Popular Posts

Friday, January 22, 2021

የመተው ባለጠግነት

 

እግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር እንድንይዘው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር እንዳንይዘው እንድንለቀው የሚፈልገው ነገር አለ፡፡ እግዚአብሄር እንድንለቀው የሚፈልግውን ነገር ብንይዝ እኛ እንጎዳለን፡፡

ሰው አንዴ የያዘውን እግዚአብሄር ቢያሳየውም ለመልቀቅ የሚያመነታው አንድ ጊዜ ሰርቶለት ስለሚያውቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር በፈጠራ የተሞላ አምላከ ነው፡፡ እግዚአብሄር አንድ መንገድ ብቻ የለውም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ አሰራር ብቻ አይወስንም፡፡

ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡10

ሰው አንዴ የያዘውን ነገር መልቀቅ የማይፈልገው አጣለሁ ይጎድልብኛል ብሎ ስለሚፈራ ነው፡፡

አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ። ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። የሉቃስ ወንጌል 6፡37-38

እግዚአብሄር በሰው ላይ የያዝነውን ቂም እንድንተው ሊፈልግ ይችእላል፡፡ እግዚአብሄር ያበደርነውን እንድንተው ሊነግረን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ክስን እንድንተው ሊጠይቀን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር የማይፈልገውን ልምምድ እንዳናደርግ ሊያዝዘን ይችላል፡፡

በምንም መልኩ ይሁን መተው ያለብንን አለመተው እግዚአብሄር ካሰበልን ከሚበልጠው ነገር ያጎድለናል፡፡

መተው ያለብንን ነገር አለመተው እግዚአብሄር ወዳሰበልን ወደሚቀጥለው የህይወት ደረጃ እንዳንሻገር ያቆመናል፡፡

መተው ያለብንን ነገር እንደመተው ያለ ባለጠግነት ደግሞ ከሰማይ በታች የለም፡፡

አግዚአብሄር ተው ይበለን እንጂ ለመተው ዛሬውኑ መወሰን አለብን፡፡

የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ወደ ዕብራውያን 10፡34

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/AbiyWakumaDinsa/notes

Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

#አዲስፍጥረት #አዲስ #መዋጀት  #መዳን #ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #መልቀቅ #አቁማዳ #መተው #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ጌታ #ማሪያም #መላእክት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ሰላም ትግስት #ልጅ


No comments:

Post a Comment