1. በ 2010 ዓመተ ምህረት በእምነት ለማደግ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማድረግ፡፡ አዲስ ኪዳንን ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ማንበብ ወይም በድምፅ መስማት ውሳኔዬ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ቆላስይስ ሰዎች 3፡16
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
2. በ 2010 ዓመተ ምህረት ለእግዚአብሔር ቤት ስራ ለቤተክርስትያን ስራ በተጨማሪ ገንዘብ በመስጠት የእግዚአብሄርን መንግስት የማገለግልበትን መንገድ መፈለግ ውሳኔዬ ነው፡፡
ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል። እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም። 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡6-7
3. በ 2010 ዓመተ ምህረት እግዚአብሄርን ከቅዱሳን ቃል ለማምለክ ፣ ለመፀለይ ፣ የእግዚአብሄርን ቃል ለመማር እንዲሁም ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር ህብረት ለማድረግ ለቅዱሳንን ህብረት ይበልጥ ራሴን መስጠትና ለመትጋት ውሳኔዬ ነው፡፡
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ዕብራዊያን 10፡24-25
4. በ 2010 ዓመተ ምህረት በጉልበቴ በእውቀቴ በገንዘቤና በጊዜዬ ደከመኝ ሳልል የእግዚአብሄርን ህዝብ ለማገልገል ወስኛለሁ፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡10
አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር። ሮሜ 12፡7-8
5. በ 2010 ዓመተ ምህረት እግዚአብሄር በግል ህይወቴ የተናገረኝን ለመፈፀም የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ውሳኔዬ ነው፡፡
ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ። ቆላስይስ 4፡17
6. በ 2010 ዓመተ ምህረት እግዚአብሄር በህይወቴ ያለውን አላማ በሙላት መፈፀም እችል ዘንድ በግል የፀሎት ጊዜዬ ጌታን ለመስማትና ለመታዘዝ ዘወትር የጥሞና ጊዜ ለመውሰድ ውሳኔዬ ነው፡፡
እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። ሐዋርያት 13፡2
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#አዲስፍጥረት #አዲስ #ፀሎት #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ንስሃ #አምልኮ #መታዘዝ #ህብረት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አገልግሎት #መናገር #የእግዚአብሄርአላማ #ሰላም ትግስት #ውሳኔ
No comments:
Post a Comment