Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, November 9, 2016

6ቱ በሰው የመታመን ምልክቶች

እግዚአብሄር ቀናተኛ አምላከ ነው፡፡ በእርሱ ላይ እንጂ በማንም ላይ እንድንደገፍ አይፈልግም፡፡ በእግዚአብሄር ላይ ካለን መታመን ተመልሰን በሌላ በማንም ሰው ላይ እንድታመን ጌታ አይፈልግም፡፡ በእግዚአብሄር ያለንን መታመን በምንም ነገር እንድለውጠው እግዚአብሄር አይፈልግም፡፡
ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ። መዝሙር 146፡3 በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። መዝሙር 118፡8
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል። በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። ኤርምያስ 17፡5-7
በሰው ላይ መታመንና በእግዚአብሄር ላይ መታመን የልብ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው መታመኑ በሰው ላይ ይሁን ወይም በእግዚአብሄር ላይ ለማወቅ የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች መመልከት ራስን ለመመርመር ይረዳል፡፡ አምስቱን በሰው ላይ የሚታመን ሰው ምልክቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
  • · ክብርን ወይም እድገትን የሚጠብቀው ከሰው ነው
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤ መዝሙር 75፡6 ብዙ ሰዎች የሹምን ፊት ይሻሉ፤ የሰው ፍርድ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ምሳሌ 29፡26
  • · ሰውን ይፈራል
ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።ምሳሌ 29፡25
  • · በሚያጋጥመው ሁኔታ ከመፀለይና እግዚአብሄርን ከመፈለግ ይልቅ ከሰው ጋር መጨቀቃጨቅና መጣላት ይቀለዋል፡፡
በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ያዕቆብ 4፡1-2
  • · ከመጠን ያለፈ ከሰው ስለሚጠብቅ በሰው ይሰናከላል
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡29
  • · የሚኖረው ለታይታ ነው
ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ። ቆላስይስ ሰዎች 3፡22
  • · ሰውን ሲያጣ እግዚአብሄርን እንዳጣ ይሰማዋል፡፡
ሰውም ሁሉ ይዋረዳል፥ የሰውም ኵራት ይወድቃል፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል። እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል? ኢሳያስ 2፡17፣22
ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም። ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፤ በኃይሉም ብዛት አያመልጥም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በምሕረቱም ወደሚታመኑ፥ ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፥ በራብም ጊዜ ይመግባቸው ዘንድ። ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና። ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና። አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን። መዝሙር 33፡16-22
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #መታመን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment