Popular Posts

Thursday, August 11, 2022

ውሸት ይለምድብሃል!



ልጆች ሆነን ወላጆቻችን አትዋሽ ውሸት ይለምድብሃል ይሉን ነበር፡፡ እውነት ነው ካልተጠነቀቅን ህይወታችን ውሸት እና ሃጢያትን ይለምዳል፡፡

1. በዋሸህ ቁጥር ውሸቱን ለመሸፈን ብዙ ሌሎች ውሸትን ለመጨር ትገደደዳለህ፡፡ አንዱ ውሸት ከሌላው ጋር እንዳይጋጭ እና ውሸቱ እንዳይታወቅብህ አላስፈላጊ ጭንቅ ውስጥ ትገባለህ፡፡

ሃጢያትም እንደዚሁ ብቻውን አይመጣም፡፡ ሃጢያት ብቻውን አይሰራም፡፡ አንድ ሃጢያት በብርሃን የማይሰራ ጨለማ ነውና እርሱን ሃጢያት ለመሸፈን ሌላ ሃጢያት ያሰራሃል፡፡ ሃጢያት በጨለማ ብቻ ሊሰራ የሚችል ነውና ሃጢያት የህይወት ድፍረትህን ይመታዋል፡፡ ሃጢያት በሰውም በእግዚአብሄርም ፊት ያለህን ድፍረትህን ይጎዳዋል፡፡

 ኀጥእ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል።መጽሐፈ ምሳሌ 281

2.  በዋሸህ ቁጥር ውሸት እንደሚሰራ ስለምታስብ ብዙ ውሸት ለመዋሸት ትደፋፈራለህ፡፡ ከፋም ለማም ውሸት ውጤት ያስገኛል፡፡ ሰውነትህ ሳያውቀው በውሸት ያገኘኸውን ውጤት እንደ ስኬት ይቆጥረዋል፡፡

በሃጢያት በትእቢት ያገኘኸውን ነገር ሰውነትህ በስህተት እንደ ድል ይቆጥረዋል፡፡ ሳታስበው ሰርቶልኛል ብለህ ራሱን ክፉውን ነገር ለማድረግ ትፈተናለህ፡፡ ሳታውቀው ክፉው ነገር የህይወትህ ስርአት ይሆንሃል፡፡

በተቃራኒ ፅድቅን እውነተኝነትን ማድረግ ስትጀምር ሳታውቀው ቀስ በቀስ የህይወትህ ልምምድ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ። 1 ወደ ጢሞቴዎስ 47

3. የውሸት ፍላጎት በአንድ አያበቃም፡፡ ሰውነትህ አንድ ጊዜ ብቻ ዋሽተህ አምልጥ የሚልህ መጀመሪያ ለመዋሸት ስትፈተን ብቻ ነው፡፡ ቶሎ መንገድህን ካልቀየርክ በስተቀር ውሸት በዋሸህ ቁጥር ሰውነትህ ለሌላ ውሸት ያለው ፍላጎት ይጨራል እንጂ አይቀንስም፡፡ የውሸት አታላይነቱ አንዴ ብቻ ዋሽ ብሎህ ነገር ግን ህይወትህ በውሸት እስኪሞላ እና እስክትዋረድ ድረስ ውሸት አይለቅህም፡፡ በዋሸህ ቁጥር ሰውነትህ ለመዋሸት ያለው ፍላጎት ከፊት የልቅ እየጨመር ይሄዳል፡፡

በአጠቃላይ ሃጢያትንም እንደዚሁ በአንድ አያበቃም፡፡ ስጋ ይህችን ሃጢያት ብቻ ስራ እና ደስ ይበልህ ብሎ ያንቆላልጨናን እንጂ በአንድ ሃጢያት እርካታ እንምደማይገኝ የምናውቀው ከብዙ ሃጢያት በኋላ ይህችን አንድ ጊዜ ብቻ ብሎ ሊያታልልን ሲሞክር ነው፡፡  ስጋችን ሁል ጊዜ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብቻ ስራና ታርፋለህ ይለናል፡፡ ነገር ግን የሃጢያት አንድ ጊዜ የለውም፡፡ ለስጋችን ሃጢያት በሰጠነው ቁጥር የሃጢያት ፍላጎቱ ከፊት ይልቅ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም፡፡ 

በተቃራኒው ውሸትን በመጀመሪያ በማለዳ እንቢ ካልከው በቀጣይነትም እንባ ባልከው መጠን ሃይሉ እየቀነሰ እየደከመ ይሄዳል፡፡

ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ የዮሐንስ ወንጌል 319-20

No comments:

Post a Comment