Popular Posts

Monday, January 11, 2021

አቢይ የጥሞና ቃል #አምስት የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅ

 


አቢይ የጥሞና ቃል #አምስት የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅ

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና። ወደ ሮሜ ሰዎች 1417

ኢየሱስ ክርስቶስን አንደ አዳኛችን ተቀብለን የምንኖርባት ፣ እግዚአብሄር ንጉስዋ የሆነላትና በአይን የማትታየው የእግዚአብሄር መንግስት በጽድቅና በሰላም ብሎም በመንፈስ ቅዱስም በሆነ ደስታ ላይ ብቻ የተመሰረተች ናት፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ከእነዚህ ከጽድቅና ከሰላም በመንፈስ ቅዱስም ከሆነ ደስታ ውጭ ልትመሰረተም ፣ ልትታይም ብሎም ልትለካም አትችልም፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ሃላፊነትዋም ጥቅምዋም ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎችዋን የምትባርክው በፅድቅ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የምትታወቀው በራሳቸው ጽድቅ የሌላቸውን ሃጢያተኛ ሰዎች ስለእነርሱ በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ፅድቅ ማፅደቅ ነው፡፡

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 521

የእግዚአብሄር መንግስት ስለ ፅድቅ ትኖራለች፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ስለ ፅድቅ ትቆማለች፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የምትኖረውም የምትቆመውም የምትሰራውም ስለፅድቅ ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት ካለ ፍርሃትና ካለ በታችነት ስሜት በእግዚአብሄር ፊት የመቆም የልጅነት መብት ነው፡፡

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ወደ ዕብራውያን 416

የእግዚአብሄር ፅድቅ የእግዚአብሄር ልጅነት መብት ነው፡፡

ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12

የእግዚአብሄር መንግስት በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ሆኖ የመገኘት ሃላፊነት ነው፡፡

የእግዚአብሄር መንግስት መንግስቱን እና ፅድቁን የማስቀደም ሃላፊነት ነው፡፡  

እግዚአብሄር ሆይ በልጅህ በክርስቶስ በኩል ስለሰጠኽኝ የክርስቶስ ፅድቅ አመሰግንሃለሁ፡፡ በክርስቶስ እንደተወደደ ልጅ  በፊትህ እመላለሳለሁ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!

#አቢይጥሞና #ሐዋርያውአቢይ #ሐዋርያጥሞና

No comments:

Post a Comment