መፅሃፍ ቅዱስ ነፍስ ያለእውቅት ትሆን ዘንድ መልካም
አይደለም ሲል የአእምሮ እውቀትን ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ስለመፅሃፍ ቅዱስ ብዙ የአእምሮ እውቀት አላቸው ነገር ግን
እውቀቱ ለህይወት ለውጥ ምንም አይጠቅማቸውም፡፡ የአእምሮ እውቀት በተግባር ሊተረጎም የማይችል ውስን እውቀት ነው፡፡ የአእምሮ እውቀት
መፅሃፍ ቅዱስን እንደማንኛውም መፅሃፍ በመሸምደድ የሚገኝ እውቀት ነው፡፡ የአእምሮ እውቀት መፅሃፍ ቅዱስን እንደ ታሪክና ፊዚክስ
በማጥናት የሚገኝ ውስን እውቀት ነው፡፡
የአእምሮ እውቀት ብቻ ነፃ አያወጣም፡፡ ነፃ የሚያወጣው
የመገለጥ እወቀት ነው፡፡ ሰው ያለው የአእምሮ እውቀት ይሁን ወይም የመገለጥ እውቀት የሚፈተነው የሚያውቀውቅን በመተግበሩና ባለመተግበሩ
ነው፡፡ የአእምሮ እውቀት ያለው ሰው የሚያውቀውን ማድረግ አይችልም፡፡ ስለአንድ ነገር ያለህ እውቀት ነገሩን እንድታደርገው ካላስቻለህ
ያለህ የአእምሮ ብቻ እውቀት ነው፡፡
ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል። ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን
ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል። ያዕቆብ 1፡22-25
የአእምሮ እውቀት ብቻ ያለው ሰው የመገለጥ እውቀት
እንዳለው ሰው ልቡ ሰፊ አይደለም፡፡ የአእምሮ እውቀት ያለው ሰው ደካማን ከማገዝ ይልቅ ርህራሄ ስለሚጎድለው በደካማ ሰው ላይ በጭካኔ
ይፈርዳል፡፡ የመገለጥ እውቀት ያለው ሰው ግን በቤተሰብነት ስሜት ሌሎችን ይረዳል ያነሳል፡፡ የአእምሮ እውቀት ብቻ ያለው ሰው ፊደሉን
ብቻ ነው የሚያወቀው፡፡ የመገለጥ እውቀት ያለው ሰው የሚያስችለው ሃይል መንፈሱም ያውቀዋል፡፡
እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡6
የአእምሮ እውቀት ያለው ሰው ስለእግዚአብሄር ያለው
እውቀት የሰሚ ሰሚ እውቀት አለው፡፡ የመገለጥ እውቀት ያለው ሰው እግዚአብሄር ራሱን ያውቀዋል፡፡ የአእምሮ ብቻ እውቀት ብቻ ያለው
ሰው እውቀቱ የሚቆመው በአእምሮ ብቻ ነው እንጂ ከህይወቱ ጋር አልተዋሃደም፡፡
ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ዕብራውያን 4፡2
የመገለጥ እውቀት ያለው ሰው ቃሉ በህይወቱ ተዋህዶታል፡፡
የአእምሮ እውቀት ብቻ ያለው ሰው የሚመራው በአእምሮው ብቻ ነው፡፡ የመገለጥ እውቀት ያለወ ሰው የሚመራው በልቡ መንፈስ ነው፡፡
እርሱም የላከውን እናንተ አታምኑምና በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም።
እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም። ዮሃንስ 5፡38-40
የአእምሮ እውቀት ያለው ሰው እውቀት ያለው ይመስለዋል
ግን ያለው ተግባራዊ እውቀት ስላልሆነ ለተግባራዊው እውቀት ራሱን ይዘጋል፡፡ የአእምሮ እውቀት ያለው ሰው ያወቀ እየመሰለው ራሱን
ያታልላል፡፡ የመገለጥ እውቀት ያለው ሰው እግዚአብሄርን በሙላት አገልግሎ ያልፋል፡፡
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ
ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። ዮሃንስ 6፡63
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እውቀት #ጥበብ #ነፍስ
#መዳን #ኢየሱስ
#ጌታ #እግዚአብሔር
#መገለጥ #እውቀት
#ቅድሚያ #መታዘዝ
#ርስት #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#ባለጠግነት #መፅሃፍቅዱስ
#መጋቢ #እምነት
#ሃይል #ጥሪ
#ክብር #ሰላም
#ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#አእምሮ #ሰላም
#ማስተዋል #ልጅ
No comments:
Post a Comment