ክርስትና ከሚታወቅበት ልዩ ባህሪዎች አንዱ ሚዛናዊ የሆነንን ህይወት መምራት ነው፡፡ክርስትያን በደስታም የሚያከብረው እግዚአብሔርን ነው፡፡ ክርስትያን በደስታም ከልክ አያልፍም፡፡ ክርስትያን ደስታውና ዘና ማለቱ ሃጢያት እስኪያሰራው አያደርሰውም፡፡ ክርስትያን በነገሮች ያለመጠን አይፈነጥዝም ደስታውን ሁሉ በልክ ያደርጋል፡፡
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29-31
ክርስትያን በሃዘንም እግዚአብሔርን ነው የሚያየውም የሚያከብረውም እግዚአብሔርን ነው፡፡ ክርስትያን ሃዘኑም ለሞት የሚያደርስ ራስን የሚያስጥል ከመጠን ያለፈ አይደለም፡፡
የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡10
ክርስትያን አገኘሁ ብሎ ብዙ አይበላም ራስን በመግዛት ራሱን ያዝ ያደርገዋል፡፡ ክርስትያን አገኘሁ አገኘሁ ብሎ ብዙ አይጠጣም፡፡ ክርስትያን ለመንቃት የሚያደክመውን ካለልክ እንዲዝናና የሚያደርገውን ኑሮ ይሸሻል፡፡ ክርስትያን ለመንቃትና ሳያቋርጥ ለመፀለይ ስለሚፈልግ እንቅልፍ እንቅልፍ የሚያስብለውን የሚያደክመውን ከመጠን ያለፈ ኑሮ አይኖርም፡፡
ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ ሮሜ 13፡11-13
በመጠኑ መኖር በመንፈስ ለመንቃት ይጠቅማል፡፡ መንቃት ደግሞ ለመፀለይና ይጠቅማል፡፡ በመጠኑ መኖር ላለመዘናጋት ነቅቶ ለመፀለይ ይጠቅማል፡፡
በመጠኑ ኑሩ ንቁም፥ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያጋሳ አንበሳ ይዞራልና፤1ኛ ጴጥሮስ 5፡8
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ምልጃ #ምስጋና #ውዳሴ #በመጠኑ #እንደፈቃዱ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment