ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል
ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማቴዎስ 16:26
ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር መልክና አምሳል
ነው፡፡ ሰው ክቡር ነው፡፡ የሰው ፍላጎት በሚበላው በሚጠጣው እና በሚለብሰው ነገር አይሟላም፡፡ የሰው ፍላጎት ከፍ ያለ ነው፡፡
ሰው በስጋ ውጥ የሚኖር መንፈስ እንደመሆኑ መጠን
ነፍሱ አምላክ ትፈልጋለች፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን እንዲያምልክ ተደርጎ ስለሆነ የሰው ነፍስ ሁልጊዜ የምታምነው የምትደገፈውን
አምላክ ትጠማለች፡፡
የሰው ነፍስ የምትሰማውን የምትከለተለውን አምላክ
ትናፍቃለች፡፡
የሰው ነፍስ ከእግዚአብሄር አምላክ ውጭ ምንም
እንዳያረካት ተደርጋ ስለተፈጠረች በምንም በሌላ ነገር አትረካም፡፡ የሰው ነፍስ ይህን የአምላክነት ፍቅር የሚተካ ምንም ማስመሰያ
ተመሳሳይ ነገር ቢቀርብላት አትረካም፡፡
የሰው ነፍስ የሚወዳትን እና የምትወደውን አምላክ
ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ የምትከተልውንና የምትኖርለትን አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ ፍቅር የምትሰጠውን እና የምትቀበለውን
አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ ራስዋን መስዋእት የምታደርግለትን ከእርስዋ ከፍ ያለ አምላክ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ ለምን
እንደምትኖር እውነተኛውን የኑሮን ትርጉም ማወቅ ትፈልጋለች፡፡ የሰው ነፍስ አስፈላጊ መሆንዋን የሚያሳያት ፣ የሚያደንቃት ፣ የሚወዳት
እና ዋጋን የሚሰጣት አምላክ ትፈልጋለች፡፡
ለነፍሳችን ሁሉን ነገር አድርገንላት እውነተኛውን
እና ዋነኛውን ጥማትዋን እና ረሃብዋን ካላረካንላት ምን ይጠቅማታል? ለነፍሳችን ተመሳሳዩን ነገር ሁሉ ሰጥተናት እውነተኛውን ዋናውን
ነገር ካልሰጠናት ምን ይጠይቅማታል?
No comments:
Post a Comment