Popular Posts

Friday, October 4, 2024

ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ክፍል 4

 

 

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖርልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2  

እንደ ክርስትያን የምንደግፈው እና የምንቃወመው የፖቲካ ድርጅት ሊኖር ይችላልየምንደግፈውም የምንቃወምውም እግዚአብሄር በቃሉ ያዘዘንን ትእዛዝ የማይቃወም መንገድ መሆን ይኖርበታል 

በስልጣን ላይ ያለውን መንግስትንም ሆነ ተቃሚውንም በፖለቲካች የማይደግፍም የማይቃወምም ክርስትያን ደግሞ ሊኖር ችላል 

ያም ሆን ይህ እንደ ክርስትና በየጊ ለሚለዋወጡት ለመንግስቱ ባለስልጣናት የማይጸልይ ክርስትያን ሊኖር ግን አይባው 

መንግስት የሰው ቋም አይደለም መንግስት የእግዚአብሄር ቋም ነው።  የማንንም ፖለቲካ ባንደግፍም የእግዚአብሄርን ስርዐት መደገፍ ግን አለብን 

የማንንም ፖለቲካ ብንቃውምም የእግዚአብሄርን አስራር ቃወም ብንም 

ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምናያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማልየሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉወደ ሮሜ ሰዎች 13:1-2 

የማንንም ፖለቲካ ብንቃውምም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ ባለመጸለይ እግዚአብሄርን እንድንጸልይለት የሰጠንን ህዝብም እንዲሁም ራሳችንን በደ የለብንም  

እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖርልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2  

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

#ጸጥ #ዝግ #እግዚአብሔርንመምሰል #ፀሎት #ኢየሱስ #ጌታ #ምልጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ምስጋና #እምነት #ነገስታት #መኳንንት #አማርኛ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ኢትዮጲያ #ፖለቲካ #መንግስት  

No comments:

Post a Comment