ፀሎትን ውጤታማ የሚያደርገው ለቅሶዋችን አይደለም፡፡
እውነት ነው ስንፀልይ አንዳንድ ጊዜ ስሜታዊ እንሆንና እናለቅሳለን፡፡ ነገር ግን የፀሎት ውጤት ከለቅሶ ጋር የሚያገናኘው ምንም
ነገር የለም፡፡
ፀሎታችንን ውጤታማ የሚያደርገው መርዘሙ አይደለም፡፡
እውነት ነው አንዳንድ ጊዜ ፀሎታችን ይረዝማል፡፡ አንዳድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ ከጌታ ጋር እንነጋገራለን፡፡ ፀሎታችን መርዘሙ ብዙ የፀሎት
ርእሶችን ለመፀለይ ካልሆነ በስተቀር ፀሎታችን እንዲሰማ ወይም ፀሎታችን ፍሬያማ እንዲሆን የሚጠቅመው ጥቅም የለም፡፡
ፀሎታችንን ውጤታማ የሚያደርገው ነገርን መደጋገማችንም
አይደለም፡፡ ተመሳሳይን ነገር በደጋገምነው መጠን ፀሎታችን ይሰማል ብለን ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ እውነት ነው ፀሎትን ስንፀልይ ልባችን
እስኪያርፍ ድረስና ሸክማችን እንከሚቀል ድረስ መፀለይ አለብን፡፡ ነገር ግን የፀሎት ርእሳችንን በደጋገምነው መጠን ፀሎታችን ይሰማል
ብለን ማመን የለብንም፡፡
ፀሎትን ውጤታማ የሚያደርገው ስንፀልይ በምናሳየው
ሃይል አይደለም፡፡ ፀሎታችን እንዲሰማ የሚያደርገው በድምፃችን ከፍታ መጠን ወይም በጣም በመወራጨታችን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር
የልብን ጩኸት ይሰማል፡፡
ፀሎትን ውጤታማ የሚያደርገው ስንናገረው ስላጣፈጥነው
አይደልም፡፡ ፀሎታችን እንዲሰማ የሚያደርገው አንደበተ ርቱእ መሆናችን አይደለም፡፡
ፀሎታችን እንዲሰማ የሚያደርገው እንደ ፈቃዱ መፀለያችን
ነው፡፡ እንደ ፈቃዱ ከፀለይን እግዚአብሄር ይሰማናል፡፡ እንደ ፈቃዱ ካልፀለይን እግዚአብሄር አይሰማንም፡፡
የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምናገኘው በእግዚአብሄር
ቃል ውስጥ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሄር ቃል ከፀለይን እግዚአብሄር ይሰማናል፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ካልፀለይን እግዚአብሄር
አይሰማንም፡፡
በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን
ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡14-15
በእኔ
ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። የዮሐንስ ወንጌል 15፡7
ይህን
ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና
No comments:
Post a Comment