በዛሬው እለት አሜሪካ በፕሬዝዳንትነት የሚመራትን መሪ ትመርጣለች፡፡ ይህ ምርጫ የአሜሪካን የአመቱን ዜና ሽፋን የያዘ ነው፡፡ በዛሬው እለት ደግሞ በመላው አለም ርእሰ ዜና ሆኖ ይውላል፡፡
በክርስትናም አንዲሁ ርእሰ ዜናም ባይሆኑ በዝምታ በየእለቱ የምንመርጣቸው የህይወትና የሞት ምርጫ የሆኑ ምርጫዎች አሉ፡፡ በየእለቱ የምንመርጣቸው ህይወታችንን ሊያሳድጉ ወይም ሊያጎለብቱ የሚችሉ ምርጫዎችን እንመልከት፡፡
- · በኢየሱስ የተከፈለልንን የሃጢያት ዋጋ ለእኔ ነው ብሎ በመቀበልና በራስ ችሎታ በስራ ለመፅደቅ የመሞከር ምርጫ
በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ገላትያ 5፡4
- · በእግዚአብሄር ምህረትና በእግዚአብሄር ቁጣ ስር የመኖር ምርጫ
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
- · ወደጌታ መጥቶ ማረፍና ራስ የመሸከም ምርጫ
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። ማቴዎስ 11፡28-30
- · በስጋና በመንፈስ ሃሳብ መካከል ያለ ምርጫ
ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። ገላቲያ 5፡16-17
- · ለጌታና ለገንዘብ በመገዛት መካከል ያለ ምርጫ
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ማቴዎስ ወንጌል 6፡24
- · ፍቅርን የመከታተልና በጥላቻ የመኖር ምርጫ
ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡13 ፣ 14፡1
- · ራስን መካድና ራስን ያለመካድ ምርጫ
ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።ሉቃስ 9፡23
- · በመጨነቅና ጭንቀትን በጌታ ላይ የመጣል ምርጫ
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡7
- · ነፍስን መያዝና ነፍስን የመተው ምርጫ
ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል። ሉቃስ 9፡24
- · እግዚአብሄርን የማመንና የጥርጥር ምርጫ
ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐንስ 14፡1
- · ራስን የማዋረድና በትእቢት የመኖር ምርጫ
እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
- · ስለስጋ ማሰብና ስለመንፈስ የማሰብ ምርጫ
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ሮሜ 8፡5-6
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ምርጫ #ምስክር #ፀጋ #ምናን ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment