Popular Posts

Sunday, August 21, 2022

ከአእምሮ በላዩ የእግዚአብሔር ቸርነት

 

እግዚአብሔር መልካም ነው። መልካምነቱ እጅግ በጣም ጥሩ ከመሆኑ የተነሳ ቸርነቱ ከማንም ቸርነት ጋር ሊወዳደር አይችልም።

እኛ በብዙ ነገር ውስን ነን። አንድን ቃል ስንሰማ የቃሉን ትርጉም በልምዳችን እንገድበዋለን። ሀሳባችን ከልምዳችን በላይ መሄድ አይችልም። ቸርነት የሚለውን ቃል ስንሰማ በህይወታችን ውስጥሉት መልካም ነገሮች ልምምድ ይወሰናል

የእኛ የመልካምነት ትርጓሜ ውስን ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው "እግዚአብሔር መልካም ነው" ሲል መልካምነቱን ልንገምት እንችላለን፡፡ ነገር ግን መልካምነትን በምናውቀው ሰው ላይ ከምናየው መልካምነት ባሻገር መገመት አንችልም። ለዚህም ነው ኢየሱስ ቸርነት የሚለው ቃል ከምድራዊው አባት ቸርነት ጋር እንዳይምታታ ቸርነት የሚለውን ቃል የበለጠ የገለፀው

እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ስጦታን አይሰጣቸውም? ማቴዎስ 711

የእግዚአብሄርን ቸርነት በጥሩ ሰው መልካምነት ከገደብነው የእግዚአብሄርን ቸርነት ሙሉ ለሙሉ ልንረዳውና ልንደሰትበት አንችልም።

የእግዚአብሔር ቸርነት ከማንም ሰው ቸርነት ጋር ሊወዳደር አይችልም። አምስ ምክንያቶች

v  የእግዚአብሔር ማስተዋል የማይመረመር ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል። እሱ የማያውቀው ነገር የለም፡፡ ሰፊ እውቀቱን ለጥቅማችን ይጠቀምበታል። አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 4028

v  እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ ሊጠረጠር አይችልም። እግዚአብሔር አፍቃሪ ብቻ ነው። እውነት ነው እኛም ፍቅርን እንለማመዳለን፡፡ ነገር ግን ፍቅራችን ከስግብግብነት እና ከራስ ወዳድነት ጋር ሊደባለቅ ስለሚችል ውስን ነው፡፡ በምድር ላይቀጣይነት ትግል ላይ ነን። የእኛ መልካምነት እንደ እግዚአብሔር መልካምነት ፍጹም ላይሆን ይችላል። የእግዚአብሔር ቸርነት ከፍቅሩ ጋር ፍጹም ነው።

v  እግዚአብሔር አይለወጥም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፡፡ አእምሮው የማይመረመር ነው፡፡ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። የያዕቆብ መልእክት 1፡17

v  እግዚአብሔር በሰማይ ይኖራል። እግዚአብሔር እኛ በምንፈተንበት በማንኛውም መንገድ አይፈተንም፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ፍጹም ነው።

v  እግዚአብሔር ዋቢ ነው። እግዚአብሔር መልካም ብቻ አይደለም። እርሱ የመልካምነት ዋቢ ነው። እሱ የመልካምነት መለኪያ ነው። እሱ መልካም ነው የሚለው ሁሉ መልካም ነው፡፡ እሱ መልካም አይደለም የሚለው ሁሉ መልካም አይደለም፡፡ ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው ኢሳይያስ 520


No comments:

Post a Comment