በአዲስ አመት አብዛኛው ሰው ለሌላው መልካም ነገርን
ይመኛል፡፡ በጎን ፈቃድ መግለፅና ለሌላው በጎውን መመኘት መልካም ነው፡፡ መልካም መመኘት ለሌላው ያለንን መልካም ፈቃድ ለማሳየት
እጅግ ይጠቅማል፡፡
እንደ መንፈሳዊ ሰው ደግሞ መልካም እንደምንመኝላቸው
ሁሉ ጊዜ ወስደን እንፀልይላቸዋለን ወይ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት
ይገባናል፡፡
የምንወዳቸውን የምናከብራቸውን ወዳጆቻችንን መልካም
ልንመኝላቸው ብቻ ሳይሆን ልንፀልይላቸው ይገባል፡፡
የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
ያዕቆብ 5፡16
በአዲስ አመት ልንፀልይላቸው የሚገባ
1.
ለወንድሞችና ለእህቶች
ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ
ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16
2.
ለቤተክርስትያን መሪዎች
ወንድሞች ሆይ፥ ስለ እኛ ጸልዩ። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡25
አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ የሚችል የለምና። 2ኛ ዜና መዋዕል 1፡10
3.
ጌታን ለማያውቁ ሰዎች
ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።
ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡2-4
4.
ለወንጌል ሰራተኞችና ለሚሽነሪዎች
ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤ ኤፌሶን 6፡19
በዚያን ጊዜም ስለ እርሱ ደግሞ የታሰርሁበትን የክርስቶስን ምሥጢር እንድንነግር እግዚአብሔር የቃሉን ደጅ ይከፍትልን
ዘንድ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ ቆላስይስ 4፡3
5.
ለመንግስት ባለስልጣናት
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና
ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞቴዎስ
2፡3-4
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ
#ፀሎት #ልመና
#ምልጃ #ምስጋና
#ውዳሴ #ተቃውሞ
#እንደፈቃዱ #መጠየቅ
#መንበርከክ #ይቃትታል
#መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል
#መፅሃፍቅዱስ #ሰላም
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment