Popular Posts

Friday, June 21, 2019

እግዚአብሄር ያሳፍራል



ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። ነገር ግን፡የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ፡ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው። 1 ቆሮንቶስ 1:26-31
v  ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤
እግዚአብሔር ጥበበኛን ቢመርጥ የሚረዳው ፈልጎ ነው ይባላል:: እግዚአብሔር እኛን ይረዳል እንጂ በማናችንም አይረዳም :: እግዚአብሔር ክብሩን ለማንም ስለማይሰጥ ሞኝን ነገር መረጠ:: እግዚአብሔር ሞኝን ጠቢብ ቢያደርግ ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው ይባላል::
ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የሐዋርያት ሥራ 4:13
v  ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
እግዚአብሄር ከሰው ጋር አይወዳደርም:: እግዝአብሄር እኛን የሚያዋርደው ያንሰኛል እበልጠዋለሁ በምንለው ሰው ነው:: እግዚአብሔር ደካማውን ያበረታና የምንመካበት የእኛ ብርታት ምንም እንዳይደለ ያሳየናል::
እርሱም፡ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና፡ አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። . . . ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2 ቆሮንቶስ 12:9-10
v  እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥
እግዚአብሔር ይህ የትም አይደርስም የተባለውን አስነስቶ እርሱ ብቻ ክብሩን መውሰድ ይፈልጋል::
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1 ሳሙኤል 2:8
እግዚአብሄር በተናቀው ተጠቅሞ የናቀውን ትእቢተኛውን ያስቀናል::
ነገር ግን፡እስራኤል ባያውቁ ነው ወይ? እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ፡እኔ ሕዝብ በማይሆነው አስቀናችኋለሁ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣችኋለሁ፥ ብሎአል። ወደ ሮሜ 10:19
ሰው በእግዚአብሔር ፊት የሚያስመካው አንዳች ነገር የለም:: ምንም እንድንበልጥ ያደረገን ነገር ቢኖረን ከእርሱ የተቀበልነው ብቻ ነው፡፡
አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡7
ሰው መመካት የሚችለውና የሚገባው እስትንፋሳችንን በእጁ በያዘው በጌታ ብቻ ነው::
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ #ዝቅታ #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment