Popular Posts

Sunday, August 7, 2022

The sooner you pray, the better.

Until now, you have not asked for anything in my name. Ask and you will receive, and your joy will be complete John 16:24
We are created to relate to God and to be happy and joyful. We are created to constantly pray to God.
But not everyone is joyful. And some people are not joyful at all.
Some people only pray to God as a last resort. They try everything else and remember God at last. They don’t have joy.
The others pray only when they come across challenges in life. If they don’t come across difficult situations, they think they can handle them and don’t pray continuously and their Joh isn’t complete. But there are those who pray and ask God before they move. They don’t trust their understanding; they acknowledge God in all their ways. Their joy is complete.
Trust in the LORD with all your heart And do not lean on your own understanding. In all your ways acknowledge Him, And He will make your paths straight Proverbs 3:5
They don’t try to get God's approval for their creative ideas and plans. They ask God for His plan for their lives in the first place.
For I know the plans I have for you," declares the LORD, "plans to prosper you and not to harm you, plans to give you hope and a future." Jeremiah 29:11
ቀድሞ መፀለይ የተሻለ ነው
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። ዮሐንስ 16፡24
የተፈጠርነው በቀጣይነት ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንድናደርግ እና በዚያም ደስተኛ እንድንሆን ነው። የተፈጠርነው ያለማቋረጥ ወደ እግዚአብሔር እንድንጸልይ ነው።
ግን ሁሉም ሰው ደስተኛ አይደለም፡፡ እና አንዳንድ ሰዎች በጭራሽ ደስተኛ አይደሉም።
አንዳንድ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የሚጸልዩት ሁሉንም ነገር ሞክረው እንደ መጨረሻ አማራጭ ብቻ ነው። ሌላውን ሁሉ ሞክረው በመጨረሻ ብቻ እግዚአብሔርን ያስታውሳሉ። ስለዚህ በህይወታቸው ደስታ የላቸውም።
ሌሎቹ የሚጸልዩት በህይወታቸው ውስጥ ተግዳሮቶች ሲያጋጥሟቸው ብቻ ነው። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ካላጋጠሟቸው በስተቀር ተግዳሮቶቹን በራሳቸው መቋቋም እንደሚችሉ በትህምከት ያስባሉ፡፡ ስለዚህ ያለማቋረጥ የእግዚአብሄርን ፊት አይፈልጉም አይጸልዩም ትሁት ስላይደሉ ደስታቸው ሙሉ አይደለም፡፡
ነገር ግን ምንም ነገር ለማድረግ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት የሚጸልዩ እና ለህይወት አቅጣጫ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የሚጠይቁ አሉ። ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ በማለት ሲጀመር ወደእግዚአብሄር የሚቀርቡ አሉ፡፡ አስቀድመው ለምሪት እግዚአብሄርን የሚፈልጉ ሰዎች በራሳቸው ማስተዋል አይደገፉም፡፡ በመንገዳቸው ሁሉ ለእግዚአብሔር መሪነት እውቅና ይሰጣሉ። ስለዚህም ደስታቸው ሙሉ ነው።
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ። በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ ጎዳናህንም ያቀናልሃል መጽሐፈ ምሳሌ 3፡5
እግዚአብሄር አስቀድሞ ለህይወታቸው በቂ እቅድ እንዳለው ይረዳሉ፡፡ ለራሳቸው የፈጠራ ሃሳቦች እና እቅዶች የእግዚአብሔርን ይሁንታ ለማግኘት አይሞክሩም። በመጀመሪያ እግዚአብሄር ለህይወታቸው ያለውን እቅድ ከመጀመሪያው እግዚአብሔርን ይጠይቃሉ። የእግዚአብሄርን አላማ ካላገኙ በስተቀር ምንም እርምጃ አይወስዱም፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29:11
No photo description available.
See insights and ads
1
1 Share
Like
Comment
Share

No comments:

Post a Comment