ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ። ቲቶ 2፡11-15
ፀጋ ምንድነው ብለን ብንጠይቅ አብዛኛው ሰው ነፃ ስጦታ ነው ብሎ እንደሚመልስ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ዛሬ ግን የተለየ ትርጉሙን እንመለከታለን፡፡
ፀጋን የሚያስችል ሃይል ፣ ለሰው በነፃ የተሰጠ የእግዚአብሄር ችሎታ እና የእግዚአብሄር ብቃት በማለት መተርጎም እንችላለን፡፡
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ያለፈውን ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና በሃጢያታችን እንድንቀጥል አይደለም፡፡
ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ሃጢያታችንን ይቅር ሊለን ከአሁን በኋላ በእግዚአብሄር ፀጋ በሃጢያት ላይ የበላይ ሆነን እንድንኖር በሃይል ሊያስታጥቀን ነው፡፡ ፀጋ በህይወታችን ያስፈገበት ምክኒያት ከሃጢያት የበላይ ሆንን እንድንኖር ሊያበረታን ነው፡፡
- · ፀጋ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን እንድንኖር ያበረታናል፡፡
ሃጢያትን መካድ ቀላል አይደለም፡፡ ከዓለማዊ ምኞት የበላይ ሆኖ ጌታን ማክበር በእኛ የእግዚአብሄር ችሎታ መገለጥን ይጠይቃል፡፡ የፀጋም አላማ እኛን በማበርታት ኃጢአተኝነትና አለማዊ ምኞት በእኛ ላይ ጉልበት እንዳይኖራቸው ማድረግ ነው፡፡
- · ፀጋ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ጉልበት ይሆነናል፡፡
አንዳንድ ሰዎች ስለመዳንም ሆነ ስለመቀደስ ሲያስቡ ሰማይ እስከሚሄዱ የማይሆንና በምድር ላይ የማይሳካ አድርገው ያስባሉ፡፡ መጽፅሃፍ ቅዱስ ግን በዚህ ዘመን ኢየሱስ ሳይመጣ የኢየሱስን መምጣት እየተጠባበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንድንኖር ፀጋው እንደሚያችለን ያስተምራል፡፡
ምክኒያቱን ሲናገር ኢየሱስ ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን እንደሰጠ ይነግረናል፡፡ የኢየሱስ ሞት አላማው እኛን በፀጋው ሃይል በማስቻል ከአመፃ የነፃን እግዚአብሄርን ለማገልገል የሚቀናን ህዝብ ማፍራት ነው፡፡
ይህ ጸጋ ተገልጦአል፡፡ ማንም ላለመዳን ፣ ራሱን ላለመግዛት ፣ በፅድቅ ላለመኖርና እግዚአብሄርን ላለመምሰል ሰበብ የለውም፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ
No comments:
Post a Comment