Popular Posts

Follow by Email

Thursday, November 3, 2016

ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23
መፅሃፍ ቅዱሳችንን ስናጠና በጣም የሚያስደንቀንና የሚያስገርመን ነገር በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን ቦታ እጅግ የከበረ እንደሆና እኛ ራሳችንን እንደምናየው እግዚአብሄር እኛን እነደማያየን ነው፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለንን ቦታ በትክክል የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
በእግዚአብሄር ዘንድ ያለንን ስልጣን የምንጠቀምበት በመናገር እንደሆነ ኢየሱስ ያስተምራል፡፡ በክርስቶስ የዳነ ሰው ቃል ስልጣን አለው፡፡ በክርስቶስ ያለ ሰው በቃሉ ያለው ስልጣን አስደናቂ ነው፡፡
ማንም ያለው እንዲደረግለት በማለት በእግዚአብሄር ዘንድ ያለን የልጅነት ስልጣንና ቦታ እጅግ ልዩ እንደሆነና መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ ማንኛውም ነገር ንግግራችንን እንደሚያከብርና ለቃላችን እንደሚገዛ ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ ያስተምራል፡፡ ንግግራችን ግን የእምነት ንግግር መሆን እንዳለበት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ የእምነት ንግግራችን ተራራን መንቀል የሚችል ጉልበት አለው፡፡
ንግግራችን ሁኔታችንን የመለወጥ ውጤት እንዳያመጣ የሚያደርገው የልብ ጥርጥር እንደሆነም ይነግረናል፡፡ ንግግራችን በልብ ጥርጥር ከሆነ አይሰራም፡፡ ቃላችን ግን በልብ በእምነትና ጥርጥር የሌለበት ከሆነ ንግግራችን ነገራችንን ይለውጣል፡፡ ነገራችን ቃላችንን ከመታዘዝ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡
ስለ ሁኔታችን የማንጠራጠረው ደግሞ እምነት ሲኖረን ነው፡፡ እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሄር ቃል ከመስማት ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
ስለምናገረውን ነገር እምነት የሚኖረን የእግዚአብሄር ቃል ስለሁኔታው ምን እንደሚል ፈልገን ስናገኝ ነው፡፡ ስለሁኔታችን ከእግዚአብሄር ቃል የእግዚአብሄርን ፈቃድ ካገኘን እምነት ይኖረናል፡፡ በእምነት የምንናገረው ነገር ደግሞ ሁኔታችንን ይለውጣል፡፡ ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment