ፍጹም
ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡18
ፍቅር
ከእምነት ይመነጫል፡፡ ፍርሃት ደግሞ ከጥርጥር ይመነጫል፡፡
ፍቅር
ሁሉን ያምናል፡፡
ፍቅር
ሁሉን ያምናል፡፡ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡7
ፍቅር
እና ፍርሃት አብረው አይሄዱም፡፡ ፍቅር ካለ ፍርሃት ለቆ ይወጣል፡፡ ፍርሃት ካለ ደግሞ ፍቅር በሙላት የለም ማለት ነው፡፡ የፍርሃት
መኖር የፍቅር መጉደል ትክክለኛ ማስረጃ ነው፡፡ ፍርሃት ካለ ፍቅር ሙሉ አይደለምና የፍቅር ችግር ሊፈተሽ ይገባዋል፡፡
ፍቅር
ነፃነት ነው፡፡ ፍርሃት ባርነት ነው፡፡ ነፃነትና ባርነት አብረው እንደማይኖሩ ሁሉ ፍቅርና ፍርሃት አብረው ሊኖሩ አይችሉም፡፡
ፍርሃት
ራሱን ይሰስታል፡፡ ፍቅር ራሱን ይሰጣል፡፡
በህይወታችሁ
የምትፈሩት ነገር ካለ በዚያ አቅጣጫ ጥርጥር አለባችሁ ማለት ነው፡፡ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ በዚያ አቅጣጫ እምነት ጎድሏችኋል
ማለት ነው፡፡ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ ስለዚያ ነገር እግዚአብሄርን አላመናችሁም ማለት ነው፡፡
በህይወታችሁ
የምትፈሩት ነገር ካለ በዚያ አቅጣጫ የሚመራችሁ ፍቅር ሳይሆን ፍርሃት ነው ማለት ነው፡፡ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር ካለ ቅጣትን
ትፈራላችሁ ማለት ነው፡፡
ፍቅር
ብርሃን ነው፡፡ በፍቅር የሚያስፈራ ምንም ነገር የለም፡፡ ፍቅር ንፁህ ነው፡፡ ንፅህና ድፍረትን ይሰጣል እንጂ አያሳቅቅም አያስፈራም፡፡
ፍቅር ሙሉ ነው፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን
ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ
#ጌታ #ፍቅር #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፍርሃት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ
No comments:
Post a Comment