ሰሞኑን
ወደ ኬንያ እንግዳ ወሬ ተሰምቶዋል፡፡ የነበረውን የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ውጤት በተመለከተ የኬንያ ፍርድ ቤት ያልተለመደ አንድ ውሳኔ
አስተላልፎዋል፡፡ በውሳኔውም የኬንያ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ የጉድለት እንደነበረውና የነበረው የፕሬዝዳንት አመራረጥ ዲሞክራሲያዊ ነፃና
ፍትሃዊ መንገድን አካሄድ ያልተከተለ አልነበረም በማለት የምርጫው ውጤት ውድቅ እንዲሆንና አዲስ ምርጫ በ 60 ቀን ውስጥ እንዲካሄድ
ወስኖዋል፡፡
ይህ
የዲሞክራሲ አንዱ ምልክት ነው፡፡
ዲሞክራሲ
ከሚታወቅባቸው ነገሮች አንዱ ሶስቱ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጪ ምክር ቤቶች ፣ ህግ ተርጉዋሚው ፍርድ ቤት እና ህግ አስፈፃሚው
የመንግስት አካል እርስ በእርሳቸው መፈታተሻቸው ፣ መጠበባበቃቸውና አንዱ የሌላው ሚዛን መጠበቃቸው ነው፡፡
መንግስት
አንድ ወጥ ቢሆን ስልጣኑን ያለአግባብ ቢጠቀም የሚመለከተው ክፍል እየኖርም፡፡ መንግስት በሶስት ክፍሎች በህግ አውጪ ፣ በህግ ተርጉዋሚና
በህግ አስፈፃሚ ባይከፋፈል በህዝብ ላይ ሃይሉን ያለአግባብ ሊጠቀም
ይችላል፡፡ መንግስት አንድ ወጥ ከሆነና በሶስቱ የመንግስት ክፍሎች ካልተከፋፈለ የመንግት አካሎች እርስ በእርሳቸውን የሚቆጣጠሩበት
መንገድ አይኖርም፡፡ መንግስት አንድ ወጥ ከሆነና በመንግስት አካሎች ካልተከፋፈለ በስተቀር አንዱ የመንግስት አካል ህግ ማውጣቱንም
፣ ህግ መተርጎሙንም ሆነ ህግ ማስፈፀሙንም ራሱ ካደረገው ስልጣኑ ካለአግባብ ቢጠቀም የሚያየው የሚከታተለውና የሚቆጣጠረው አካል
አይኖርም፡፡
ለምሳሌ
አንዱ የመንግስት አካል አስፈፃሚው ክፍል ወይም ፖሊስ አንድን ሰው ራሱ ከከሰሰ ፣ ያው ፖሊስ የከሰሰውን ሰው ራሱ ከፈረደበትና
ያው ፖሊስ ፍርዱን ከፈፀመበት ዲሞክራሲ ሳይሆን አምባ ገነንነት ነው፡፡
አንድ
ፖሊስ ሰውን ጠረጠረ ወይም ከሰሰ ማለት መንግስት ጠረጠረው ወይም ከሰሰው ማለት አይደለም፡፡ አንድ ፖሊስ ሰውን ጠረጠረ ማለት አንዱ
የመንግስት አካል ብቻ ጠረጠረው ማለት ነው፡፡ ፖሊስ እንደ ህግ አስፈፃሚነቱ ሰውን ጠረጠረ ወይም ከሰሰ ማለት ከሰሰ ወይም ጠረጠረ
ማለት ብቻ እንጂ ሰው ተፈረደበት ማለት አይደለም፡፡ ፖሊስ አስፈፃሚነቱን ስልጣኑን አልፎ ሌላ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡
ፖሊሱ ሊያደርግ የሚችለው ብቸኛ ነገር ህግ ተርጓሚው ፍርድ ቤት ጋር ማቅረብ ነው፡፡
ፍርድ
ቤቱ ደግሞ ስራው ህጉን መተርጎም ነው፡፡ ህጉምን በመተርጎም ይህን ሰው ያስጠይቀዋል ወይስ አያስጠይቀውም የሚለውን የሚስነው ፍርድ
ቤቱ ነው፡፡ ስለዚህ በፍርድ ቤቱ ፊት ፖሊስም ተጠርጣሪው እኩል ናቸው፡፡ ሰው በፍርድ ቤት ተከራክሮ ጥፋተኛ እስካልተባለ ድረስ
በደለኛ አይደለም፡፡ ፖሊስም ተጠርጣሪው ሰውም ስለህጉ አተረጓጎም እኩል ይከራከለራሉ፡፡ ህግ አስፈፃሚው ፖሊሱና ተከሳሹ በህግ ተርጓሚው
ፊት እኩል ናቸው፡፡ ህግ አስፈፃሚው እንደ መንግስር ሳይሆን እንደ አንድ የመንግስት አካል ክፍል ተጠርጣሪውን የሚቀርበበው ሌላው
የመንግስት አካል ክፍል ጋር ነው፡፡
ህግ
አውጪው ምክር ቤት እንዲሁ ህግ የማውጣት ስራውን በነፃነት ይሰራል፡፡ ነገር ግን ህግ አውጪ እንጂ ህግ ተርጉዋሚም ሆነ ህግ አስፈፀጻሚ
አይደለም፡፡ ህግ አውጪው ህግ በማውጣት ብቻ ህግ ተርጓሚውንም ሆነ ህግ አስፈፃሚውን ይፈትሻቸዋል ሚዛናቸውን ይጠብቃል፡፡
ፍርድ
ቤቱም እንዲሁ የራሱ ስልጣን እንዲሁም ለስልጣኑ የራሱም ገደብ አለው፡፡ ፍርድ ቤቱ ስልጣኑ እና ሃላፊነቱ በህግ አውጪው የተሰጠውን
ህግ መተርጎም ነው፡፡ ነገር ግን ህግ ተርጓሚው ፍርድ ቤት ህጉን መተርጎም እንጂ የሌሎቹን የመንግስት አካላት የህግ አውጪውንም
ሆነ የህግ አስፈፃሚነትን ስራ አይሰራም፡፡ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ህጉን በመተርጎሙ ሂደት የህግ አስፈፃሚው ሆነ የህግ አውጭው ምክር
ቤት ጣልቃ አይገቡበትም፡፡ ህግ ተርጉዋሚውም ህግ አውጭውንና ህግ አስፈፃሚውን ድንበራቸውን እንዳይስቱና ካለአግባብ በስልጣናቸው
እንዳይጠቀሙ ህጉን በመተርጎምና በመወሰን ይጠብቃቸዋል፡፡
መንግስት ሃይሉን ካለአግባብ እንዳይጠቀም በሶስት
ዋና ዋና የመንግስት ክፍሎች በህግ አውጪ ምክር ቤት ፣ በህግ ተርጓሚ ፍርድ ቤትና በህግ አስፈፃሚ ተከፋፍሏል፡፡ አንዱ የመንግስት
ክፍል ሌላው የመንግስት ክፍል ከስልጣን ከድንበሩ እንዳያልፍ ይጠብቀዋል ይፈትሸዋል ይቆጣጠረዋል፡፡ አንዱ የመንግስት አካል የሌላውን
የመንግስት አካል ሚዛን ይጠብቃል፡፡
በኬንያ የሆነውም ነገር ይህ ነው፡፡ ስለምርጫው
ውዝግብ ሲነሳ አንዱ የመንግስት አካል ህግ ተርጉዋሚው ጋር በመድረሱ ህግ ተርጉዋሚው በህጉ መሰረት ያልተገበሩ ነገሮች አሉ በማለት
የምርጫውን ውጤት ውድቅ ከማድረጉም በላይ በ60 ቀን ውስጥ አሰዲስ ምርጫ እንዲደረግ ወስኖዋል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ፖለቲካ #ፀሎት #ፍርድቤት #ህግአውጪ
#ህግአስፈፃሚ #ምክርቤት #ፖሊስ #ዲሞክራሲ #ህግተርጉዋሚ #ተቃውሞ #ሃዘን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ወንጌል #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment