የአእምሮ እውቀት ብቻ በራሱ መጥፎ ባይሆንም እንደመገለጥ እውቀት የሰውን ህይወት አይለውጥም፡፡ ህይወታችን በመገለጥ እውቀት ካልተለወጠ ደግሞ እግዚአብሄር በምድር ሰርተን አንድናልፍ ያዘጋጀልንን መልካሙን ስራ ፈፅመን ልናከብረው አንችልምን፡፡ የአእምሮን እውቀት የምናገኘው መፅሃፍ ቅዱስን በማንበብ ብቻ ነው፡፡ የመገለጥ እውቀት ግን መፅሃፍ ቅዱስን በማንበብ ብቻ ወደእኛ ሊመጣ አይችልም፡፡ በህይወታችን የመገለጥ እውቀትን ሊያመጡ የሚችሉትን ነገሮች ካደረግን የመገለጥ እውቀት ወደ ህይወታችን ይመጣል በዚያም ህይወታችን ይለወጣል፡፡ እኛ የመገለጥ እውቀት እንድናገኝ ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር የመገለጥ እውቀት እንድናገኝ ይፈልጋል፡፡
የመገለጥ እውቀት ለማግኘት የመጀመሪያው ደረጃ ዳግመኛ መወለድ ነው፡፡ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር ምንም ስለ ኢየሱስ በታሪክ ቢያውቅ እግዚአብሄርን ግን ሊያውቀው አይችልም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችን ሆና ሳለ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያያት አይችልም፡፡
ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ዮሃንስ 3፡3
የመገለጥ እውቀት ለማግኘት ራስህ ትሁት በማድረግ ባወቅነው እውቀት እርምጃ መውሰድን ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሄር የመገለጥ እውቀት የሚሰጠን እንድንኩራራበት ሳይሆን እርሱን አንድንታዘዘውና ለክብሩ እንድንኖር ነው፡፡ እግዚአብሄር የመገለጥ እውቀት ከመስጠቱ በፊት ባለን እውቀት ምን ያህል ታማኞች እንደሆንንና እንደታዘዘነው ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ፍላጎታችን እግዚአብሄርን ለመታዘዝ ካልሆነ እግዚአብሄር የመገለጥ እውቀት ለእኛ በመስጠት እውቀትን አያባክነውም፡፡
በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። ሉቃስ 8፡15
የመገለጥ እውቀት ለማግኘት ቃሉን ማሰላሰል ወሳኝ ነው፡፡ ለቃሉ የመጀመሪያውን ስፍራ መስጠታችን ቃሉን እንድናሰላስለው ያደርገናል፡፡ በዚህም በቃሉ ውስጥ ያለውን ጭማቂ ማግኘት እንችላለን፡፡ የአእምሮ እውቀት ከእኛ ጋር የሚዋሃደውና የሚጠቅመን ለቃሉ የመጀመሪያውን ስፍራ በህይወታችን ስንሰጥና ቃሉን እንደ ባጣ ቆየኝ ካላየነው ነው፡፡ የአእምሮ እውቀት ከእኛ ጋር በእምነት የሚዋሃደው ቃሉን ስናከብርና ቃሉን ሰናሰላስለው ነው፡፡
ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም። ዕብራውያን 4፡2
የመገለጥ እወቀት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ፊት በመፈለግ ነው፡፡
የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ኤፌሶን 1፡17
ፀሎት
እግዚአብሄር አባት ሆይ ስለህይወቴ አመሰግንሃለሁ፡፡ በምድር ላይ የሰጠኸኝን ስራ ሰርቼ ላከብርህ እፈልጋለሁ፡፡ ህይወቴ እንዲለወጥ በሁለንተናዬ ክርስቶስን እንድመስል እፈልጋለሁ፡፡ ብዙዎችን የሚነካ እና የሚደርስ ህይወት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ ህይወቴን የሚለውጠውን ይህን የመገለጥ እውቀት እንድስትሰጠኝ እለምንሃለሁ፡፡ ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እውቀት #ጥበብ #ነፍስ #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #መገለጥ #እውቀት #ቅድሚያ #መታዘዝ #ርስት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ማሰላሰል #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ቅድሚያመስጠት #ጥሪ #ክብር #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #አእምሮ #ሰላም #ማስተዋል #ልጅ
No comments:
Post a Comment