Popular Posts

Monday, January 4, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #አራት ፍቅር የማይገባውን አያደርግም

 


አቢይ የጥሞና ቃል #አራት ፍቅር የማይገባውን አያደርግም

ፍቅር . . . የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡5

ፍቅር የህግ ፍፃሜ ነው፡፡ ማንኛውም ህግ የተሰጠው ሰው በፍቅር እንዲኖር ለማስቻል ነው፡፡ በፍቅር የሚኖር ሰው እግዚአብሄርን በማስደሰት የተፈጠረበትን አላማ ከግብ ያደርሳል፡፡

ከፍቅር ባህሪዎች መካከል አንዱ ደግሞ ፍቅር የማይገባውን አለማድረጉ ነው፡፡  

የማይገባውን የሚያደርግ ሰው ሌላውን የማያከብር ፣ እንደፈለገ የሚናገር ፣ እንደፈለገ የሚያደርግ ፣ ትሁት ያልሆነ ፣ ሌላውን የሚያስቀይም ፣ መጥፎ ባህሪ ያለው ፣ ለሌላው የማይጠነቀቅ ሰው ነው፡፡

ፍቅር የማይገባውን አያደርግም ማለት ፍቅር ሌላውን ያከብራል ፣ ለሌላው ይጠነቀቃል ፣ እንዳመጣለት አይናገርም ፣ እንደፈለገ አያደርግም ማለት ነው፡፡

ፍቅር የማይገባውን አያደርግም ማለት ፍቅር ትሁት ነው ፣ ፍቅር ለራሱ የግል ጥቅም ብሎ ሌላውን ላለማስቀየም ይጠነቀቃል፣ ፍቅር ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ይተጋል ማለት ነው፡፡

ፍቅር የማይገባውን አያደርግም ማለት ፍቅር የማይገባውን ጥቅም አይፈልግም ፣ ፍቅር የየትኛውም ችግር መንስኤ ላለመሆን ይጠነቀቃል፣ ፍቅር የሚያደርገው ማድረግ የሚገባውን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡

ፍቅር ያለው ሰው በእርሱ ምክንያት ሌላው ከሚጎዳ እርሱ ቢጎዳ ይሻለዋል፡፡

ፍቅር ያለው ሰው የመርህ ሰው ነው፡፡ ፍቅር ያለው ሰው እርሱን የማይጠቅመውም ቢሆን ስለእውነት ትክክለኛውን ነገር ያደርጋል፡፡ ፍቅር ያለው ሰው እርሱን የሚጎዳውም ቢሆን እውነትን ይኖራል፡፡

ፍቅር . . . የማይገባውን አያደርግም፥

እግዚአብሄር ሆይ በዚህ ቀን በፍቅር ለመመላለስና የማይገባኝን ላለማድርግ ቃል አገባለሁ፡፡ መንፈስህ ስለሚመራኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን !

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና

No comments:

Post a Comment