ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን
ከሙታን ለማውጣት ነው። ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡6-10
እግዚአብሄር ሰውን ያውቀዋል፡፡ እግዚአብሄር የሃጢያትን
እዳ ሁሉ በኢየሱስ ከከፈለ በኋላ ሰው ግን ላለመዳን ምክኒያት እንደሚፈልግ ያውቀዋል፡፡ ሰው ቀላል የሆነውን ነገር እንዴት እንደሚያወሳሰብና
የማይቻል እንደሚያደርገው እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ስለዚህ ነው እንዲህ ተብሎ የተፃፈው፡፡
በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ
ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል ሮሜ 10፡6-7
ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ፣ ከዘላለም ፍርድ
መዳን ፣ የዘላለም ህይወት ማግኘት ከባድ አይደለም፡፡ መዳን የአመታት ስራ አይጠይቅም፡፡ መዳን የአመታት ጥረት ፣ ትጋትና ጉስቁልና
አይጠይቅም፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያት እዳችንን ሁሉ ስለከፈለ ለመዳን የሚጠበቅብን ነገር የደህንትን ነፃ ስጦታ በእምነት
መቀበል ብቻ ነው፡፡
የቃሉ ማስጠንቀቂያ እነዲህ ይላል መዳን እንደ
ሰማይ የራቀ ነው አትበል፡፡ እንዲሁም መዳን እንደ ጥልቅ ሩቅ ነውም አትበል፡፡ ለመዳን ሰበብ አይኑርህ፡፡ ላለመዳን የምታቀርበው
ማንኛውም ምክኒያት በቂ አይደለም፡፡ ላለመዳን የምታቀርበው የቱም ምክኒያት ሰንካላ ምክኒያት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያታችንን እዳ ሁሉ ፈፅሞ ከከፈለ በኋላ ላለመዳን ለምናቀርበው ማንኛውም ምክኒያት ጆሮ የለውም፡፡
እግዚአብሄር መዳንን እጅግ አቅርቦታል፡፡ ለመዳን
እጅግ ዋጋ ቢከፈለምና መዳን እጅግ የላቀ ዋጋ ያለው ቢሆንም እግዚአብሄር ለእኛ ግን መዳንን ቀላል አድርጎታል፡፡
በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ሮሜ
10፡8
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም
ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ኢየሱስን እንደአዳኝና ጌታ አሁኑኑ መቀበል ከፈለጉ
ይህን ፀሎት አብረው ይፀልዩ
እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በኢየሱስ የሃጢያቴን
እዳ ሁሉ ስለከፈለክ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስለሰጠኸኝ የደህነት ነፃ ስጦታ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እመሰክራለሁ፡፡ እግዚአብሄር
ከሙታን እንዳስነሳው በልቤ አምናለሁ፡፡ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት
#ደህንነት #ነፃስጦታ
#ፀጋ #ሞት
#የዘላለምህይወት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ቃል
#ፍጥረት #ልጅነት
#ብትመሰክር #እምነት
#አምባሳደር #ብርሃን
#ብታምን #ልጅነት
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment