I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
የሚበድል ሰው ያልገባው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የተሳሳተው ነገር አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጎደለው እውቀት አለ፡፡ የሚበድል ሰው የጠፋበት መንገድ አለ፡፡ የሚበድል ሰው የሚያደርገውን ...
-
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። ወደ ሮሜ ሰዎች 12፡16 ሃጢያት ያታልላል፡፡ ...
-
1. ለጭንቀት የእግዚአብሄር ፅድቅና መንግስቱን ለመፈለግ በቀን 24 ሰአት 7 በሳምንት ሰባት ቀን አለን፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን ከመፈለግ የሚተርፍ እና ለጭንቀት የሚሆን አንድ ...
-
ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል ! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው። ምሳሌ 16፡16 ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤ በወርቅና ...
-
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ዘካርያስ 4:6 v አንድን ነገር እ...
-
… From Oppressive Obligations to Incredible Opportunities The phone isn’t just ringing, it seems to be screaming. You’ve got yet another...
Tuesday, May 30, 2023
Sunday, May 28, 2023
የፀሎት መሰረት
ፀሎት ከእግዚአብሄር የተሰጠ ታላቅ እምቅ ጉልበት
ያለው ውጤታማ መንፈሳዊ ስራ ነው፡፡
የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
የያዕቆብ መልእክት 5፡16
ውጤታማ ፀሎትን ለመፀለይ መረዳት ያለብንን ነገሮችን
ከእግዚአብሄር ቃል እንመለከታለን፡፡
በመጨነቅ ምንም ውጤት ስለማናመጣ ከመጨነቅ ይልቅ
ብንፀልይ ለጭንቀት የምናወጣውን ጉልበት ለፀሎት ብንጠቀምበት ህይወታችን ፈፅሞ ይለወጣል፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡6
በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት የምናምን ሁላችን
የልጅነት ስልጣን ተሰጥቶናል፡፡
ፀሎት ከአባት ጋር የሚደረግ የልጅ ንግግር ነው፡፡
ፀሎት የልጅነት መብት ነው፡፡ እግዚአብሄር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ በኩል ልጆቹ አድርጎናል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
እግዚአብሄር ተቀብሎናል፡፡ እግዚአብሀር ዙፋን
ፊት ቀርበት ጉዳያችንን የማስፈፀም መብት ተሰጥቶናል፡፡
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 4፡16
በክርስቶስ የመስቀል መስዋእትነት በኩል እግዚአብሄር
በክርስቶስ ባለነው በእኛ ደስተኛ ነው፡፡
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት
ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡17
ካለበታችነት ስሜት ካለፍርሃት እና ካለመሸማቀቅ
በእግዚአብሄር ፊት ለመቅረብ የእግዚአብሄር ፅድቅ ሆነናል፡፡
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን
ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡21
ውጤታማ ፀሎት የሚጀምረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ
ከማወቅ ነው፡፡
በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
የፀሎት ትልቁ ክፍል ስላለንበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን
ፈቃድ መፈለግ እና ማወቅ ነው፡፡ ውጤታማ ፀሎት የሚጀምረው ስላለንበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከእግዚአብሄር ቃል ፈልጎ ከማግኘት
ነው፡፡ በፀሎት ለእግዚአብሄር መናገር የሰከንዶች ስራ ነው፡፡ ትልቁን
ጊዜያችንን የሚወስደው ስለምንፀልየው ነገር ከእግዚአብሄር ቃል መረዳትን ማግኘት ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡17
በእርሱ
ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን
ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
ፀሎት
የሚጀምረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ያገኘን ጊዜ ነው፡፡ የእግዚአብሄን ቃል እያጠናን መረዳቱ ሲመጣልን ልንፀልይ እና ሊመለስልን ይችላል፡፡
ስንፀልይ
በምስጋና መፀለይ አለብን
ስንፀልይ
እግዚአብሄር አባታችን እንደሆነ መልካም እንደሚያደርግልን ከዚህ በፊት መልካም ሲያደርግልን እንደቆየ በምስጋና ልብ መፀለይ አለብን፡፡
እግዚአብሔር
እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።
ወደ
ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙረ ዳዊት 100፡4
ስንፀልይ
በእረፍት መፀለይ አለብን
አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። የማቴዎስ ወንጌል 6፡7-8
ስንፀልይ
የፀሎት ርእሱን ለመናገር መቸኮል የለብንም፡፡ ስንፀልይ ለጌታ ካልነገርነው አያውቅም በሚል አስተሳሰብ መፀለይ የለብንም፡፡
ስንፀልይ
በእግዚአብሄር መንፈስ በመደገፍ መፀለይ ውጤታማ ያደርገናል፡፡ በአእምሮዋችን ያለውን ፀሎት ሳይሆን ጌታ አሁን እንድንፀልይ የሚፈልገውን
መፀለይ ውጤታማ ያደርገናል፡፡ አሁን በእውነት የሚያስፈክገንን ለመፀለይ በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ በፀሎት ቦታችን ልባችንን መስማት
አለብን፡፡ መንፈስ ሲመራን በአእምሮዋችን የሌለውን ነገር ወደ ልባችን ያመጣዋል፡፡ አንዳንዴ ለራሳችን ልንፀልይ ብለን ለሌሎች እንድንፀልይ
ይመራናል፡፡
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡26-27
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
Friday, May 26, 2023
የፀሎት ያለህ !
ስለአንድ ነገር ውጤታማ ለመሆን የእግዚአብሄርን
ልብ ማግኘት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም ይለናል፡፡ ነገር ግን
በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እንደተረከው መፅሃፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሄርን ልብ ሊተርክ የሚችል ኢየሱስ ነው፡፡
መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።የዮሐንስ ወንጌል 1፡18
ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ባለጠግነት ያውቃል፡፡
ኢየሱስ እግዚአብሄር ለህዝቡ ያለውን የአባትነት የፍቅር ልብ ያውቃል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ህዝብ ምን ያህል በፀሎት ሊጠቀም
እንደሚችል ያውቃል፡፡
ሰው ግን የእግዚአብሄርን ልብ ካልተረዳ በእጦት
ውስጥ ሊኖር እንደሚችል ደግሞ የሰውን ሁኔታ ያውቃል፡፡ ሰው በፀሎት ጠይቆ መቀበል ሲችል በእጦት ሊሰቃይ እንደሚችል የሚያውቀው
ኢየሱስ በብዙ ቦታ ስለፀሎት በተደጋጋሚ ተናግሮዋል፡፡ የእግዚአብሄርን ልብ የሚያውቀው ኢየሱስ ሰው በፀሎት የእግዚአብሄርን ባለጠግነት
መካፈል እንደሚችል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲያበረታታ እንመለከታለን፡፡
ከእነዚህ ጥቂት ጥቅሶች እግዚአብሔር ስለፀሎት
ያለውን የእግዚአብሄርን ልብ እንመለከታለን፡፡
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 16፡24
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። የዮሐንስ ወንጌል 16፡23፡7-8
በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። የዮሐንስ ወንጌል 16፡24
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7
ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። የማርቆስ ወንጌል 11፡24
ከኢየሱስ ትምህርት እና ህይወት እግዚአብሄር የሰውን
ፀሎት ለመመለስ ያለውን የቅናት ልብ በቀላሉ እንመለከታለን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
Thursday, May 25, 2023
ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም
ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:16
ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:2
ከሰው
ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ለማድረግ ሰውን ማወቅ ወሳኝ ነው፡፡ ሰው ማነው? የሚለውን ጥያቄ በሚገባ የመመለስ ሸክም አለብን፡፡ ሰውን
በሚገባ ካላወቅነው እንደሚገባ አብረን ልንኖር አንችልም፡፡
ሰውን
ለማወቅ ባለን ጥረት ሰውን በተለያየ መመዘኛ ለማወቅ እንጥራለን፡፡ ስለሰው ስናስብ በተፈጥሮ እነዚህ የሰው መመዘኛዎች ወደ አእምሮዋችን
ይመጣሉ፡፡
ማነው
? ምን ይሰራል ? የት ይኖራል ? ገቢው ምንድነው ? በማህበረሰብ ውስጥ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው ? ተምሮዋል ወይስ
አልተማረም ? ሃያል ነው ደካማ ? ባለጠጋ ነው ደሃ ? የኑሮ ደረጃም ዝቅተኛ ከፍተኛ መካከለኛ ነው ? የአገሬ ሰው ነው አይደለም
? ላምነው እችላለው ? ልደገፍበት እችላለሁ ?
እነዚህን
እና የመሳሉትን ጥያቄዎች የመመለስ ሸክም በእኛ ላይ ወድቆብናል፡፡
ችግሩ
ደግሞ እነዚህን ጥያቄዎች በትክክል መመለሳችን ሰውም በሚገባ እንድንመዝነው በቂ አይደሉም፡፡ በእነዚህ መመዘኛዎች ሰውን መዝነን
ከጨረስን በኋላ ልንሳሳት መቻላችን የሰውን አመዛዘን ውስብስብ ያደርገዋል፡፡
እነዚህ መመዘኛውዎች በእግዚአብሄር መልክ እና አምሳል የተፈጠረውን ሰው ለመመዘን ብቁዎች አይደሉም፡፡
ሰዎች
ሰውን በተለምዶ የሚመዝኑባቸው መመዘኛዎች ሰውን በብቃት ለመመዘን ብቁ እንዳልሆኑ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
እነዚህ
መመዘኛቸው የራሳቸው ጉድለት ስላለባቸው ሰው ራሱንም ሆነ ሌላውን ሰው በእነዚህ መመዘኛዎች በመመዘን ሊሳሳት ይችላል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 9፡23-24
ጠቢብነት ሃያልነት እና ብልጥግና የሰውን የወደፊት ስኬት እንደማይወስኑ መፅሃፍ ቅዱስ ግልፅ አድርጎታል፡፡ ሰው ጠቢብ መሆኑ እና አለመሆኑ የሚያስመካም
የሚያዋርድም ነገር አይደለም፡፡ ሰው ሃያል መሆኑ እና ደካማ መሆኑ ከቁጥር የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ ሰው ባለጠጋ መሆኑ እና አለመሆኑ
የህይወት ስኬት ቁልፍ መያዙን ወይም አለመያዙን አያሳይም፡፡
ምክኒያቱም እነዚህ የምድር መመዘኛዎች የሰውን ስኬት እና ውድቀት ሊመሰክሩ የሚችሉ
ብቁ ምስክሮች ስላይደሉ ነው፡፡
የሰውን
ትክክለኛ ዋጋ ሊያሳየን የሚችለው እግዚአብሄ ብቻ ነው፡፡ የሰውን ትክክለኛ ደረጃ ልናይ የምንችለው ሰውን በእግዚአብሄር ስናየው
ብቻ ነው፡፡ ሰውን በትክክል የምናየው በእግዚአብሄር ፍጥረትነቱ ስናየው ብቻ ነው፡፡ ሰውን ከእግዚአብሄር ፍጥረትነቱ ባነሰ መመዘኛ
መዝነነው ልናውቀው በፍፁም እንችልም፡፡ ሰውን በእግዚአብሄር መመዘኛ በተለየ መልኩ በስጋ መዝነነው እንሳሳታለን እንጂ ትክክል ልንሆን
እንችልም፡፡
የሰውን
ትክክለኛ ደረጃ ማወቅ የምንችለው እግዚአብሄር እንደሚያይ ስናየው ብቻ ነው፡፡
እኛም
እንደሰባኪው ወደእውነቱ መመለስ አለብን፡፡
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መጽሐፈ መክብብ 9፡11
ሰውን በሰውኛ መመዘኛ መመዘን የሰውን ዋጋ ሊያረጋግጥ አይችልም፡፡
ሰውን
በትክክል ልንመዝን የምንችለው በክርስቶስ ስንመዝነው ብቻ ነው፡፡ ሰውን በክርስቶስ ማየት ካልቻልን ትክክለኛ ደረጃውን ማወቅ ይሳነናል፡፡
ሰው ከክርስቶስ ውጭ በስጋ መዝነን በትክክለኛ ማንነቱ ልናውቀው እና እንደሚገባ ልንይዘው እንችልም፡፡
ስለዚህ
እኛም ተመልሰን ሰውን በስጋ ላለማወቅ እስካልወሰንን ድረስ የሰውን እውነተኛ ዋጋ መረዳት ያቅተናል፡፡ ተመልሰን ሰውን በክርስቶስ
ለማየት ካልወሰንን በስተቀር ሰውን መረዳት በፍፁም አንችልም፡፡
ስለዚህ
እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ
ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
Matrimonial Earthly Mission
Understanding God's special
purpose in marriage from God's word is crucial. Achieving the purpose of
marriage's first establishment by God himself is an unparalleled life
responsibility.
Marriage is God's design.
Marriage is not man made. Marriage wasn’t established as a solution to a human
problem. Marriage is an original plan of God that was planned in connection
with the creation of man. Marriage was instituted as soon as human beings were
created.
God believes in marriage. God
believes that two different people, two upbringings, two cultures, two
families, a man and a woman, united in love, can reflect God's love to the
world through marriage. God believes that marriage works. God prepared every
provision for marriage and gave marriage to people. God gave marriage Marriage
is a gift from God.
God gave grace and love to human
beings so that marriage could work. God gave everything needed for marriage to
flourish and achieve the purpose it was originally created for.
Marriage is God's very own idea,
and God will always fully support marriage in every way. Man should humble
himself before God's idea, for God will support marriage with all his might.
Man shouldn’t reject God's idea of marriage out of selfishness. As long as man
cooperates with God in humility, God supports his own institution, marriage,
with everything he has.
This is the written account of
Adam’s family line. When God created mankind, he made them in the likeness of
God. He created them, male and female, and blessed them. And he named them
"Mankind" when they were created. Genesis 5:1-2
The purpose of marriage is to
show and reflect the full image of God in the characteristics of strength and
tenderness of the husband and wife, respectively.
God created man and woman in his
own image. Both males and females reflect the full image of God.
A man reflects God's strength,
discipline, and leadership, while a woman reflects God's compassion, love,
forgiveness, and care. The full image of God in man and woman is reflected in
the union of marriage.
It is the marriage of husband and
wife that fully reflects God.
The marriage of a man and a woman
is a reflection of the relationship and unity of Christ and the Church as well.
After all, no one ever hated
their own body, but they feed and care for their body, just as Christ does the
church— for we are members of his body. "For this reason a man will leave
his father and mother and be united to his wife, and the two will become one
flesh." This is a profound mystery—but I am talking about Christ and the
church. Ephesians 5:29-32
God is a God of purpose. Marriage
has its own purpose on earth.
Marriage speaks of God's presence
in silence.
Marriage speaks of God's love in
silence.
Marriage speaks of God's patience
in silence.
Marriage silently speaks of the
unity of Christ and the church.
Satan opposes anything that
speaks of God and reminds us of God’s existence. This is why Satan seeks to
destroy the full image of God found in marriage.
Satan knows that there is only a
short time left to destroy this image of God from the face of the earth. He is
out to erase the image of God reflected in marriage from the face of the earth
in great anger. Christ defeated Satan on the cross. He will not succeed in
destroying God's male and female images reflected in marriage as long as we
humbly work with God to honour his institution of marriage.
In the midst of a generation that
doubts and denies the existence of God, we show our love for God's existence
when we treat our marriage as God's mission. We shouldn’t lose a sense of
mission in marriage.
We use the marriage that God has
given us to carry out our mission for the kingdom of God and reflect the
relationship and unity of Christ and the church. We glorify God among a
generation that doubts the existence of God and the true church of Jesus
Christ.
Abiy Wakuma Dinsa
Wednesday, May 24, 2023
የትዳር የምድር ተልእኮ
Tuesday, May 23, 2023
The Secret Instead
Man
is created in the image of God. Man can only succeed by teaming up with God. A
man can’t be neutral. You can’t be successful in Christian life without action.
Even
when the Bible tells you not to do something, it also tells you what to do
instead. You can’t be ideal. You can’t be neutral. Instead of worrying, pray.
You have to channel the energy of worry into that of prayer. You can’t just
block the energy without rechanneling it in the right direction.
Don’t
worry about anything; instead, pray about everything. Tell God what you need,
and thank him for all he has done. Philippians 4:6
You
can’t protect yourself from sin by doing nothing instead. No. You substitute
sin with righteousness. You were created to do something, not to be ideal.
Do
not offer the parts of your body to sin, as instruments of wickedness, but
rather offer yourselves to God, as those who have been brought from death to
life, and offer the parts of your body to him as instruments of righteousness.
Romans 8:13
Whether
you want to be filled is out of the question. The question is, "What will
you be filled with?
And
be not drunk with wine, wherein is excess; but be filled with the Spirit, and
be not drunken with wine, wherein is riot, but be filled with the Spirit;
Ephesians 5:18
The
channel can’t be empty. It must be filled and occupied with something. Take
advantage of it to fill it with the right material. You can’t just not think
about sin; you have to actively think about the word of God and meditate upon
it.
Do
not conform to the pattern of this world, but be transformed by the renewing of
your mind. Then you will be able to test and approve what God’s will is—his
good, pleasing, and perfect will. Romans 12:2
You
can’t just avoid conforming to the pattern of the world unless you actively
renew your mind. You can’t just succeed in not having the mind of the flesh
without doing something about it. You have to have the mind of a spirit.
Those
who live according to the flesh have their minds set on what the flesh desires;
but those who live in accordance with the Spirit have their minds set on what
the Spirit desires. Romans 8:5
You
can either use the spirit or the flesh. You can’t have none of them.
Abiy
Wakuma Dinsa
Terms and conditions apply
Terms and conditions apply.
God is a God of covenant. God has been seeking to give himself in covenant relationships throughout human history. God always gives his word to people. He wants to work with people in a partnership. He promised the people his full support in return for their seeking the advancement of his kingdom. One of the terms and conditions of the partnership agreement between God and man is his provision for those who seek him and the well-being of his kingdom. God promised to provide the condition of seeking the kingdoms of God and His righteousness first. Making the kingdom a priority secures God's provision. This is one of the fundamental terms of the kingdoms in which God provides for his children in Jesus Christ. Without properly understanding the term, we don’t succeed in achieving significant achievements in the kingdom of God.
But seek first his kingdom and his righteousness, and all these things will be given to you as well. Matthew 6:33
Abiy Wakuma Dinsa
Saturday, May 20, 2023
ፍጹማን ሁኑ
ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 5:43-48
ኢየሱስ እንዲህ አለ " እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ "
እነዚህን ቃል የተናገረው እኛን የሚያውቀን ኢየሲስ ነው፡፡ ፍፁማን ሁኑ ብሎ ያዘዘን
ምን እንደሰጠን በሚገባ የሚያውቀው ጌታ ኢየሱስ ነው፡፡ ይህን ያዘዘው አፈጣጠራችንን ድካማችንን ብርታታችንን ሁሉ ጠንቅቆ የሚያውቀው
እግዚአብሔር ነው፡፡
እግዚአብሔር ሲናገር ከልቡ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለቀልድ አይናገርም፡፡
እግዚአብሔር ካዘዘ ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር የማይቻል ነገር አያዝም፡፡
ስለእኛ ሊመሰክር የማይችለውን የሚሰማንን ስሜት ትተን እንደታዘዝነው ፍፁማን እንሁን፡፡
ዙሪያችን የሚሰማውን የአካባቢያችንን ድምፅ ትተን ፍፁማን ሁኑ የሚለውን የጌታን ቃል
እንታዘዝ፡፡
ሰው
ብዙ ነገር ብሎ ሊሳሳት ይችላል፡፡ ሰው ግን እግዚአብሄር ያለውን ብሎ አይሳትም፡፡ እንደተሳሳትን ቢሰማንም እንኳን እግዚአብሔር
የሚለውን በድፍረት እንበል፡፡
ፍፁም
መሆን እችላለው ማለት ትእቢት ሳይሆን ትህትና ነው፡፡ እንዲያውም ትእቢት የሚሆነው ፍፁም መሆን አልችልም ማለት ነው፡፡ ፍፁም መሆን አልችልም ማለት እግዚአብሄር ያዘዘው ነገር መፈፀም የማይቻል
ነገር ነው ብሎ እግዚአብሔርን እንደማማት ይቆጠራል፡፡
ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡ 30-31
ባይገባንም
ባንረዳውም እንኳን እግዚአብሔር ያለውን አሜን እሆናለሁ ብሎ እንደመቀበል ያለ ነገር የለም፡፡
የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።
አሜን ፍፁም እሆናለሁ፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር
ኤልሳዕም።
ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ አለው፤ ቀስቱንና ፍላጻዎችንም ወሰደ። የእስራኤልንም ንጉሥ። እጅህን በቀስቱ ላይ ጫን አለው። እጁንም ጫነበት፤ ኤልሳዕም እጁን በንጉሡ እጅ ላይ ጭኖ። የምስራቁን መስኮት ክፈት አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም። ወርውር አለ፤ ወረወረውም። እርሱም። የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው፤ በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያዊያንን በአፌቅ ትመታለህ አለ። ደግሞም። ፍላጻዎቹን ውሰድ አለው፤ ወሰዳቸውም። የእስራኤልንም ንጉሥ። ምድሩን ምታው አለው። ሦስት ጊዜም መትቶ ቆመ። የእግዚአብሔርም ሰው ተቆጥቶ። አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ኖሮ ሶርያን እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ አለ። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 13:18-18
ይህ የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል የሚያስተምረን የእስራኤል
ንጉስ በነቢዩ አማካኝነት ስለደረሰው የውጊያ ስልት መልእክት ነው፡፡ ንጉሱ በነቢዩ ተመርቶ በምሳሌነት ሶስት ጊዜ ብቻ ፍላፃውን
እንደወረወረ እና እንዳቆመ ከዚህ ክፍል እንመለከተታለን፡፡ እግዚአብሄር ግን በነቢዩ በኩል ሲናገረው ሶስት ጊዜ ብቻ ባትመታ ኖሮ
ጠላቱን ፈፅሞ ያጠፋ እንደነበር መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
ይህ ክፍል የሚያስተምረን ጠላትን ፈፅመን እንድንመታ
ነው፡፡ ብንሰንፍ እና ጠላትን ፈፅመን ለመምታት ቸል ብንል ጠላታችንን ፈፅመን በመምታት ሙሉ ድልን እንዳናገኝ የማግኘት እድላችንን
በከንቱ እናባክነዋለን፡፡
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። የሉቃስ ወንጌል 10፡19
በተለይ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የዲያቢሎስን ስልጣን
ገፎታል፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችል ላደረግነው በጠላት ላይ ስልጣን ተሰጥቶናል፡፡
አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡15
ጠላትን መቃወም እና የጠላትን ምርኮ ፈፅመን
መበዝበዝ አለብን፡፡ ነገር ግን ጠላትን ተዋግተን ለማሸነፍ ቸል ብንል እንደሚገባን ማሸነፍ እንደማንችል እና የድሉን አክሊን መጎናፀፍ
እንደማንችል መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። የማርቆስ ወንጌል 3፡27
እና ጦርነትን እንዳካሄደ እና ነገር ግን የሚገባውን
ያህል በጠላቱ ላይ ስላልጨከነ የሚገባውን ያህል ድል እንዳላገኘ ከዚህ ክፍል እንማራለን፡፡
በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 610-12
በህይወታችን ዲያቢሎስን መቃወም አለ፡፡ ዲያቢሎስን
ፀንቶ መቃወም ደግሞ አለ፡፡ ሙሉ ድል የሚያስገኘው ዲያቢሎስን ፀንቶ መቃወም ብቻ ነው ፡፡
በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡9
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa