንን ተወጥተን በመጨረሻ አክሊላችንን መቀበል ነው፡፡
 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡21-24
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

Thursday, November 21, 2019

ተምሬአለሁ



የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13
በክርስትና ህይወት በምናልፍበት የህይወት ዝቅታና ከፍታ የምንማረው እጅግ ውድ የሆነ ትምህርት ይበቃኛል ማለትን ነው፡፡
ሰው ይበቃኛል የሚለውን ከተማረ በእውነት እጅግ ውድ የሆነ ትምህርት ቀስሟል ማለት ነው፡፡ ሰው በሚያልፍፈበት ነገር ውስጥ ሁሉ ይበቃኛል የሚለውን ካልተማረ ገና አልተማረም ማለት ነው፡፡
ሰው ሌላውን ለማገልገል ዝግጁ የሚሆነው ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡ ሰው ለሌላው የሚተርፈው ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡ ሰው ሌላውን የሚያገለግልበት ነገር የሚኖረው ይበቃኛል ሲል ብቻ ነው፡፡  
ሰው ራሱ ካላቆመው የሰው ልጅ ፍላጎት የማያልቅ እንደሆነ የሚረዳው ለመኖር ብዙ እንደማያስፈልገው ሲረዳ ብቻ ነው ፡፡ ሰው ከማያልቅ የሰው ልጅ የሩጫ ውድድር ራሱን የሚያገለው ለመኖር ብዙ እንደማያስፈልገው ሲረዳ ብቻ ነው፡፡ ሰው የዚህን አለም ፉክክር ከንቱነት የሚረዳውና ጌታን ለማገልገል ራሱን የሚሰጠው ያለኝ ይበቃኛል የሚለውን ሲማር ብቻ ነው፡፡
በእግዚአብሄር ዘንድ የተማረ የሚባለው ሰው ማግኘትም ማጣትም ምንም እንዳይደሉ የሚረዳ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሄር አይን የተማረ የሚባለው ማግኘትም ማጣትም ምንም ነገር እንደማያስችሉ የተረዳ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ የተማረ የሚያስብለው ማጣት ሁሉን ማድረግን እንደማይከለክል ማግኘት ሁሉን ማድረግን እንደማያስችል መረዳት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ የተማረ የሚያስብለው ያጣንም ሆነ ያገኘንም ሰው የሚያስችለው ማግኘታቸው ወይም ማጣታቸው ሳይሆን ክርስቶስ እንደሆነ መረዳት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የተማረ የሚባለው ክርስቶስ ሁሉን እንደሚያስችል የተረዳ ሰው ነው፡፡
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
ሰው የተማረ የሚያሰኘው ማግኘትንም ማጣትንም ትክክለኛ አቅማቸውን ማወቁ ነው፡፡ ሰው የተማረ የሚያሰኘው ለማግኘት ከሚገባው በላይ ትኩረት አለመሰጠቱ ነው፡፡ ሰው የተማረ የሚያሰኘው ማግኘትን ከአቅሙ በላይ ዋጋ አለመስጠቱ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማግኘት ሊያደርግ የሚችለውንና ሊያደርግ የማይችለውን ነገር ለይቶ መረዳት ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው የክርስቶስ ሃይል እንጂ ማግኘትም ሆነ ማጣት በህይወት ላይ ምንም እንደማይጨምሩ ማወቁ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማጣት በህይወት ላይ ምንም እንደማያጎድል መረዳቱ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማጣት ህይወታችንን ሊያበላሽ እቅም እንደሌለው መረዳቱ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው በህይወት ማጣት ከህይወት አላችን እንደማያግደንንና አቅምን እንደማያሳጣን ልኩን ማወቁ ነው፡፡ ሰውን የተማረ የሚያሰኘው ማጣትን ልኩን ማወቁና አለመፍራቱ ነው፡፡
የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡11-13
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መጥገብ #መራብ #መብዛት #መጉደል #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


Sunday, November 17, 2019

የማንጠቅም ባሪያዎች

እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። የሉቃስ ወንጌል 17፥10
አንዳንድ ጊዜ አገልግለን ሰጥተን ጠቅመን ነገር ግን መጨረሻ ላይ የምናፈርሰው በአመለካከታችን አለመስተከካል ምክንያት ነው፡፡
ሲጀመር አገልግሎት መስጠት መጥቀም የሚጀመረው ከእግዚአብሄር ነው፡፡ አገልግሎት መጥቀም መስጠት የሚጀመረው እግዚአብሄርን ከማመስገን ከምስጋና ልብ ነው፡፡
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡15
ለሌላው አገልግሎት መጥቀም መባረከ ለእኛ ለመገልገል ለመጠቀም ለመባረክ መሆን የለበትም፡፡ አገልግሎት መጥቀም መባረክ እኛ አስቀድመን በእግዚአብሄር ስለተገለገልን በእግዚአብሄር ስለተባረክንና በእግዚአብሄር ስለተጠቀምን ነው፡፡
አገልግሎት መጥቀም መባረክ ተደርጎልኛል ተቀብያለሁ ተሞልቻለሁ ከሚል ከምስጋና ልብ ካልመጣ ሙሉ ፍሬ አያፈራም፡፡
ሌላውን መጥቀም መባረከ እና ማገልገል ተደርጎልኛል ተባርኬያለሁ ተጠቅሜያለሁ ከሚል የምስጋና ልብ ከመጣ ውለታን ለመክፈል ይተጋል እንጂ ውለታ እንዲዋልለት አይጠብቅም፡፡
ተጠቅሜያለሁ ተባርኬያለሁ ተቀብያለሁ የሚል ሰው የሚያደርገውን ሁሉ በምስጋና ልብ ያደርገዋል እንጂ ስለሚያደርገው ማንኛውም ነገር ምስጋናን አይጠብቅም፡፡
እግዚአብሄር ለህይወቱ ሙሉን ዋጋ ከፍሎለት በከበረው በክርስቶስ ደም የገዛው ሰው ራሱን ሊሰጥ ሊያገለግል ጌታውን ሊያስደስት እንጂ ጎሽ እንዲባል እንዲጨበጨብለት አይጠብቅም፡፡
በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡12
ልጁን ኢየሱስን ከፍሎለት ከጥፋት ከሞት ከመቅበዝበዝና ከከንቱነት ያደነው ሰው ለጌታው የሚጠቅም እቃ በመሆኑ ብቻ ይደሰታል እንጂ ጌታው ስለተጠቀመበት ከጌታው ክፍያ እና ከሚያገለግለው ምስጋናን አይጠብቅም፡፡
ልጁን ኢየሱስን ከፍሎለት ለዘላለም ከእግዚአብሄር ከመለየት የዘላለም ሞት ያዳነው ሰው እግዚአብሄር ስለተጠቀመበት ብቻ ራሱን እንደ እድለኛ ያደርጋል እንጂ ስለተጠቀመበት ዋጋን አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ታዘዘኝ አገልግለኝ የሚለው ሰው በፊት ከሰይጣን ስልጣን በፊት የወደቀ ሰው ነበር፡፡
በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡1-2
ልጁን ከፍሎ ከጠላት መንግስት ያዳነው ሰው ወደ እግዚአብሄር አላማ በመመለሱ እና ጌታ ለአለማው ስለተጠቀመበት ብቻ ደስ ይለዋል አገልግሎቱንም በነፃ ይሰጣል እንጂ ስለመታዘዙ ክፍያን አይጠይቅም፡፡
እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1፡13-14
ልጁን ኢየሱስን በመስቀል ላይ ሰውቶ ያዳነው ሰው እግዚአብሄር ካልተጠቀመብኝ ለምንም የማልጠቅም ሰው ነበርኩ ብሎ ራሱን ያዋርዳል እግዚአብሄርም ስለተጠቀመበት ብቻ ደስ ይለዋል እንጂ እንደ እኩያ ስለደሞዝ ስለምስጋና ስለክብር አይደራደርምን፡፡
ከእግዚአብሄር በቀር በጎነት የለንም፡፡ የምንጠቅም ካደረገን እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሔርን፦ አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። መዝሙረ ዳዊት 16፡2
እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ። የሉቃስ ወንጌል 17፥10
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ#ዝቅታ ትህትና#ኢየሱስ #ጌታ#መሪነት #ቤተክርስትያን#አማርኛ #ስብከት#መዳን #መፅሃፍቅዱስ#መጋቢ #እምነት#ተስፋ #ፍቅር#ጌታ #ሰላም#ደስታ #አቢይ#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ#እወጃ #መናገር#ፅናት #ትግስት#መሪ

Wednesday, November 13, 2019

የምስራች!


የምስራች! 
የቀጥታ መልዕክት በኢትዮጲያ ሰአት አቆጣር ከሰአት በኋላ በ10 ሰአት

በግልጥ ይከፍልሃል


አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። የማቴዎስ ወንጌል 66
ከሚያስፈነቅዱኝ የእግዚአብሄር የተስፋ ቃሎእች አንዱ ይህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል የሚለው ቃል ነው፡፡
ወደ እግዚአብሄር መፀለይ እግዚአብሄር ትልቅ ስራን እንደሰራንለት ያህል ዋጋን እንዲከፍለን ያደርገዋል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ወደ ዕብራውያን 11፡6
በሁኔታዎች ውስጥ መፅናት ትልቅ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄርን ስንፈልግ እግዚአብሄር በፅናት ዋጋን ይከፍለናል፡፡
እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። መዝሙረ ዳዊት 105፡3-4
እግዚአብሄርን መፈለግ ብቻ እግዚአብሄር ዋጋ እንዲከፈለን ያስደርጋል፡፡
እግዚአብሄር መጠየቅ መለመንን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ለሚጠይቁት ለሚለምኑት መስጠት ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር የሚጠይቁትን የሚለምኑትን መልስ በመስጠት ደስ ይለዋል፡፡
እግዚአብሄር የሚለምኑትንና የሚጠይቁትን ከባለጠግነቱ በማካፈል ይደሰታል፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡12
እግዚአብሄርን ያየው ማንም የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው እንደሚል እግዚአብሄርን በትክክል ልቡን የሚተርክልን ኢየሱስ ነው፡፡ እግዚአብሄርን ልብ የምናየው በኢየሱስ ትምህርት ነው፡፡ እግዚአብሄርን ለልጆቹ ያለውን ልብ የምንረዳው በኢየሱስ እካሄድና ትምህርት ነው፡፡
ኢየሱስ ከተራራው ስብከት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ሰአት ድረስ ደቀመዛሙርቱ ወደደእርሱ ለሚፀልዩት ሰዎች ሁሉ ወደሚከፍለው እንዲፀልዩ በትጋት ያስተምር ነው፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የማቴዎስ ወንጌል 7፡7-8
ሰው የሚፀልየው ፀሎት ይታያል፡፡ ሰው በእልፍኙ የሚተጋው ትጋት ይታያል፡፡
ፀሎት አይደበቅም አይሰወርም፡፡ ፀሎት በክፍያ ይታያል ይገለጣል፡፡
የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። የሉቃስ ወንጌል 8፡17
በእልፍኙ እግዚአብሄርን የሚፈልግና ወደ እግዚአብሄር የሚፀልይን ሰው እግዚአብሄር በግልፅ ይከፍለዋል፡፡  
ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። የሉቃስ ወንጌል 12፡2-3
እግዚአብሄር ፀሎትን የሚከፍለው እንዳይሰወር በወዳጅም በጠላትም ፊት ለፊት በግልፅ ነው፡፡
በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። መዝሙረ ዳዊት 23፡5
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡6
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ለምኑ #ፈልጉ #አንኳኩ #ይቀበላል #ያገኛል #ይከፈትለታል #በግልፅ #ይከፍልሃል #ቃል #ብልፅግና #ሃብት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Tuesday, November 12, 2019

ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ፦ እጅ የለውም ይላልን? ትንቢተ ኢሳይያስ 45:9 ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን? ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? ወደ ሮሜ ሰዎች 9:20-21

ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ፦ እጅ የለውም ይላልን? ትንቢተ ኢሳይያስ 45:9
ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን? ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? ወደ ሮሜ ሰዎች 9:20-21

Monday, November 11, 2019

ሰባቱ የፆም ጥቅሞች



ፆም በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው፡፡ ፆም ለህይወታችን የሚጠቅመውን ነገሮች ከእግዚአብሄ ቃል እንመልከት
1.      ስጋ ያለልክ እንዳይጠግብ ይጠቅማል
ፆም እግዚአብሄርን የማይፈልገው የወደቀው የሃጢያት ማንነት እንዳያይል ስጋን ለመጎሸም እና ለእግዚአብሄር ፈቃድ ብቻ ለማሰገዛት ይጠቅማል፡፡
ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡27
2.     ፆም ስጋችን እንዳይከብደው ያደርጋል
ምግብን የማድቀቅ ስርአት በጣም ጉልበትን የሚጠይቅ ስርአት ነው፡፡ ሰውነታችን የምግብን ውህደት ሂደት የሚያካሂደው እንደትልቅ ፋብሪካ ነው፡፡ ከባድ ምግብ ልክ እንደበላን ድካም ድካም የሚለን ስለዚህ ነው፡፡
ፆም የሰውነታችንን ትልቅ የምግብ ማድቀቅ ስርአት ነፃ በመሆን ሰውነታችን ቀለል እንዲለውና እንድንነቃ በመንፈሳዊ ሁኔታ ላይ እንድናተኩር ይረዳናል፡፡  
3.     ፆም በመንፈሳዊ ነገር ላይ እንድናተኩር ይረዳል
ፆም  በማይታየው በእግዚአብሄር በአምልኮ ላይ እንድናተኩር ያደርገናል፡፡ ፆም ስጋችነነ ስለሚያደክመው የምድሩን ሳይሆን ቅድሚያ መስጠት ያለብንን ሰማያዊውን እንዳናስብ ይረዳናል፡፡
በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ። የሐዋርያት ሥራ 13፡1
4.     ፆም መንፈስ እንዲያሸንፍ ይረዳል
ፆም መንፈስን እንዲያሸንፍ መንፈስን ለመደገፍ ይጠቅማል፡፡ ፆም ስጋ እንዳያሸንፍ ለመጫን ይጠቅማል፡፡
ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡17
የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡24
5.     ፆም ለመንቃት ይጠቅማል
ብዙ ስንበላ እንቅልፍ እንቅልፍ ይለናል መንቃትም ይከብደናል፡፡ ብዙ ካልባለን ግን ነቅተን ስራችንን ማቀላጠፍ እንችላን፡፡
በጣም ብዙ በልቶ ከተኛ ሰው እና ጥቂት በልቶ ከተኛ ሰው መካከል ማነትው ንቁ እና ቶሎ የሚነቃው ብንል ትንሽ በልቶ የተኛው ሰው ነው፡፡ ብዙ ከጠጣውና ጥቂት ከጠጣው ሰው መካከል ማነው በቶሎ ሊነቃ የሚችለው ብለን ብንመለከት ጥቂት የጠጣው በቶሎ ነገሮችን ማስተዋል ወደ አእምሮው መመለስ እንደሚችል እናስተውላለን፡፡  
በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤  1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡8
6.     ስጋ ፍላጎቱ እንዲገደብ ያደርጋል
ስጋ በሰጠነው መጠን ሌላ ይጠይቃል፡፡ ስጋ ባሟላልነት መጠን የሚቀጥለውን ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ፆም ስንይዝ ስጋ በምግብ ጥያቄ ብቻ ላይ እንዲቆም እንገድበዋለን፡፡  
ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡23
7.     ፆም የስጋችንን ድምፅ በመቀነስ የመንፈስን ድምፅ እንድንሰማ ይረዳናል
ፆም የስጋን ድምፅ በመቀነስ የመንፈስ ድምፅ እንዲያይል ለማድረግ ይጠቅማል፡፡
እግዚአብሄር በመንፈሳችን አማካኝነት ሁልጊዜ ፈቃዱን ይናገራል፡፡ የመንፈስን ድምፅ ለመስማይት የሚያስፈልገውን ነገር ማድረግ ያለብን እኛ ነን፡፡ ስጋውን እንደፈለገ የሚመግበው ሰው የመንፈስን ድምፅ ለመስማት ይቸግረዋል፡፡ በፆም የስጋውን ድምፅ የሚያዳክም ሰው ግን የመንፈስን ድምፅ በጥራት መስማት ይችላል፡፡
እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡6
በፀሎት እግዚአብሄርን ይበልጥ መስማት የምንችለው ስንፆም ነው፡፡
ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡8
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ፆም #ፀሎት #ስጋ #መንፈስ #ነፍስ #እምነት #ሃሳብ #ጥበብ #ማስተዋል #አምልኮ #መስማት #ጥበብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #እምነት #ቃል  #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ