Popular Posts

Saturday, August 6, 2022

ልበ ንጹሖች

 

ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

ማቴዎስ 5:8

በህይውታችን እግዚእብሔርን ማየት ከፈለግን የልብ ንፅህና ወሳኝ ነው::

ሰው በተፈጥሮው ንፁህ ነገርን ይፈልጋል:: ቤቱን በትጋት ያፅዳል:: መኪናውን በትጋት ያሳጥባል:: ሰውነቱ ሲቆሽሽ እንደገና እስኪታጠብይቸኩላል:: ልብሱ እንዲቆሽሽ በፍፁም አይፈልግም:: 

ከእነዚህ ነገሮች ንፅህና በላይ ሊያሳስበው የሚገባው የልብ ንፅህናነው:: እነዚህ ነገሮች ቢቆሽሹ የሚያየው ሰው ነው:: ከእነዚህ ነገሮችበላይ በመንፈሳዊ ህይወታችን ላይ ትልቅ አሉታዊ ትፅእኖየሚፈጥረው የልብ ንፅህና ጉድለት ነው:: ከምንም ነገር ንፅህና በላይሙሉ ትኩረታችንን እና ትጋታችንን ሊጠይቅ የሚገባው የልብንንፅህና መከታተል ነው:: የልብ ንፅህና ልብን የሚመረምረውንንናየሚያነፃውን የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና መታዘዝ ይጠይቃል:: 

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለውሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንናቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገርየተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረትየለም። ዕብራዊያን 4:12-13 

እነዚህ ነገሮች በክፉ አሳብ የሰውን የልብ ንፅህና በማቆሸሽ ሰውንያረክሳሉ::

እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ  ነው። ከውስጥከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣልሰውን ያረክሰዋል። ማርቆስ 7:20-23

የልባችንን ንፅህና በትጋት በመጠበቅ ልባችንን ከህይወት ቆሻሻበትጋት መጠበቅ ይኖርብናል:: 

አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።ምሳሌ 4:23

No comments:

Post a Comment