አቢይ ጥሞና #አንድ
አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 6፡33
ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በህይወቱ የእግዚአብሄርን ነገር እንዲያስቀድም ነው፡፡ ሰው
የተፈጠረው የእግዚአብሄርን ፅድቅ እንዲፈልግ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው እግዚአብሄርን በሁለንተናው እንዲከተል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው
በሚሰራው ስራ ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ እንዲኖር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄርን መንግስት እንዲኖር
ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው አስቀድሞ የእግዚአብሄርን መንግስት መልካምነት እንዲፈልግ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር መንግስት
ማሸነፍ እንዲሰራ ነው፡፡
ሰው የተፈጠረበትን የእግዚአብሄርን አላማ ሲከተል በህይወቱ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይይዛል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ነገር
በህይወቱ ካላስቀደመ ግን የተፈጠረበትን አላማ ስለሳተው በህይወቱ ሁሉም ነገር ይዘበራረቃል፡፡
ሰው እግዚአብሄርን አስቀድሞ የሚያጣው እና የሚጎድልበት ነገር አይኖርም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲያስቀድም የተፈጠረበትን
አላማ ስለሚከተል በምንም ነገር ውስጥ ቢያልፍ ደስተኛ ይሆናል፡፡ ሰው በህይወቱ ማስቀደም ያለበትን የእግዚአብሄርን አላማ ካላስቀደመ
ምንም ነገር ቢሆንለትም በእምነት ብቻ በመኖር ከእግዚአብሄር ብቻ በሚገኘው እርካታ ደስተኛ ሊሆን አይችልም፡፡
የሰው ሃላፊነት የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ሃላፊነት ሰው የሚያስፈልገውን ነገር
ሁሉ ማሟላት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረበትን አላማ እግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስት እስከፈለገ ድረስ ስለሚበላውና ስለሚጠጣው እስከማይጨነቅ
ድረስ እግዚአብሄር የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ያቀርብለታል፡፡
እግዚአብሄር ሆይ በዚህ ቀን ደግሞ የአንተን ፅድቅና መንግስት እፈልጋለሁ፡፡ አንተም የሚያስፈልገኝን ስለምትጨምርልኝ
አመሰግንሀለሁ፡ በኢየሱስ ስም አሜን፡፡
#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ
#ሐዋርያጥሞና
No comments:
Post a Comment